Mols.gov.et

ዜና

ዜና

ትውልዱ በቴክኒክና ሙያ. . .

ትውልዱ በቴክኒክና ሙያ ያገኘውን ክህሎት ለእድገት በተግባር መተርጎም ይጠበቅበታል
ትውልዱ በቴክኒክና ሙያ መስክ የሚያገኛቸውን ክህሎቶች በተግባር በመተርጎም ለእድገት የበኩሉን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ።
የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ100ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓል የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት “ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች አከብሯል።
በሥነ-ሥርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮሌጁ መምህራንና ተማሪዎች፣ የቀድሞ ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመድረኩ በኮሌጁ የተሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አውደ-ርዕይ፣ የኪነ-ጥበብ ስራዎችና የባህል አልባሳት ትዕይንት ቀርበዋል።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሚደቅሳ ከበደ በዚሁ ወቅት፤ የከተማ አስተዳደሩ የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ብቁ ሙያተኛ ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሰልጣኞች በቂ ክህሎት እንዲጨብጡ ከኢንዱስትሪዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ከቴክኖሎጂ ዕውቀት ውጪ ልማትና ዕድገት ማረጋገጥ እንደማይታሰብ ጠቁመው፤ በዚህ በኩል ተማሪዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በብቃት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በዓሉን ከማክበር ባለፈ በቴክኒክና ሙያ መስክ የታነፀ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

Read More »
ዜና

የሀገራችን ዕድገት ትልቁ ምሰሶ ሠራተኛው ነው ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ

የሀገራችን ዕድገት ትልቁ ምሰሶ ሠራተኛው ነው
ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
በኢትዮጵያ ለ51ኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ137ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የሠራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ) አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የዘንድሮው በዓል “የሠራተኛው መብት መከበር ለኢንዱስትሪ ሰላምና ለምርታማነት መሠረት ነው!” በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 23 ቀን በድምቀት የሚከበረውን የሜዴይ በዓል አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነትን ለማስፈን በርካታ ሪፎርሞችን ማድረጉን ጠቁመው፣ አሰሪና ሠራተኛ ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አብራርተዋል።
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገራት የሚገኙ ዜጎችን ደህንነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ጠቁመዋል።
መንግስት የሠራተኞችን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የሥራ ላይ ደህንነትን ለመጠበቅና አደጋዎችን ለመከላከል የቁጥጥር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን(የኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው የሠራተኛው መብት መከበር ለሀገር እድገትና ለምርታማነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የዘንድሮውን በዓል ልዩ የሚያደርገው አሰሪ፣ ሠራተኛና መንግስት በጋራና በትብብር የሚያከብሩት መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሞገስ ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የሠራተኛውን መብት የማያከብር አሰሪ ምረታማነቱን ከማሳደግ ይልቅ ጊዜውን በንትርክ ይጨርሳል ብለዋል፡፡
ይህንን ተገንዝበው በአሁኑ ወቅት በርካታ አሰሪዎች ለሠራተኞቻቸው ቅድሚያ በመስጠት አበረታች ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ።
ከወዲሁ እንኳን ለአለም የሰራተኞች ቀን አደረሳችሁ!

Read More »
ዜና

ቢሮው የISO 9001:2015 ትግበራን በይፋ ጀመረ

ቢሮው የISO 9001:2015 ትግበራን በይፋ ጀመረ
የአማራ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጡን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችለውን የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ስቡህ ገበያው እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ ፈርመዋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ዶ/ር መሰረት በቀለ እንደገለጹት፣ የጥራት ማኔጅመንት ሥርዓትን መተግበር ተቋማት የተገልጋይ እርካታን በተጨባጭ እንዲያረጋግጡ ከመርዳቱም በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።
ስምምነቱ ቢሮው ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች አኳያ የሚሰጠውን አገልግሎት ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችለው ተመላክቷል።
ቢሮው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በስሩ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ በጀመረው ጥረት፣ በ2017 በጀት ዓመት 5 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የISO ትግበራን አጠናቅቀው እውቅና ማግኘት ችለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም ተጨማሪ 7 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችን የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ማረጋገጫ ባለቤት ለማድረግ ዝግጅቶች ተጠናቅቀው ወደ ሥራ መገባቱ ቢሮው አስታውቋል።

Read More »
ዜና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንተርፕራይዞችን . . .

በክልሉ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት ውጤት አስገኝተዋል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍና በማብቃት ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስገኘታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
የክልሉ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ “የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው አውደ ርዕይና ባዛር እንዲሁም የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ ኢንተርፕራይዞችን በማብቃት ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት አስገኝተዋል።
ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
በክልሉ ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የክልሉ ስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሙስጠፋ ኢሳ ናቸው።
በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል በሆሳዕና ከተማ የሚገኘው የጡማ ፕላስቲክ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ሰለሞን ታሪኩ እና የእንጨትና የብረታብረት ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ ሰብሳቢ ወጣት ዘርፍነሽ ሽብሩ የደረጃ ሽግግሩ ድርጅቶቻቸው ስራቸውን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲከውኑ ማስቻሉን ጠቁመዋል።
ፋብሪካው ከ120 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገቡንና ከ150 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠሩን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።
ወጣት ዘርፍነሽ በበኩሏ ኢንተርፕራይዙ 10 ሚሊየን ብር ካፒታል ማስመዝገቡን ገልጻ 30 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ብላለች። ዘገባው የኢዜአ ነው።

Read More »
ዜና

ኢንተርፕራይዞች …

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የክልሉን ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ከፈቱ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየውን የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ከፍተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በአዲስ መልክ ለሁለተኛ ጊዜ በሚያካሄደው ኢግዚቢሽንና ባዛር የሞዴል ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግርና ዕውቅና ፕሮግራም እንደሚኖር ቢሮው አስታውቋል ።
በባዛሩ በኢንዱስትሪና በግብርና የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን አጋጣሚው አምራቾችና ሸማቾች በቀጥታ የሚገናኙበት ሰፊ የገበያ ትስስር የሚፈጥር እንደሚሆንም የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ አስታውቀዋል፡፡
በዝግጅቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

Read More »
ዜና

ፕሮጀክቱ በግብርና ዘርፍ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማላቅ የሴቶችና ወጣቶችን

ፕሮጀክቱ በግብርና ዘርፍ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማላቅ የሴቶችና ወጣቶችን ዘላቂ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ተገለጸ
የግብርና ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለሥራ ፈጠራ (AMD4J) ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ የተገመገመ ሲሆን በተለይም የግብርና-ቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ማጠናከር፣ የሥራ ማዕከላት አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን እና የፋይናስ አቅርቦትና ተደራሽነትን ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
በዚህም የወጣቶችንና የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ከመገንባት አኳያ ያለው ሚና የላቀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የግብርና ዘርፉንም ከማዘመን አኳያ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
በተጨማሪም በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሥራ ፈጣሪዎችን የመቋቋም አቅም ማሳደግ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በዚህም የኢንተርፕራይዞችን አደጋ የመቋቋም አቅም ማጎልበት ፕሮጀክት፤ በተለያየ ምክንያት ችግር የሚገጥማቸውን ኢንተርፕራይዞች መልሶ ለማቋቋምና ችግሮችን የመቋቋም ዝግጁነታቸውን በማሻሻል የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ለመደገፍ የሚያስችል እንደሆነ የተመላከተ ሲሆን ስትሪንግ ኮሚቴው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡፡

Read More »
ዜና

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም …

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም ለሥራ ባህል ግንባታ መሠረት እየጣለ መሆኑ ተገለጸ
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትን የኩባንያዎች መፈልፈያ ለማድረግ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቀረፀውን አዲሱን የሪፎርም እሳቤ መነሻ በማድረግ፣ በርካታ ተቋማት ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም የሰልጣኞችን የሥራ ባህልና ክህሎት እያሳደጉ መሆኑ ተመላከተ።
የአማራ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገቢያው(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ እነዚህ ኢንተርፕራይዞች ሰልጣኞች ተግባራዊ ሥልጠናን በተጨባጭ ከማግኘታቸው ባለፈ፣ ጠንካራ የሥራ ባህል እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
ሰልጣኞች በተጨባጭ እያመረቱ የሚማሩ መሆኑ የጊዜ አጠቃቀምን፣ ሥራን በአግባቡ መፈፀምን፣ እንዲሁም ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በተግባር እንዲለማመዱ ዕድል እየፈጠሩላቸው መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።
ዶ/ር ስቡህ አክለውም፣ ይህ አሠራር ሰልጣኞች በሥራ ቦታ የሚፈለገውን የዳበረ ሥነ-ምግባር እንዲያጎለብቱ ከመርዳቱም በላይ፣ በቡድን የመሥራት፣ የመግባባትና የመተባበር ክህሎታቸው እንዲያድግ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። እነዚህ እሴቶች ሰልጣኞች ወደፊት ወደ ሥራው ዓለም ሲሰማሩ በቀላሉ እንዲላመዱና ውጤታማ እንዲሆኑ አስተማማኝ መሠረት ይጥላሉ።
በኮሌጆች ውስጥ የሚቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች የሰልጣኞችን የኢንተርፕርነርሽፕ አስተሳሰብ (Entrepreneurial mindset) በማሳደግ ረገድ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ስቡህ፤ ሰልጣኞች የገቢና ወጪ ቁጥጥርን እንዲሁም የገበያ ትስስርን በተግባር እንዲያውቁ በማድረግ የራሳቸውን ሥራ ለመፍጠር ያላቸውን ተነሳሽነትና በራስ መተማመን እንደሚያሳድጉት ጠቁመዋል። ይህም ጥራትን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ላይ በማተኮር በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ የመሆን አቅምን ይፈጥርላቸዋል ብለዋል።
በአጠቃላይ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም ሰልጣኞችን ከንድፈ-ሀሳብ ባለፈ ለተግባራዊ ዓለም የሚያዘጋጅ ስትራቴጂ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

Read More »
ዜና

የሥራ ማዕከላት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የሚሳለጥባቸው ወሳኝ …

የሥራ ማዕከላት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የሚሳለጥባቸው ወሳኝ ድልድዮች ናቸው፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፤ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጆዜፍ ሲኬላ እና የስዊድን የፍልሰት ሚኒስትር ጆሃን ፎርሴል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ የሥራ ማዕከል ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የሰው ኃይሏን ወደ ውጤታማ ሀብት ለመቀየርና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የቴክኒክና ሙያ ተቋማትንን እንደ ግብርና፣ ማዕድንና ኢንዱስትሪ ካሉ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር አስተሳስራ እየተገበረች ትገኛለች፡፡
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ መሠረት፣ በ2018 በጀት ዓመት (2025/26) ብቻ 5.6 ሚሊዮን አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ሰለሞን፤ የሥራ ማዕከላት ደግሞ ይህንን ግብ ለማሳካት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የሚሳለጥባቸው ወሳኝ ድልድዮች ናቸው ብለዋል።
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በኢትዮጵያና በአውሮፓ ሕብረት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ጠቁመው ለዚህም የሰለጠነ የሰው ኃይልን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ከአለም የሥራ ድርጅት (ILO) እና ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑ ጨምረው ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ላይ የአውሮፓ ሕብረትና የስዊድን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እንዲሁም የILO እና IOM መሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ የልዑካን ቡድኑ በሥራ ማዕከሉ ያለውን አገልግሎትና የዲጂታል አሠራር ተመልክቷል።

Read More »
ዜና

ለወጣቶችና ሴቶች አዲስ የሥራ ዕድል የከፈተው …

ለወጣቶችና ሴቶች አዲስ የሥራ ዕድል የከፈተው የግብርና ኢንተርፕራይዞች ልማት ፕሮጀክት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የግብርና ኢንተርፕራይዞችን ለማዘመንና የእሴት ሰንሰለቱን የተከተለ የሥራ ዕድል ለወጣቶችና ሴቶች ለመፍጠር ያለመ ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከክልል ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በዙም (Zoom) ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ ግብርናውን ከባህላዊ አሰራር በማውጣት ወደ ዘመናዊ የንግድ ሥራ (Agri-Business) ለመቀየር አቅም ሰንቆ የተነሳ ነው።
ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚዘልቅና ዘንድሮ ወደ ትግበራ የገባ መሆኑን ገልጸው አፈጻጸሙን ውጤታማ ለማድረግና የታለመለትን ግብ እንዲመታ ክልሎች ፕሮጀክቱን በልዩ ትኩረት የቅርብ ክትትል በማድረግ እንዲደግፉ አሳስበዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በግብርና ዘርፍ የወጣቶችንና የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ዘላቂ ምህዳር መፍጠሪያ በመሆኑም በባለቤትነት ስሜት አፈጻጸሙን መከታተል እንደሚገባ ጨምረው ገልጸዋል
እያንዳንዱ አካባቢ ያለውን የግብርና ምርት አቅም መለየት ለሥራ ዕድል ፈጠራው ስኬት መሠረት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ይህም በየአካባቢው ያለውን ጸጋ መሠረት ያደረገ እሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
በግብርና ኢንተርፕራይዝ የሚሳተፉ ዜጎች የሳይኮሜትሪክ ፈተና (Psychometric Test) እንዲወስዱ በማድረግ ብቃታቸውን መሰረት ያደረገ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የዘርፉ ተቋማትን የማስጸም አቅም የሚገነባ ሲሆን ለኢንተርፕራይዞች ደግሞ ቴክኒካዊ ስልጠናዎች፤ የንግድ ልማት ምክር አገልግሎት፤ የፋይናንስ አቅርቦት እና የተሳለጠ የገበያ ትስስር ድጋፍ ያደርጋል።

Read More »
ዜና

‹‹የጥራት ዓመት ››ግብን ለማሳካት በኢኒስቲትዩቱ የተካሄዱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች

‹‹የጥራት ዓመት ››ግብን ለማሳካት በኢኒስቲትዩቱ የተካሄዱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጥናት፣ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ረገድ የያዘውን ‹‹የጥራት ዓመት ››ግብ ለማሳካት በታቀደው መሠረት በርካታ ሥራዎች ማከናወኑ ተገለፀ፡፡
የኢኒስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ(ዶ/ር) እንደሚገለጹት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 12 ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች ተጠናቀው ለተጠቃሚ እንዲበቁ ተደርገዋል።
በተጨማሪም ስድስት ጥናቶች በሂደት ላይ እንደሚገኙና ለ24 ተከታታይ ሳምንታት በተካሄደ የምርምር ሴሚናር 61 የጥናት ሥራዎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ጠቁመዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህል ማዕከል ማቋቋሙና በስነ-ጥበብ ሥራዎች የተቋሙን ገጽታ የመገንባት ሥራ ማከናወኑ እንዲሁም የምሩቃንን የቅጥር ሁኔታና የገበያ ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ዘጠኝ የእሴት ሰንሰለት ጥናቶች መጠናቀቃቸውም ተመላክቷል።
የማህበረሰብ አገልግሎትን በተመለከተም ኢንስቲትዩቱ የሙያ ብቃቱን ወደ ህብረተሰቡ በማውረድ ረገድ ተጨባጭ ሥራዎችን አከናውኗል። “አንድ ተጨማሪ ክህሎት ለዜጎች” በሚለው መርሃ-ግብር 368 ሰዎች የሰለጠኑ ሲሆን በሌሎች 11 ተቋማት ደግሞ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች የልል ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።
ከዚህም ባሻገር ተንቀሳቃሽ የንግድ ኪዮስኮችን በመሰራት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ለማዕድ ማጋራት እና ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና አካል ጉዳተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን ሀብታሙ ሙሉጌታ(ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡
መረጃው የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ነው፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
amAM
Scroll to Top