
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ካውንስል ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት መደበኛ ውይይቱን አካሂዷል፡፡
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ካውንስል ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት መደበኛ ውይይቱን አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ያለፉት ሁለት ወራትን ጨምሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ተመልክተናል፡፡
የ2018 በጀት ዓመት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድንም በዝርዝር ተመልክተን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለይተናል፡፡
እያጠናቀቅን ባለው በጀት ዓመት የሥራ ስምሪቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ የመዳረሻ ሀገራትን በማስፋት እና ከባለድርሻና ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡
በዚህም ከ500 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ45.8 በመቶ እድገት ያለው ቢሆንም ከያዝነው ግብ እና ዘርፉ ካለው እምቅ አቅም አኳያ ብዙ መስራት እንደሚገባን ተመልክተናል፡፡
በመሆኑም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችን የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ላይ አተኩሮ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦቱ የሥራ ገበያው ፍላጎቱን በአግባቡ ለመመለስ፤ የአገልግሎት አሰጣጡም ይህንኑ የሚያሳላጥ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ተዋንያን በተሰናለሰ አግባብ መስራት እንደሚገባን ተግባብተናል፡፡
ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ እየሰጡ ላለው ውጤታማና ጠንካራ አመራር እንዲሁም ሚናችሁን እየተወጣችሁ ላላችሁ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!