Mols.gov.et

News

News

የላቀ ስኬት ለዜጎች ተጠቃሚነት…

የላቀ ስኬት ለዜጎች ተጠቃሚነት….
የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የዜጎችን ድህንነትና ጥቅም በማስጠብቅ ህጋዊ የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ህጋዊ የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት ለዜጎች የተሻለ አማራጭ እንዲሆን የሚያስችሉ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆን ዜጎች ያለምንም እንግልት እንዲሁም ከፓስፖርት እና ከጤና ምርመራ ክፍያዎች ውጪ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ወደ ውጭ ሄደው ደህንነታቸው፣ መብታቸው እና ጥቅማቸው ተከብሮ መስራት የሚችሉበት ፈጣን አገልግሎት የሚያገኙበት በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል።
በመሆኑም በዘርፉ በማኑዋል አሰራር ይሰጥ ከነበረው አገልግሎት በወር ከ5.6 እጥፍ በላይ የዘረፉን አፈጻጸም ማሰደግ ተችሏል። ባለፈው በጀት ዓመት የነበረውን 127,000 ወደ ውጭ ሃገር የማሰማራት ከፍተኛ አፈጻጸም በያዘነው በጀት ዓመት ከ 144,000 በላይ ዜጎችን በ5 ወራት በማሰማራት በዘርፉ ሃገራችን ያላትን የሰራተኛ ስምሪት ታሪካዊ ቁጥር ከፍተኛውን ቁጥር ማሳካት ተችሏል። በዚህም በመካከለኛው ምስራቅ ከ14 ሃገራት በላይ ዜጎችን ለሥራ ከሚልኩ ሃገራት በ2ተኛ ደረጃ ላይ እንድንገኝ አድርጎናል፡፡
ከባለድርሻ አካላት ጋር በተፈጠረ ጠንካራ ቅንጅት፣ በሚንስቴር መስሪያቤቱ በተዘረጋው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአሰራር ስርዓት እንዲሁም በሚደረግ ክትትልና ድጋፍ በውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት በየወሩ እያደገ የሚገኝ አፈጻጸም እየተመዘገበ ይገኛል።

Read More Âť
News

ሁለተኛ ዙር Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB)…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሁለተኛ ዙር (Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB)) ውይይት ተካሄደ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ካውንስል አባላት በየወሩ ማለዳ 1፡00 ሰዓት ተገናኝተው ተቋማዊና አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ አፍላቂ ምክክር የሚያደርጉበት Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB) ሁለተኛ ዙር ውይይት ተካሄደ፡፡
በዕለቱ የኢንተርፕሪነርሺፕና የኢኖቬሽን ምህዳርን በማስፋት ረገድ መንግስትና የግሉ ዘርፍ ያላቸው ሚና እና በዚህ ረገድ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚያስችሉ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

Read More Âť
News

ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተወጣጡ…

ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸው በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ እና ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘውን የብየዳ ልህቀት ማዕከል እና በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችንና የሥራ እንቅስቃሴችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የሚዲያ ኃላፊዎቹም በጉብኝታቸው እና በተመለከቷቸው ሥራዎች መደሰታቸውንና በቀጣይ በጉዳዩ ላይ የባህሊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራዎችን እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

Read More Âť
News

“የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በኢንተርፕሪነርሺፕ …

“የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በኢንተርፕሪነርሺፕ እሳቤ የተቃኙ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየሠራን ነው።”
ክቡር ዶ/ር ተሸለ በሬቻ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን (Business Incubation Center) በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በማስፋፋት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በኢንተርፕሪነርሺፕ እሳቤ የተቃኙ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ችግርን ወደ ዕድል የመቀየርና አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው ሃሳቦችን የማፍለቅ አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ተግባራት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በማሰልጠኛ በተቋማት ውስጥ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን ማቋቋም አንደ አንድ ስልት የተወሰደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የኢንተርፕሪነርሺፕ ሥነ- ምህዳር በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ለማስፋት፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዕውን እንዲሆን ለማስቻል፣ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛና በቢዝነስ ተቋማት መካከል ትስስር ለመፍጠር እና ለምሩቃን ምቹ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላቱን መደገፍና ማሳደግ ወሳኝ ተግባር መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡
በቀጣይም ውጤታማ የሆኑ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በመላ አገሪቱ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለማስፋፋት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንጆይ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በማቋቋምና ውጤታማ በማድረግ አንፃር የተገኙ የተለያዩ ተሞክሮዎችና ማዕከላቱን በቀጣይ መስፋትና ማሳደግ የሚያስችሉ ገለፃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Read More Âť
News

የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ጥምረት… ለላቀ ስኬት !

የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ጥምረት… ለላቀ ስኬት !
የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት የዜጎቻችንን መብት፣ ደህንነትና ጥቅም በማስጠበቅ የሃገራችንን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የተጀመሩ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የወሩን አፈጻጸም ገምግመናል።
በዘርፉ የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጥን ሃገራችን በሰራተኛ ስምሪት ባለፉት አምስት ወራት ከ144,825 በላይ ዜጎችን ለስራ ወደ ውጪ ማሰማራት መቻሉ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑን እንዲሁም ለበርካታ ዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል አቅም መገንባቱን ተመልክተናል። በዚህም የተጀመሩ ስራዎች በጥሩ ደረጃ ላይ መሆናቸውን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የተጀመረውን ጠንካራ የቅንጅት ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ክቡር አምባሳደር ግርማ ለሥራው ውጤታማነት እያደረጉት ላሉት የቅርብ ክትትል እንዲሁም ርብርብ እያደረጉ ላሉ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

Read More Âť
News

ስምምነቱ ኢትዮጵያ በጋራ መልማትን …

” ስምምነቱ ኢትዮጵያ በጋራ መልማትን ያስቀደመች ሀገር መሆኗን ያረጋገጠ ነው”
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ምክንያት በማድረግ ደስታቸውን የገለጹበት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት የህዝብ ቁጥራችን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢኮኖሚያችንም ግዙፍ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ወደ መሆን እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡
ይህ በመሆኑም የቀይ ባህርንና የወደብ አስፈላጊነት አጀንዳ የህልውና ጉዳይ ሆኗል፡፡ መንግስት ለጉዳዩ ሌሎች እንደሚሉት በሀይል ሳይሆን ጥበብ በተሞላበት ዲፕሎማሲ እልባት ለመስጠት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ያደረጉት ስምምነት ለዘመናት ወደብ አልባ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለቀጣዩ ትውልድ ትርጉም ያለው የታሪክ እጥፋቶች መካከል አንዱ እንደሆነም ነው የጠቆሙት፡፡
በተገኘው ፍጹም ሰላማዊ እና የዲፕሎማሲያዊ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ክብርት ሚኒስትር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰጡት ጥበብ የተሞላበትና ቁርጠኛ አመራር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አሁን ላይ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ቢሆንም መነሻው ድህነት እንሆነ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከድህነት ጋር ያለንን ዝምድና ለማቆም ከመቼው ጊዜ በላይ መትጋት፣ መደማመጥ እና መከባበር የሚጠበቅብን ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ ለዚህም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

Read More Âť
News

የአብሮነት ሳምንት..

የአብሮነት ሳምንት (ከታህሳስ 20 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም)
በዓለም ለ26ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአብሮነት ቀን “ብዝሃነትን መኖር” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል፡፡
ለአምስት ተከታተይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግብር በህብረተሰቡ መካከል የመከባባር፣ መቻቻል፣ አብሮነት እና የሠላም ግንባታ አስተሳሰብ እንዲጎለብት የሚያስችሉ ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን በዓሉ አገራዊ አንድነትንና አብሮነትን በሚያጎላ መልኩ እንደሚከበር ተጠቁሟል።

Read More Âť
News

ፕሮግራሙ ለበርካታ ማህበራዊና…

“ፕሮግራሙ ለበርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶችን ህይወት ከመታደግ አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ አለው።”
ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
ወጣቶች በተመረጡ ተቋማት የሥራ ላይ ልምምድ አድርገው ወደ ቅጥር ሥራ እንዲሰማሩ ለማስቻል በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው ‹‹ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ የሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ‹‹ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› ለበርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶችን ህይወት ከመታደግ አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡
ሴቶች ለድህነት ያላቸውን ተጋላጭነት ከግምት በማስገባት 60 በመቶ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ልጅ ያላቸው 27 በመቶ እናቶችም ተገቢውን ትኩረት አግኝተውና ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥሮላቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል የፕሮግራሙ ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በአገራችን በሚገኙና ለሥራ አጥነት ተጋላጭ በሆኑ አስራ አንድ ከተሞች ላይ በዓለም ባንክ ትብብር እየተተገበረ የሚገኘው ይህ ፕሮግራም እድሜያቸው ከ18 እስከ 25 የሚሆን ወጣቶች ስለ ሥራ ያላቸውን አመለካከት ለማነፅ የሚያስችል ሥልጠና ሰጥቶ ለቅጥር ሥራ ከማዘጋጀት፣ በመንግሥትና በግል ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ከማሳደግ እና ሥራ ላይ ልምምድ ስረርዓት በኢትዮጵያ ባህል እንዲሆን ከማስቻል አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው ክቡር አቶ ንጉሡ አብራርተዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር የፕሮግራሙ አፈፃፀም ለተጠቃሚነት ተመዝግበውና ሥልጠና ወስደው በሥራ ላይ ልምምድ ከቆዩ ወጣቶች መካከል 82 በመቶ የሚሆኑት ቋሚ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው በመድረኩ ተገጿል፡፡
በሁለተኛው ዙር የፕሮግራሙ ትግበራ ለሥልጠና ጥራት ትኩረት መስጠት፣ ፕሮግራሙ በተቀመጠለት ስታንዳርድ መሰረት መተግበሩን እና የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው መከታተል ከሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቅ ኃላፈነት መሆኑን ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በአፅንኦት አንስተዋል፡፡

Read More Âť
News

የተቀናጀና ስልታዊ ተግባቦት፤ ለግቦቻችን ስኬት…

የተቀናጀና ስልታዊ ተግባቦት፤ ለግቦቻችን ስኬት….
እንደ ዘርፍ ለለየናቸው ግቦች ስኬት የተቀናጀና ስልታዊ የተግባቦት ሥራዎችን ማከናወን በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ከኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እና የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡
በውይይታችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተሰጠው ተልዕኮ አኳያ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም አሠሪና ሠራተኞች ግንኙነት እና ከተቋም ግንባታ አንፃር የለየናቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች እና እንዲያሳኩ የታሰቡትን ግቦችን ተመልክተናል፡፡
በየደረጃው ጠንካራ፣ የተቀናጀና ስልታዊ የተግባቦት ሥራ መስራት ለግቦቹ ስኬት ወሳኝ እንደሆነም የተግባባን ሲሆን በቀጣይም ዝርዝር የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት ለይተን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በምናደርግበት ሁኔታ ላይ መክረናል፡፡
የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እና የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ ለሰጣችሁን ጊዜ እና እሴት አካይ ግብዓት እንዲሁም ለሥራው ስኬት ላሳያችሁን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!

Read More Âť
News

አማካሪ ቦርዱ አካታችነትን በተግባር …

”አማካሪ ቦርዱ አካታችነትን በተግባር ያስመሰከረና አካል ጉዳተኝነት የተሻለ መሪ ከመሆን እንደማያግድ በተግባር ያሳየ ነው::“
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የወጣቶች አማካሪ ቦርድ አባላት ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡
ክብርት ሚኒስትር ከወጣት አመካሪ ቦርዱ አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተነሱላቸውን ጥያቄዎች ያብራሩ ሲሆን የሕይወት ተሞክሮሯቸውንም አካፍለዋቸዋል፡፡
የወጣት አማካሪ ቦርዱ አባላት አካታችነትን በተግባር ያስመሰከረና አካል ጉዳተኛነት የተሻለ መሪ ከመሆን እንደማያግድ ያሳየ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ወጣቶቹ በትውልዶች መካከል እውቀትን የማመጋገብን ጠቀሜታ ተረድተው ከልምዶቻችን ለመማር ያነሷቸው ጥያቄዎች ብልህነታቸውና ብስለታቸውንም ጭምር የሚያሳይ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills