Mols.gov.et

የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራውን ከዕቅድ በላይ ማሳካቱን ቢሮው አስታወቀ

ግንቦት 14, 2026
የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራውን ከዕቅድ በላይ ማሳካቱን ቢሮው አስታወቀ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከባለድርሻና አስፈፃሚ አካላት ጋር ገምግሟል። በዚህም ለ320,000 በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስታውቋል። ይህም ከዕቅዱ አኳያ 111 በመቶ እንደሆነ ነው የተገለፀው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ትልቁ ሪፎርም መዋቅር መቀየር ሳይሆን በአመራሩና በአስተግባሪው ዘንድ የሚፈጠር የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ብለዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራ ወቅት የሥራ ማማረጥ ችግር እንደ ዋነኛ ተግዳሮት የታየ መሆኑን አመላክተው ቢሮው ለወላጆችና ለሥራ ፈላጊዎች የአመለካከት ቀረጻ ንቅናቄ መደረጉ ትርግም ያለው ውጤት ማምጣቱን አመላክተዋል። ባለፉት 10 ወራት በቢሮው ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው የ2.2 ቢሊዮን ብር የብድር አቅርቦትና የሥራ ቦታዎች ማመቻቸት መቻሉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
amAM
Scroll to Top