Mols.gov.et

News

News

ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ እምቅ አቅም ያለው የቱሪዝም ዘርፍ

ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ እምቅ አቅም ያለው የቱሪዝም ዘርፍ
የቱሪዝም ዘርፍ ያለውን ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ እምቅ አቅም መነሻ በማድረግ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስልጠናዎችን በተቀናጀ መልኩ እየሠጠ እንደሚገኝ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ፡፡
ኢንስቲትዩቱ የሥራ አጥነትን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍና የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስልታዊ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደገለጹት፤ የቱሪዝም ዘርፍ በባህሪው ሰፊ የሰው ኃይል የሚፈልግ በመሆኑ፣ ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው ስልጠናዎች ከገበያው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣሙ እየተደረገ ነው።
በተለይም ወጣቶች በዘርፉ ሰልጥነው ሲወጡ የራሳቸውን ቢዝነስ እንዲጀምሩ የሚያስችል የክህሎትና የሥራ ፈጠራ ስልጠናዎችን በማቀናጀት፣ ዜጎች መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ከመሸፈን ባለፈ ለሌሎችም የሥራ ዕድል የሚፈጥሩበት ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ይታሰብ አክለውም፣ አሁን ላይ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የቱሪዝም ቴክኖሎጂዎችን በስልጠና ክፍሎቹ በማስተዋወቅ ሰልጣኞች በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት መስጠት የሚችሉበትን ብቃት እንዲላበሱ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

Read More »
News

“ከፈጠራ ሐሳብ ወደ ተጨባጭ ተግባር’’

“ከፈጠራ ሐሳብ ወደ ተጨባጭ ተግባር’’
የክህሎት ባንክ የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ችግር ፈቺ ተግባር በማሸጋገር ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም በሆነው በኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው “የክህሎት ባንክ” (Skill Bank)፣ የፈጠራ ስራዎችን በማልማትና ወደ ንግድ ማዕቀፍ (Commercialization) በማሸጋገር ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ በተለይ በክረምት መርሃ-ግብር እና በ“ስኪል ኢትዮጵያ ስታርታፕ” ፕሮግራም የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ለገበያ በማቅረብ ለሀገራዊ ምርታማነት የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ነው፡፡
የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፀዳለ ተክሉ እንደገለጹት፤ ስኪል ባንክ ከመረጃ ቋትነት ባለፈ አዳዲስ የፈጠራ ሐሳቦች ተቀርጸው ወደ ተግባር የሚቀየሩበት ህያው የፈጠራ መድረክ (Innovation Hub) ነው ።
እስካሁንም ከ600 በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ160 በላይ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲፈጠሩ ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ ተኪ ቴክኖሎጂዎች ወደ ተጠቃሚው ማህበረሰብ እየደረሱ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ፀዳለ ገለጻ፣ በማዕከሉ ከለሙና ወደ ንግድ ከተሸጋገሩ ስኬታማ ቴክኖሎጂዎች መካከል በኢንተርኔት የታገዘ ስማርት መስኖ (IoT Smart Irrigation) በአፋርና ሶማሌ ክልሎች በንግድ ደረጃ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፣ አፈር አልባ የሆነው የ”ሃይድሮፖኒክ” የእንስሳት መኖ ማምረቻ ቴክኖሎጂም ከኢንተርፕራይዞች ጋር በተፈጠረ ትስስር ምርቱን በስፋት እያቀረበ ይገኛል።

Read More »
News

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የሪፎርም ትግበራውን ወደ ተግባር አሸጋገረ

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የሪፎርም ትግበራውን ወደ ተግባር አሸጋገረ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቴክኖሎጂና የሥራ ባሕል ዕድገትን የሚመጥን ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችለው የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ወደ ተግባር ምዕራፍ መሸጋገሩ ተገለጠ።
ይህንንም ተከትሎ ቢሮው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ለአመራሮች፣ ለዓብይና ለቴክኒካል ኮሚቴ አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ የሪፎርም ሥራዎችን በአግባቡ መተግበር ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎትን በማቅረብ ረገድ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
ሪፎርሙ በሰው ሀብት ልማት ላይ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑን የጠቀሱት አማካሪው፣ የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ የበቃና ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይል መፍጠር እንደሚገባም አስረድተዋል።

Read More »
News

ከ26 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረው የከተማ ግብርና…

ከ26 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረው የከተማ ግብርና
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 8 ወራት ብቻ በከተማ ግብርና ዘርፍ ከ 26 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን እንደገለጹት፤ 2,088 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም በቅጥር ከ 26 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
በከተማዋ ባለፉት 8 ወራት ከተፈጠረው 287 ሺህ በላይ ቋሚ የሥራ ዕድል ውስጥ የከተማ ግብርና የ 9.3 በመቶ ድርሻን ይዟል።
በከተማዋ የሥራ ዕድል ሊፈጠርባቸው የሚችሉ 44,307 የከተማ ግብርና ጸጋዎች ተለይተው ወደ ሥራ መገባቱን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ብቻ 17,404 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
የከተማ ግብርና ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር የተሻገረ ፋይዳ እንዳለው የጠቆሙ ዳይሬክተሩ ለነዋሪዎች የዕለት ተዕለት የምግብ ፍጆታ የሚውሉ (አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ዶሮና እንቁላል…) የመሳሰሉ ምግቦች በራስ ግቢና አካባቢ በማምረት የኑሮ ውድነትን መቋቋም ያስችላል ብለዋል።

Read More »
News

የዘርፍን ውጤታማነት የማላቅ ግብ ያለው ቴክኒካዊ ድጋፍና ክትትል

የዘርፍን ውጤታማነት የማላቅ ግብ ያለው ቴክኒካዊ ድጋፍና ክትትል
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ የታቀዱ የለውጥ አጀንዳዎችና ስትራቴጂካዊ ግቦች ውጤታማ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የሚከናወን መጠነ-ሰፊ የቴክኒክ ድጋፍና የመስክ ክትትል ሥራ ጀምሯል።
የክትትልና ድጋፍ ሥራውን የሚመሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሐመድ እንደገለጹት፤ ይህ የመስክ ምልከታ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሀገራዊ ተልዕኮውን በስኬታማነት ለማስፈፀም የቀረፃቸውን እሳቤዎችን ተግባራዊነት ለመመዘን የሚያስችል ነው፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በከፍተኛ አመራሮች የተመራ የክትትልና ድጋፍ ቡድን በ10 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ምልከታ ማድረጉን ያስታወሱት ክብርት ነቢሃ የታዩ ክፍተቶችን መሠረት በማድረግ ለክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ለዘርፍ ቢሮ ኃላፊዎች በተሰጠው ግብረ-መልስ መሰረት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ዕቅዳቸውን ከልሰው ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡
ቴክኒካል ባለሙያዎችን ያካተተው የአሁኑ የመስክ ምልከታ ዋና ዓላማ በአመራር ደረጃ በቸካሄደው የድጋፍና ክትትል ሥራ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የገቡትን ቁርጠኝነትና የጀመሩትን የሥራ አፈጻጸም በተጠናከረ መልኩ እንዲፈጽሙ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ይህ የሱፐርቪዥን ቡድን በየክልሎቹ ከሚገኙ አቻ የቴክኒክ ቡድኖች ጋር በቅንጅት በመሥራት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማትና በኢንዱስትሪ ሰላም ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችን በቦታው በመገኘት የሚፈታና የልምድ ልውውጥ የሚያደርግ ይሆናል።
በመሆኑም በየደረጃው የሚመለከታቸው አካላት ለክትትልና ድጋፍ ቡድኑ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ፣ የዘርፉን ሥራዎች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ክብርት ነቢሃ ጥሪ አቅርበዋል።

Read More »
News

የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት አዲስ ተስፋ…

የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት አዲስ ተስፋ ይዞ እንደሚመጣ የሚጠበቀው ስምምነት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጋር በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የትምህርት ዘርፍ ያለውን አቅም ለማጠናከር እና ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችለውን የጋራ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት በትምህርት ላይ ብቻ ሳይወሰን በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ የበለጸጉ የቱሪስት መስህቦችን በተለይም የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የቱሪዝም ሀብቶች በዘላቂነት ለማልማትና ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት በቴክኒክና በዕውቀት ለመደገፍ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች ለስምምነቱ መሳካት ላሳዩት ቁርጠኝነት የዩኒቨርሲቲው አመራር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህ አጋርነት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በዕውቀትና በክህሎት የሚመራ ብቁ የሰው ኃይል ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ስምምነት ተቋማቱ ያላቸውን አቅም በማቀናጀት ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት አዲስ ተስፋ ይዞ እንደሚመጣም ይጠበቃል።

Read More »
News

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሥራ የሚያቆሙ ኢንተርፕራይዞችን …

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሥራ የሚያቆሙ ኢንተርፕራይዞችን ዳግም ወደ ሥራ ለመመለስ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ሥራ የሚያቆሙ ወጣትና ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ኢንተርፕራይዞቹ የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች ተቋቁመው ዳግም ወደ ምርትና አገልግሎት እንዲገቡ በማድረግ፣ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻልና የአካባቢዎችን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት እንደሚያስችል ተመላክቷል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ዓለማየሁ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በቅርቡ የጸደቀውን የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ በኢኮኖሚ ቀውስና በአደጋ ወቅት የኢንተርፕራይዞችን ተጎጂነት ለመቀነስ ፖሊሲው ያስቀመጠውን አቅጣጫ መሠረት በማድረግ ወጣቶችንና ሴቶችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚረዳ ገልጸዋል።
ይህም ሚኒስቴሩ የፖሊሲ ማዕቀፎችን ወደ ተጨባጭ የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ ድጋፍ ለመቀየር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአፍሪካ ልማት ባንክ የሀገር ውስጥ ፕሮግራም ኦፊሰር ፓዋልም ኢልቡዶ በበኩላቸው፤ ባንኩ የአፍሪካን ወጣቶች የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ወደ ኢኮኖሚያዊ ኃይል ለመለወጥ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ይህ ፕሮጀክት ዘላቂ የሥራ ዕድልና ሰላም ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።
የፕሮጀክቱን ዝርዝር አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አሺቅ በድሩ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ ለአራት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ 20 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት ተመድቦለታል። ከዚህም ውስጥ 10 በመቶው በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ይሆናል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት በአማራ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በሶማሌ ክልሎች የሚገኙ ከ3,000 በላይ ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ አቅርቦት፣ በክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠናን ጨምሮ በተለያዩ ድጋፎች ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

Read More »
News

ኢፍጣር፤ የአብሮነት መገለጫ!

ኢፍጣር፤ የአብሮነት መገለጫ!
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጋራ የኢፍጣር መርሃ ግብር በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቅጽርግቢ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጨምሮ የባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ይህ የኢፍጣር መርሃ ግብር በረመዳን ወር የሚታዩትን የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና የመካፈል ታላላቅ መንፈሳዊ እሴቶች መሠረት ያደረገ ነው።
መሰል መርሃ ግብሮች በተቋሙ አመራርናሠራተኞች መካከል ያለውን አብሮነት በማጠናከር በመካከላቸው ያለውን ቤተሰባዊ ቅርርብን በማላቅ ለተቋማዊ ስኬትና ለሥራ ተነሳሽነት መሠረት የሚጥሉ ናቸው፡፡

Read More »
News

ምርትና ምርታማነትን ማጎልበት

ምርትና ምርታማነትን ማጎልበት፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ማመንጨትና ከባቢያዊ ችግሮችን መፍታት የሚጠበቅባቸው የቴክኒክና ሙያ ተቋማት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ከሥልጠና ማዕከልነት ባለፈ የኩባንያዎች መፈልፈያ፣ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፍለቂያና የሥራ ዕድል ፈጣራ ማዕከላት እንዲሆኑ የሚያስችል አዲስ እሳቤን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
የዚህ እሳቤ ዋንኛ ዓላማ የስልጠና ተቋማቱ ያላቸውን ማሽኖችና ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ከባቢያዊ ችግርን የሚፈቱ ምርቶችን እንዲያመርቱ ፣ በሂደቱም በተግባር በተደገፈ መልኩ ሰልጣኞቻቸውን በክህሎት እንዲያበቁ ማስቻል ነው፡፡
በዚህ መሰረት በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ራሱን የቻለ ህጋዊ ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው ወደ ሥራ እየገቡ ይገኛሉ፡፡
የመሰል ኢንተርፕራይዞች መቋቋም ተቋማቱ የውስጣዊ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ፣ ምርትና ምርታማነትን እንዲያጎለብቱና አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በማመንጨት የአካባቢቸውን ችግር እንዲፈቱ የሚያስችል አቅምን እንደሚያላብሳቸው ይጠበቃል፡፡

Read More »
News

የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ሀገር በቀል ክህሎትን

የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ሀገር በቀል ክህሎትን በማጎልበት የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ነው – የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የዜጎችን የዲጂታል ፈጠራና ክህሎት ለማስፋት የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው።
በተለይም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሳይበር ደኅንነት ያሉ አዳዲስ የሥልጠና መርሃ ግብሮች ተቀርጸው ተግባራዊ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።
ለዚህም የክህሎት ማበልጸጊያ ቴክኖሎጂዎችን በማሟላት የግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና መሰል ዘርፎችን ምርታማነት የሚያሻሽል ሀገር በቀል የፈጠራ ክህሎት እንዲጎለብት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት መሳለጥ መሰረት መጣሉንም ዋና ዳይሬክተሩ አውስተዋል።
የ2030ው ስትራቴጂ ደግሞ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ሥርዓቱን የበለጠ በማዘመን ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት ሀገር በቀል የፈጠራ ክህሎትን በማጠናከር ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ምርምር ውጤቶችን እንዲያፈልቁ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም የሰልጣኞችን የቅበላ አቅም በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በዘርፉ የተሰማሩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችም ስትራቴጂውና የተሰጣቸው ስልጠና ለስኬታቸው መነሻ መሆኑን ገልጸዋል። ።ዘገባው የኢዜአ ነው

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
oroORO
Scroll to Top