Mols.gov.et

News

News

የሥራ ባህልን በማሳደግ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ በትኩረት እየተሠራ ነው። ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራ ባህልን በማሳደግ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ በትኩረት እየተሠራ ነው።
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ በአዲስ አበባ የሚሊኒየም አዳራሽ ተክፍቷል ፡፡
ኤክስፓው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከደረጃ ዶት ኮም እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ መንግሥት ለዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ከደረጃ ዶት ኮም እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የሥራ ኤክስፖ ሥራ ፈላጊዎች እና ቀጣሪ ድርጅቶችን ለማገናኘትና የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው።
ይህም ከ30ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ያስችላል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ኤክስፓው ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን አመላክተዋል።
የሥራ ባህልን በማሳደግ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ እንዲሁም ቤተሰብንና ማህበረሰብን የምርታማነት ማዕከል ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ተሻለ በሬቻን፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ፣ የትምህት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ አቶ ሳሙኤል ያለው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ካንትሪ ዳይሬክተር፣ አቶ የሱፍ ረጃ የኢትዮ ጆብስ እና ደረጃ እናት ኩባንያ የሆነው የአፍሪካ ጆብስ ኔትወርክ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተገኝተዋል።

Read More »
News

ፈጠራ የታከለበት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት…

ፈጠራ የታከለበት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት…
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓትን ጨምሮ ዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት በማበልፀግና ወደ ሥራ በማስገባት ተስፋ ሰጪና ተጨባጭ ውጤቶችን ለማዝመዝገብ ተችሏል፡፡
ከቴክኖሎጂ አማረጭ ጎን ለጎን በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ፈጠራ በታከለበት የአሰራር ስርዓት ለመፍታት ሚኒስቴሩ ከሚተገብረው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ጎን ለጎን የ ‹‹ Public Sector Innovation Lab ›› ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
ሚኒስቴሩ የጀመረውን የፐብሊክ ሴክተር ኢኖቬሽን ላብ ማጠናከር የሚያስችል ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ ባስተላለፉት መልዕክት ፐብሊክ ሴክተር ኢኖቬሽን ላብ ሚኒስቴሩ የተሰጠውን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ተጨማሪ አቅም ይሆነዋል፡፡
በዚህ ላብራቶሪ በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦች ይፈልቃሉ፣ ችግሮች ተለይተው የመፍትሔ ሀሳቦች ይቀርቡበታል፣ የምርምር እና የትግበራ ሥራዎች ይከናወኑበታል ብለዋል፡፡

Read More »
News

በበጀት ዓመቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተቀመጠውን ሰፊ ዕቅድ ለማሳካት ያሉ ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር መሰራት እንዳለበት ተገለፀ።

በበጀት ዓመቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተቀመጠውን ሰፊ ዕቅድ ለማሳካት ያሉ ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር መሰራት እንዳለበት ተገለፀ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እያካሂዷል፡፡
በውይይቱ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻን ጨምሮ የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተቀመጠውን ሰፊ ዕቅድ ለማሳካት ያሉ ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ታሳቢ በማድረግ መድረኩ እንደተፈጠረ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ተሻለ በሬቻ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል፡፡
በበጀት አመቱ ያስቀመጥነው ግብ ትልቅ እንደመሆኑ የአገር በቀል ዕውቀቶችና ክህሎቶችን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ በማልማት፣ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ለማሳካት ከእሴት ሰንሰለት በመነሣት የሙያ ደረጃዎችን የማሻሻል ሥራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም የሩብ ዓመቱን ግምገማ ከ11 የዲ ኤን ኤ እና ከሶስቱ አበይት አንኳር የሥራ ተግባራት አንጻር ቁጥሮችን በማናበብ ግብረ መልስ መሰጠት አለበት ብለዋል ፡፡
በቀጣይ በግምገማችን እንደችግር የተነሱ እና አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የሆኑት ላይ የማካካሻ ዕቅድ በማዘጋጀት በፍጥነት ወደ ሥራ ይገባል፡፡
እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ የግንኙነት አግባብ መሻሻል እንዳለብት አንስተው የሠራተኛው የመረጃ ልውውጥን ማሳደግ፣ የሪፎርም ሥራዎችን እንዲሁም አበይት ተግባራት ላይ በፖሊሲ፣ በአይ ሶ ስታንዳርድ ፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በመመሪያዎች ፣በመምህራን ልማት እና የሥልጠና ጥራት ላይ በቀጣይ ትኩርት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡

Read More »
News

የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይኖርብናል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይኖርብናል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች የዘርፊን አፈፃፀም ለማላቅ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የምክክር መድረኩን አጠናቋል፡፡
የማጠቃለያ መድረኩ ላይ “Perspective” በሚል ርዕሰ በዘርፉ ትልቅ ልምድና ተሞክሮ ባለው ለማ ደገፋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ ዘርፉ ሀገር ብዙ የምትጠብቅበት በመሆኑ ሥራ አጥነትን ጨምሮ የዘርፉ አንገብጋቢ ችግሮችን ለመቅረፍ አዲስ ዕይታና ልዩ ተነሳሽነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በየዓመቱ በርካታ ዜጎች ሥራ ፈላጊ ሆነው እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ሰለሞን በሥራ ፈላጊው ልክ ረጅም ርቀት መሄድና አንገብጋቢነቱን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይገባል።
በቀጣይ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ግብዓትና ግብይት ላይ እንዲሁም የቤተሰብ ቢዝነስና የማህበረሰብ አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ተቋማዊ ግባችንን ለማሳካት ሁሉንም አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ የጠቆሙት ክቡር አቶ ሰለሞን በየደረጃው በቅንጅት እንዲሠራ አሳስበዋል።

Read More »
News

የሥራ ዕድልን ማስፋት ለሰላማችን መረጋገጥ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት መሰረት በመሆኑ ዋናኛ ተልዕኳችን ነው! ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

የሥራ ዕድልን ማስፋት ለሰላማችን መረጋገጥ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት መሰረት በመሆኑ ዋናኛ ተልዕኳችን ነው!
ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
የሥራ ዕድልን ማስፋት ለሰላማችን መረጋገጥ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት መሰረት በመሆኑ የመንግስት ዋናኛ ተልዕኮ እንደሆነ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪ አየሰጡ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በ2017 በጀት ዓመት 4.3 ሚሊዮን ሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እየጠነከረ መምጣቱን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራው ብዙ ዘርፎችንም ጭምር እያካተተ የሚገኝ መሆኑና የልማት እንቅስቃሴ እያደገ የሚሄድ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ዕቅዱ መያዙንም አብራርተዋል፡፡
በግብርና 39 በመቶ፣ በአገልግሎት 31 በመቶ እንዲሁም በኢንዱስትሪ 29 በመቶ የሥራ ዕድል ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዲጂታላይዜሽንን ተጠቅሞ እየተገበረ በሚገኘው የሪፎርም ሥራዎች ባለፉት 3 ወራት 1መቶ ሺ ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር ለሥራ ማሰማራት መቻሉንም በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 7መቶ ሺ ሰዎችን በውጭ ሀገር ሥራ ገበያ ላይ ለማሰማራት ዕቅድ መያዙን በማንሳትም በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ተወስኖ የቆየውን የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ወደ አውሮፓ ሀገራትም ጭምር በማስፋት ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች መላክ መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡
በውጭ ሀገራት በሚፈጠሩ የርቀት የሥራ ዕድሎች (outsourcing) ቁጥራቸው ከ26ሺ የሚልቁ ወጣቶች በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም አስረድተዋል፡፡

Read More »
News

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት የሪፎርም ትግበራ ሂደት የልምድ ልውውጥ አካሂደ

በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባቴ የተመራ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት የሪፎርም ትግበራ ሂደት የልምድ ልውውጥ አካሂደ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባቴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሪፎርም ትግበራው አኳያ የሄደበት እርቀት እጅግ የሚደነቅና ጥሩ ግብዓት ያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡
በተለይ መደበኛ ሥራውንና የሪፎርም ሥራውን ጎን ለጎን በተቀናጀ መንገድ የተመራበት መንገድ እጅግ አስተማሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሪፎርም ትግበራ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው፤ ሚኒሰቴሩ በቅርቡ ተደራጅቶ ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ አዲሱን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያከናወነ የሚገኘው አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ትግበራ ሂደትን ከመጀመሪያው ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ድረስ የተከናወኑ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች ላይ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በሪፎርም ሥራው የተከናወኑ እና የተጠናቀቁ ሥራዎችም የኮሚቴ አባላቱ ተዘዋውረው ተጎብኝተዋል፡፡

Read More »
News

ሚኒስቴሩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ አፈፃፀሙን ገመገመ

ሚኒስቴሩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ አፈፃፀሙን ገመገመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይፋ የተደረገው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ በፓይለት ደረጃ እንዲተገበርባቸው ከተመረጡ ተቋማት አንዱ ሆኖ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብቷል፡፡
በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ አፈፃፀምሙ ተገመግሟል፡፡
በመድረኩ ከሰባቱ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ሥራዋች አኳያ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
አፈፃፀሙም በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ የተጠቀሰ ሲሆን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተሰጡ አቅጣጫዎችን ተከትሎ በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
ወደ ተሟላ ትግብራ መግባት እንዲቻልም ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን በተዋረድ በሚገኙ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መዋቅር የአገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያውን እኩል ማስኬድ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በውይይቱ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሪፎርሙን በተሟላ ሁኔታ መተግበር ሲጀምር በተቋሙ የተቀመጡ ግቦች እጅግ በዘመነ መንገድ ለመተግበር ምቹ መደላድል ከመፍጠር ባሻገር ተቋሙን ትራንስፎርም ማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡

Read More »
News

ኤክስፖው የጀመርነውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል ልምድ ያገኘንበት ነው፡

ኤክስፖው የጀመርነውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል ልምድ ያገኘንበት ነው፡፡
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የቴክኒክና ሙያ ሚኒስትር ዴኤታ
ስድስተኛው የሳውዲ አረቢያ የሰው ሃብት ኤክስፖ በሪያድ እየተካሄደ ነው፡፡
በሪያድ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ኤክስፖ የሀገሪቱ ታላላቅ የሰው ሀይል ቅጥር ኩባንያዎችን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ፣ እስያ እና የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሚመራ የልዑካን ቡድንም በኤክስፖ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
ከኤክስፖው ጎን ለጎን የልዑካን ቡድኑ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ ያደረገ ሲሆን በሪያድና ጂዳ ከሚገኙ አምባሳደሮች እና ቆንጽላዎችና የአጄንሲ ማህበራት በተገኙበት በዘርፉ በሚስተዋሉ ችገሮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄዷል
በዚህም ኤክስፖው ሀገራችን ከቤት ውስጥ ሥራ ባለፈ ሰፊ የሆነ የሰለጠነና በከፊል የስለጠነ የሰው ኃይል ያላት መሆኑን ለማስተዋወቅ እድል የሰጠና የጀመርነውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሻሻል ልምድ የተገኘበት መሆኑን ክቡር ዶ/ር ተሻለ ተናግረዋል፡፡

Read More »
News

የሰልጣኞች ቅበላ መጀመሩን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ

ሰልጣኞች ቅደበላ መጀመሩን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሰልጣኞች ቅበላን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም በአስተዳደሩ 6 የግል እና 2 የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ዘርፎችን የመለየት ሥራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ የዲጂታላይዜሽን ስልጠናዎችን ጨምሮ የአካባቢውን ፀጋ ለመጠቀም የሚስችሉ ስልጠናዎች የሚሰጡ በመሆናቸው አውቅና እና ብቃት ወዳላቸው ኮሌጆች በማምራት የሥልጠና መስክ መምረጥ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በደረጃ 3 እና 4 ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የመቀበል አዝማሚያዎች እንደነበሩ ያመላከቱት ኃላፊዋ በዚህ ዓመት ሁሉም የግል እና የመንግስት ኮሌጆች ደረጃ 1 እና 2 ተቀብለው ምዝገባ እንዲያካሂዱ አሳስበዋል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓት ግንባታ (system thinking) ላይ ተወያዩ፤

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓት ግንባታ (system thinking) ላይ ተወያዩ፤
በሪፎርም አስተሳሰብ ውስጥ የተወለደው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዳዲስ እሳቤዎችንና አሠራሮችን በመቅረፅ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ አዳዲስ አሰራሮች መካከል ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓትን (system thinking) በሚኒስትር መ/ቤቱ ለማስጀመር የሚያስችል የፐብሊክ ሰርቪስ ላብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ነው ፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአስተሳሰብ ሥርዓትን (system thinking) ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተካሄደ ጥናት ለካውንስል አባላቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ወጥ የሆነ እሳቤን ቀርፆ በየደረጃው የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚስችል ሥራ ሲሰራ ቆይቷል።
የዲጂታል አማራጮችን ጭምር በመጠቀም ዘርፉን ተናባቢ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት የተሰጠውን ተልዕኮ በሚመጥን መልኩ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተናባቢ የሆነ ሥርዓትን ለመገንባት እያንዳንዱ አመራር ኃላፊነቱን በትኩረት መወጣት እንደሚኖሩበትም በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
tigTIG
Scroll to Top