Mols.gov.et

አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!

ግንቦት 14, 2026
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል (Future Fit International) እና ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ካናዳ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም መፈራረሙ ይታወሳል። 👉 ሆኖም ይህንን ተከትሎ፣ አንዳንድ ሕገ-ወጥ አካላት የሚከተሉትን የፈጠራ ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ ይገኛሉ፦ • ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI/Deepfake) በመጠቀም የተፈበረኩና አሳሳች ምስሎችንና በቨዲዮዎችን ማሰራጨት 📽️ • “ምዝገባ ተጀምሯል” የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመልቀቅ ማህበረሰቡን ማደናገር፣ • በግል ስልክ ቁጥሮች ደውሉ በማለት ዜጎችን ለኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ መጋበዝ 📞 እነዚህ ማስታወቂያዎች ሙሉ በሙሉ የማጭበርበር ተግባራት መሆናቸውን እናሳውቃለን። 🚫 ❗ ትኩረት የሚሹ ነጥቦች፦ • በአሁኑ ወቅት ለካናዳ የሥራ ስምሪት ምንም አይነት ይፋዊ ምዝገባ አልተጀመረም፣ • በግል ስልክ ቁጥሮች የሚደረጉ ጥሪዎችም ሆኑ የሚላኩ አጫጭር መልዕክቶች (SMS) ሚኒስቴሩን አይወክሉም! ✅ የምዝገባ ጥሪ የሚደረገው 👉በብሔራዊ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች፤ 👉የሚኒስቴሩን ይፋዊ የማረጋገጫ ምልክት (Blue Badge) ባላቸው ማህበራዊ ትስስር ገጾች ብቻ 🚫 ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች • ለማያውቁት ወይም በግል ስልክ ቁጥር ለሚደረግ ጥሪ ምላሽ አይስጡ፤ • በማንኛውም ሁኔታ የገንዘብ ክፍያ አለመፈጽም፤ • ምንጫቸው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን በማሰራጨት የጥፋቱ ተባባሪ አይሁኑ ✅ ምን ማድረግ ይገባዎታል? ✔️ መረጃዎችን ከሚኒስቴሩ ይፋዊ የመገናኛ ዘዴዎች ብቻ ያረጋግጡ፤ ✔️ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ( 9138 በነፃ የስልክ መስመር ወይም info@mols.gov.et ) እና በአቅራቢያዎ ለሚገኙ የህግ አስከባሪ አካላት ይጠቁሙ። 📢 አስቸኳይ 📍 ዜጎች ከዲጂታል ማጭበርበርና ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን!
amAM
Scroll to Top