Mols.gov.et

News

News

“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሼል ባህል እድገትና ምርታማነት!”

“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሼል ባህል እድገትና ምርታማነት!”
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ምርታማነት ማረጋገጥ የሚያስችል የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ለማስጀመር በአመቻችነት የሚሳተፉ የአሰልጣኞች ሥልጠና ሁለተኛ ዙር መድረክ በሲዳማ እና በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የጅግጅጋውን መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የሱማሌ ክልል ብልጸግና ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀመረው በሥራ ባህል ላይ የሚደረገው ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ለዘመናት ተሸክመነው የቆየውን ድህነትና ኋላቀርነት ማራገፍ የሚስችል አዲስ መንገድ ነው ብለዋል።
የሀዋሳውን መድረክ በንግግር የከፈቱት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ኃላፊ እና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ገቢሳ በበኩላቸው፣ የማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይት በትኩረት መተግበር ከተቻለ የሥራ ባህል በመቀየር በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።
መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከኦሮሚያ፣ ከድሬዳዋ ከሀረሪ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኢትዮጽያ እና ከሱማሌ ክልሎች የተወጣጡ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰልጣኞች እየተሳተፉበት ይገኛል።

Read More Âť
News

የምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጣናዊ የሚኒስትሮች ፎረም …

የምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጣናዊ የሚኒስትሮች ፎረም አባል ሀገራት በሰራተኛና ፍልሰት አስተዳደር ዙሪያ የሚያደርጉትን ትብብር ማላቅ የሚያስችል ውይይት አካሂደናል፡፡
ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የምትመራው ይህ ፎረም 11 አባል ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን በዘርፉ የሚስተዋለውን ህገወጥ የሰራተኞች ፍልሰት ችግርን ለመፍታት ከመዳረሻ ሀገራት፣ ከዘርፉ ተዋናዮች፣ ከሀጉር እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት እና ምክክር ማድረግ እንደሚገባ ተመልክተናል፡፡
ፍልሰትን ማስተዳደር እንጂ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት እንደማይቻል ከግምት በማስገባት በቀጠናው የአስተዳደር ስርዓቱን ለማሻሻል፣ የመዳረሻ ሀገራትን ፍላጎት ያማከለ የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ልማትን ለማስፋት እንዲሁም የሰራተኛ ፍልሰት እና ልማትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ የባለብዙ ወገን የጋራ ትብብር ለመፍጠር ተግባብተናል፡፡
በመድረኩ ላይ ለተገኛችሁ የምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም የገልፍ ሀገራት አምባሳደሮች እና የኤምባሲ ተወካዮች ለነበራችሁ እሴት አካይ ተሳትፎ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
Ahead of the upcoming 5th High-Level Ministerial Forum slated for 29 February in Addis Ababa, I held a fruitful round-table discussion on labor migration governance that brought together Addis-based Ambassadors of Member States of the East and Horn of Africa Regional Ministerial Forum on Migration (RMFM) and those of GCC and Middle East countries.
Chaired by Ethiopia since April 2022, the RMFM consists of 11 member countries. It champions the harmonization of migration policies in the East and Horn of Africa region.
In our discussion today, we have heartily discussed the need for continuous dialogue and consultation with countries of destination, regional, continental and international stakeholders to deal with the formidable challenges irregular migration is posing.
I am also heartened by the promising gestures from ambassadors of both sides to improve the migration management systems in our regions, to expand the development of skilled and semi-skilled labor force tuned to the needs of countries of destination, and above all to create an inter-regional and multilateral cooperation beyond bilateral relations on issues related to labor migration and development.
On behalf of the RMFM Members States and of my Ministry, a huge thank you to ambassadors and representatives of GCC, of Middle East as well as of the RMFM Member States.

Read More Âť
News

“ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው፡፡” …

“ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው፡፡”
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የመጀመሪያው ዙር ማጠቃለያ እና የሁለተኛ ዙር ምዕራፍ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተከናውኗል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለፁት፤ መንግስት የሥራ አጥነት ምጣኔን ለመቀነስ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው ክህሎት መር እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ በዘርፉ ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በመደበኛ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጓዳኝ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር “ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም” ተግባራዊ በማድረግ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ ወጣቶችን ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ይህ ፕሮግራም ወጣቶች በሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አቅም ከመገንባት አንፃር በርካታ ልምድና ተሞክሮዎች የተገኘበት ነው፡፡
ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው ብለዋል።
ለፕሮግራሙ ስኬት አበርክቶ ለነበራቸው የዘርፉ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በፕሮግራሙ አንደኛ ዙር ትግበራ የተገኙ ተሞክሮዎችን ቀምሮ በሁለተኛው ዙር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የድሬዳዋ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁዋር በበኩላቸው፣ መርሃ ግብሩን በጋራ እውን ላደረጉት ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለዓለም ባንክ ምስጋና አቅርበው በከተማ የጀመረው መርሃ ግብር ወደ ገጠር አካባቢም እንዲሰፋ ጠይቀዋል።
የድረዳዋ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ከተሳተፉት ወጣቶች መካከል 96 በመቶ የሚሆኑትን ቋሚ የስራ ዕድል ባለቤት ማድረግ ተችሏሏ።
ከዚህ ባለፈም ለሁለተኛ ዙር ትግበራ መሰረት የጣለ፣ የመንግስት እና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያጎለበተ እና የሥራ ላይ ልምምድ ባህል እንዲዳብር ያስቻለ ስኬታማ ፕሮግራም ነው ብለዋል።

Read More Âť
News

መድረኩ ያሉንን ጠንካራ ጎኖችን የለየንበት እና ጉድለቶቻችንን ለማረም በጋራ የተግባባንበት ነው።

“መድረኩ ያሉንን ጠንካራ ጎኖችን የለየንበት እና ጉድለቶቻችንን ለማረም በጋራ የተግባባንበት ነው።”

ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ሼል በክህሎት ይመራ!” በሚል መሪ ሀሳብ ከክልሎች፣ ተጠሪ ተቋማቱ፣ ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በሠመራ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የመጀመሪያውን ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የምክክር መድረክ አጠናቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስተቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለፁት፣ መድረኩ በሥራ ስምሪት፣ በክህሎት ልማት እና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ያሉ ጠንካራ ጎኖች የለየንበት እና ያሉ ጉድለቶችንም ለማረም የተግባባንበት ስኬታማ መድረክ ነው።
ሥራ በክህሎት እንዲመራ በተጀመረው ከፍተኛ ጥረት በርካታ ዜጎች ሰልጥነው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው በቀሪ ወራት በሶስቱም ዘርፍ ቀሪ ስራዎቻችን ማሳካት በሚያስችል መልኩ መረባረብ ይገባል ብለዋል።
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፣ በጀት ዓመቱ አበረታች ስራዎች የተተገበሩበት እንደነበር ገልጸው የስልጠና ጥራት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን በመገንዘብ በልዩ ትኩረት ልንመራው ይገባል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነቢሃ መሃመድ እንደገለጹት በየደረጃው በእቅድ የተግባባንባቸው ስራዎች የሚገኙበት ደረጃ ለማየት ሀገር አቀፍ የሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ድጋፍና ክትትል አድርጓል።
በዚህም በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸውን በድጋፍና ክትትሉ መረጋገጡን ገልጸው በጉድለት የታዩ ጉዳዮች ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚወርድ ጠቁመዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በርካታ ልምድና ተሞክሮ ያገኙበትና ለቀጣይ ሥራዎች መግባባት የፈጠሩበት መሆኑን ጠቁመው በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛው ዘርፍ ላይ ሊሻሻሉ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እድሳት ላይ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አካላት እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

Read More Âť
News

“ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና መረጋጋትን እንዱሁም ሼል ፈጣሪ ዜጎችን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች።”

“ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና መረጋጋትን እንዱሁም ሼል ፈጣሪ ዜጎችን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች።”

ክቡር አቶ አወል አርባ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከክልል እና ተጠሪ ተቋማቱ ጋር የሚያካሂደው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ እና የምክክር መድረክ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና መረጋጋትን እንዱሁም ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች።
ድህነት፣ ሥራ አጥነትና ህገ ወጥ ስደት የህዝባችን መሠረታዊ ከሚባሉት ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ይህንን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ የጋራ ርብርብን ይጠይቃል።
“ሼል በክህሎት ይመራ!” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ይህ መድረክ ይህንና መሰል ችግሮችን በመፍታት ሰላምና መረጋጋት እንዲሠፍንና የታቀደው ልማትና ብልፅግና እውን እንዲሆን ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሰምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው፤ መድረኩ ሰኬቶቻችንና የጋጠሙ ተግዳሮቶች የምንፈትሽበት እና ለቁልፍ ችግሮቻችን ቁልፍ የሆኑ መፍትሄዎች የሚቀመጡበት ነው ብለዋል።

Read More Âť
News

የሥራ ላይ ልምምድ ለወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የላቀ ድርሻ አለውደ…

“የሥራ ላይ ልምምድ ለወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የላቀ ድርሻ አለው”

ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

‹‹ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› ሁለተኛ ዙር ትግበራ በሐዋሳ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
በፕሮግራሙ ማብሰሪያ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ለወጣቶች የተሟላ ክህሎት በማላበስ ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ድርሻው የላቀ ነው ብለዋል፡፡
የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ወደ ሥራ ላይ ልምምድ ከመሰማራታቸው በፊት የህይወት ክህሎት፣ የሥራ ፈጠራ፣ የኮምፒውተርና ሙያዊ ክህሎት ሥልጠናዎችን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አማካኝነት ማግኘታቸው ለሥራ ገበያው ራሳቸውን ለማዘጋጀት እንዳስቻለቸው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡
ወጣቶቹ በዚህ መልኩ ያደረጉት ቅድመ ዝግጀት በተሠማሩበት የሥራ ላይ ልምምድ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ጉልህ አበርክቶ ነበረው በማለት የሚገልፁት ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በዚህም መሠረት በሐዋሳ ከተማ በ110 ድርጅቶች ውስጥ ለስድስት ወራት የሥራ ላይ ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩ 868 ወጣቶችን ወደ ቅጥር የሥራ መስክ ላይ መሰማራታቸውን አብራርተዋል፡፡

Read More Âť
News

“ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው…

“ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የጋራ ጉባኤ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሎ ሙፈሪሃት ካሚል በክህሎት ልማት፣ ሼል ዕድል ፈጠራ እና ኢንዱስትሪ ሰላም ዙሪያ ገለፃ እያቀረቡ ይገኛል።
በመድረኩ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱም ከተማ አስተዳድሮች የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንና የሚዲያ አመራሮች፣ የሁሉም የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን የሥራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

Read More Âť
News

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በክህሎት ልማት፣ ሼል ዕድል ፈጠራ እና…

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ
“ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የጋራ ጉባኤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሪፎርም ሀሳቦችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚያተኩር ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራ የአንድ ሴክተር ጉዳይ አይደለም፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብቁና ተወዳዳሪ የሰለጠነ የሰው ሃይል የማፍራት፣ የማክሮ ኢኮኖሚው ትልቅ ስብራት የሆነውን የሥራ አጥነት ችግር ትርጉም ባለው መልኩ የመቀነስ እና ምርታማነትን ማዕከል ያደረገ የኢንዱስትሪ ግንኙነት የመፍጠር ተልዕኮ አለው፡፡
ይህም በትኩረት ከሰራንበት የትላንት የተከማቸ ዕዳን የሚመልስ፣ የዛሬ ዕድላችንን የሚወስን እና የነገ ተስፋችንን ብሩህ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡
ስለሆነም እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ልማትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተቀመጠው ግብ እንዲሳካ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡
በተለመደው አካሄድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እንደማይቻል ከግምት በማስገባት ሁሉም በትልቁ አቅዶ በትልቁ መፈፀም የምርጫሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
ስለሆነም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ያላቸው ሚና የማይተካ መሆኑን የገለጹት ክብርት ሚኒስትር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት በዘርፉ የጋራ መግባባት መፍጠር እና የባህሪ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎችን በመስራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ አምስቱን የኢኮኖሚ የትኩረት መስኮች ላይ የሚያጠነጥኑ ሥራዎችን መስራት ይኖርበታል፡፡
ሃገራዊ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዓላማን በአግባቡ በመረዳት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን እቅድ ውስጥ አካቶ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

Read More Âť
News

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ……

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር …
በጀርመን ቆይታችን በደቡባዊ ባቫሪያ በምትገኘው ጥንታዊቷ ዌልሃይም ከተማ የሚገኙትን የሕዝብ የሙያ ማሰልጠኛ ተቋምን፣ የዕደ-ጥበብ ማዕከልን እንዲሁም በኢኖቬቲቭና ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሚታወቀውን ኤፌ ባወር የቤተሰብ ትውልድ ተሻጋሪ ድርጅት ጎብኝተናል፡፡
በሥራ ጉብኝታችን በትምህርትና ስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪው መካከል ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራትም፣ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንም ሆነ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ ተመልክተናል፡፡
በማሰልጠኛ ተቋማትና በኢንዱስትሪዎች መካከል በሚፈጠር ጠንካራ ግንነት የሚሰጠው የሁለትዮሽ የትብብር ስልጠና ሰልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ያለፈ በተግባር እውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ዕድልን የሚፈጠርላቸው እንደሆነም አይተናል፡፡ ይህም በየሙያ መስኩ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ መሆኑን ከግምት በማስገባት እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ሥራዎች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡
ይህ የሥራ ጉብኝት በዘርፉ ለጀመርናቸው ተስፋ ሰጪ የሪፎርም ሥራዎቻችን ግብዓት የሚሆኑ ልምድና ተሞክሮዎችን ያገኘንበትና በብዙ ያተረፍንበት ነው፡፡ ስለሆነም መርሃ ግብሩን ላመቻቹልን እና ተሞክሮዎቻቸውን ላካፈሉን አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

Read More Âť
News

በሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኘው የልዑካን ቡድናችን በሀገረ ጀርመን በጋርቺንግ ከተማ …

በሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኘው የልዑካን ቡድናችን በሀገረ ጀርመን በጋርቺንግ ከተማ ታዋቂው የሳይንስ ጥናትና የምርምር ማዕከል የሚገኘውን የስታርትአፖች መፈልፈያ ማዕከልን የመጎብኘት ዕድል አግኝተናል፡፡
ጌት ጋርቺንግ (gateGarching) የተሰኘው ይህ ማዕከል በከፍተኛ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ ለሚሰማሩ ስታርትአፖች ከስልጠናና ማማከር ጀምሮ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
በማዕከሉ የነበረን የሥራ ጉብኝት እንደ ሀገር ሪፎርሙን ተከትሎ ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችና ስታርታፖች ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር የጀመርነውን ሥራ ለማላቅ የሚያስችል ልምድና ተሞክሮ ያገኘንበት ነው፡፡
የማዕከሉ ም/ል ዋና ዳይሬክተር ካትጃ አቤሌና የሥራ ባልደረቦቻቸው ከተጨባጭ ተሞክሮ በመነሳት ለስታርትአፖች ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር መከተል ስለሚገባን ስትራቴጂ ስላካፈላችሁን ልምድ እና ስላደረጋችሁልን ደማቅ አቀባበል ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills