
የሀገር ብልጽግናን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ለመደገፍና ኮትኩቶ ወደ ውጤት ለመቀየር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
የሀገር ብልጽግናን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ለመደገፍና ኮትኩቶ ወደ ውጤት ለመቀየር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች መደገፍና ወደ ውጤት መቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከፋይናንስ ተቋማት እና ከልማት አጋሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ሀገር ወደ ብልጽግና የሚያሻግሩ ትላልቅ ካምፓኒዎች ለመፍጠር መሰረት የሚጥሉ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን ለመደገፍ እና ወደ ውጤት ለመቀየር በተናጠል ከመሄድ ይልቅ ተቀናጅቶ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ብሩህ ኢትዮጵያ- የፈጠራ ሃሳቦች በሚል ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው አወዳድሮ በመለየት ወደ ፌዴራል የሚያልፉ ሀሳቦች ላይቶ የማሰልጠን፣ የመሸለም እና የማብቃት ስራ ሲሰራ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር እየፈለቁ የሚገኙ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች በርካታ ከመሆናቸው የተነሳ ሃሳቦች በሚፈለገው ልክ ደግፎ እና ኮትኩቶ ለሀገር እድገትና ብልጽግና ለመጠቀም የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ሥራውን በማገዝ ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደገባ ጠቁመዋል፡፡
ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ5 መቶ በላይ የፈጠራ ሃሳቦች መለየታቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ከነዚህ መካከል 251 የሚሆኑ የፈጠራ ሀሳቦች ከህዳር 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ አቅማቸው የሚገነባበት ቡትካምፕ ይገባሉ ብለዋል፡፡
በዘንድሮ ብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳቦች ውድድር ላይ ተወዳድረው ከሚያልፉት መካከል የተወሰኑት ሀሳባቸውን ወደ ውጤት እንዲቀይሩ በኤስ ኤን ቪ ሊዌ ፕሮግራም(SNV, LIway program) ለመደገፍ መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡
የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች ቀሪ የፈጠራ ሀሳቦች ወደ ውጤት እንዲቀየሩ በመደገፍ ሀገራዊ ሃላፊነታቸው እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡








