Mols.gov.et

ሚኒስቴሩ የጋራ ዕቅድ አፈፃፀሙን ከልማት ባንክ ጋር ገመገመ

April 24, 2024
ሚኒስቴሩ የጋራ ዕቅድ አፈፃፀሙን ከልማት ባንክ ጋር ገመገመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል፡፡ ስምምነቱን መሰረት በማድረግም በክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ፈጠራ ዙሪያ የጋራ ዕድቅድ ታቅዶ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በተገኙበት የዕቅድ አፈፃፀሙ ተገምግሟል፡፡ በዚህም ተቋማዊ ቅንጅት ለዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ያለውን ፋይዳ በመረዳት እና የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችን ስኬት ለማላቅ ባለመው የጋራ ዕቅድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘቱ የተገመገመ ሲሆን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም ላይም ውይይት አድረዋል፡፡
Scroll to Top