Mols.gov.et

News

News

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ዋና ዓላማ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ተቋማትን መፍጠር ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ዋና ዓላማ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ተቋማትን መፍጠር ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ተግባራዊ የሚያደርጉት የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ አፈፃፀምን አስመልክቶ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ከተቋማቱ የካውንስል አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሪፎርም ትግበራውን አስመልቶ በየዘርፉ ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ መልዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት፣ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ዋና ዓላማ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ተቋማትን መፍጠር ነው፡፡
ይህን በአግባቡ በመረዳት በየደረጃው የሚገኝ አመራር በቁርጠኝነት መፈፀምና ማስፈፀም ይኖርበታል ብለዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎችን በአይሶ ስታንዳርድ እና ፐብሊክ አንተርፕረነርሺፕ የመሳሰሉ የሪፎርም መሳሪዎች ትግባራዊ እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ይህም ለሪፎርሙ ትግበራ ምቹ መደላድል ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡
በቀጣይ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በየደረጃው ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በዝርዝር ውይይት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Read More Âť
News

ለሀገር አቀፍ የግብርና ናሙና ቆጠራ በቴክኖሎጂ ታግዞ የተደረገው የሰው ሃይል ምልመላ ሂደት ውጤታማ እንደነበር ተገለፀ፡፡

ለሀገር አቀፍ የግብርና ናሙና ቆጠራ በቴክኖሎጂ ታግዞ የተደረገው የሰው ሃይል ምልመላ ሂደት ውጤታማ እንደነበር ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ለሚያካሂደው የግብርና ናሙና ቆጠራ የሰው ሃይል ምልመላ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ለማከናወን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱ ይታወሳል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር በከር ሻሌን (ዶ/ር) ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የምልመላ ሂደቱ ተገምግሟል፡፡
በመድረኩ 43,500 የመስክ መረጃ ሰብሳቢዎችን ለመቅጠር በወጣው ማስታወቂያ መሰረት በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ለሥራው ማመልከታቸው ተመላክቷል፡፡
በዚህም በሁሉም ክልሎች ባሉ ቀበሌዎች ደረጃ ታሳቢ ባደረገ የምዝገባ ስርዓት መስፈርቱን የሚያሟሉ 73 ሺህ የሚሆኑ ዕጩዎች አጭር የጽሁፍ መልዕክት ተልኮላቸው ፈተናውን በኦን ላይን በተሳካ ሁኔታ እንዲወስዱ እየተደረገ ነው፡፡
ይህም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ለውጭ ሀገር ብቻ ሳይሆን ለሀገር ውስጥ ሥራ ስምሪቱ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የማይተካ መሆኑንም ማረጋገጥ እንደተቻለም ነው የተገለፀው፡፡
በተሰራው የቅንጅት ሥራ ለለማው ስርዓት እና በቅንጅት ሥራዎች ላይ በርካታ ልምዶች የተገኙበት እንዲሁም በዲጂታል ስርዓት ከአድሎ የፀዳ፣ ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረውን ሀገራዊ ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ ፈተናውን ላለፉ እጪዎች አጭር የጽሁፍ መልዕክት በእጅ ስልካቸው እንደሚላክና ያንን መሰረት በማድረግ በየደረጃው ያሉ የሥራና ክህሎት መዋቅር የሥራ ውል ቅጽ የማስሞላት ሥራ ይከናወናል ተብሏል፡፡

Read More Âť
News

የሰለጠና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪት ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተጠቆመ

የሰለጠና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪት ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተጠቆመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ሙክታር ከድር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ በዘርፉ የተረደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ሥምሪት ለማድረግ የተደረገው ጥረት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደነበር ተመላክቷል፡፡
በሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ከፍተኛ የሰው ሃይል ፍላጎት እንዳለና በዚህም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለመውሰድ በሚያስችል መልኩ በቅንጅት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
በሳውዲ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አኳያ የሰለጠና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪት ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

Read More Âť
News

መድረኩ በተቋሙ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ዕይታ ይበልጥ ማጎልበት የሚያስችል ነው፡፡

መድረኩ በተቋሙ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ዕይታ ይበልጥ ማጎልበት የሚያስችል ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በየወሩ ጠዋት ከ1፡00 እስከ 3፡00 በአዳዲስ አሰራሮች(innovation) ላይ አተኩሮ የሚያካሄደው መድረክ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ በSystem Thinking እና የሥልጠና እና የገበያ ፍላጎት አለመጣጣም ላይ ያተኮረ መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተናጠል ሩጫ እና አስተሳሰብን አስወግዶ ቅንጅታዊ እና አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደረገ ተቋም መሆኑን ገልጸው በየወሩ የሚካሄደው የማለዳ ውይይትም ይህን ያዳብረዋል ብለዋል፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች በተለመደው መንገድ በመሄድ አይፈታም ያሉት ክብርት ሚኒስትር ያደሩ ተግባራት፣ የአሁንና የቀጣይ ፍላጎቶችን ያስተሳሰረ ችግር ፈቺ ዕይታና አካሄድ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል፡፡
ነባሩን የአስተሳሰብ፣ የባህል እና የሲስተም ችግር በአንድ ጀንበር የሚፈታ ባይሆንም ስራው እያደገ መሄዱን ማረጋገጥና ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የአመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማቱ አመራርና ሠራተኞች የሚያደርጉት ወርሃዊ የማለዳ ውይይት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና ሰላማዊ ኢንዱሰትሪ ግንኙነት ላይ የሚስተዋሉ ሀገራዊ ችግሮችን ፈጠራ በታከለበት አግባብ ለመፍታት ያለመ ነው።

Read More Âť
News

የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥ በሚያመጣ እና በተቀናጀ መልኩ መካሄድ እንዳለበት ተጠቆመ

የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥ በሚያመጣ እና በተቀናጀ መልኩ መካሄድ እንዳለበት ተጠቆመ
የሥራና ክህሎት የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሥራዎች ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
በመድረኩ የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሥራ የደረሰበት ደረጃ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በዚህም ሥራው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
ማሻሻያው የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥ በሚያመጣ እና በተቀናጀ መልኩ መካሄድ እንዳለበት የተጠቆመ ሲሆን የተጀመሩ ሥራዎችን ጥራት ባለው መልኩ በማስቀጠል ሁሉም ሠራተኛ በማሻሻው ላይ በቂ ግንዛቤ ገንዛቤ እንዲኖረውና ግብዓት እንዲሰጥበት እንደሚደረግም ነው የተገለፀው፡፡

Read More Âť
News

የሥራ ስምሪቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል።

የሥራ ስምሪቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል።
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከሳውዲ አረቢያ መንግስት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
ልዑኩ በታካሞል ሆልዲንግ የሙሳነድ ፖርትፎሊዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካሊድ አልቱኪ የተመራ ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፤ በዘርፉ የተደረገው ሪፎርም መነሻና መዳረሻው የዜጎችንን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡
በመሆኑም በሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ዜጎች በቂ ስልጠና እንዲወስዱና ብቃታቸውን በምዘና እንዲያረጋግጡ እየተደረገ ነው።
አገልግሎቱ ፍትሃዊና ቀልጣፋ እንዲሆን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ሰርዓቱን ለማዘመን እና ህገወጥነትን ለመከላከል የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው እስከ አሁን ባለው ኢትዮጵያ በፍጥነትና በተሻለ የጥራት ደረጃ የሰው ሀይል በማሰማራት ቀዳሚ መሆኗን ገልፀው ባዩት የሪፎርም ሥራ እጅግ መደነቃቸውንና መደሰታቸውን ገልፀዋል።
በዘርፉ ተግባራዊ የተደረገው ሪፎርም ውጤታማ እንደሆነ የጠቆሙት የልዑካን ቡድኑ በዘርፉ ባለው የሁለቱ ሀገራት ትብብርም ደስተኛ እንደሆኑና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

Read More Âť
News

ከሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሠራለን፡፡

ከሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሠራለን፡፡
ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ
የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ከሳውዲ አረቢያ መንግስት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ላይ በርካታ ዜጎችን ለማሰማራት የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በቀጣይም አሰራሩን ለማሻሻልና ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራ አመላክተዋል፡፡
የልዑካን ቡድን አባላቱ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሚሰማሩ ዜጎች የጤና ምርመራ ከሚያደርጉ ተቋማትና የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ጋር በሂደቱ የሚታዩ ችግሮችን ለማፍታት የሚያስችሉ ውይይቶችንም አካሄደዋል፡፡

Read More Âť
News

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ልዑካን ቡድን አባላት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላትን ጎበኙ

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ልዑካን ቡድን አባላት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላትን ጎበኙ
በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የተመረጡ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ወደ ውጭ አገር ለሥራ የሚሰማሩ ዜጎች አስፈላጊውን ክህሎት እንዲላበሱ የሚያስችሉ ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ ማዕከላት መካከል አንዱ የሆነው የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሳውዲ አረቢያ የሥራና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የልዕካን ቡድን አባላት ተጎብኝቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ ለሰጠው ትኩረት የተሰማቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን በሥፋት ለሥራ የሚሰማሩባት ዋንኛዋ የመዳረሻ አገር እንደመሆኗ ብቁ ሠራተኞችን ለማፍራት የሚሰጠውን ሥልጠና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተቀራርበው እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲያከናውናቸው የነበሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ …

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲያከናውናቸው የነበሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የልማት ስራዎች በማጠናቀቅ አስረከበ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ልማት ሥራዎች ሲያከናውናቸው የነበሩ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ እና ማስፋፍያ ሥራ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ግንባታ ስራ በማጠናቀቅ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በተገኙበት በዛሬ ዕለት ርክክብ ተደርጓል።
በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እንደገለጹት፤ በፌዴራል ደረጃ አሁን የተጀመረው የመተጋገዝ ባህል ተጠናክክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸው ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
ከለውጡ በኋላ በክልሉ በርካታ ውጤታማ የልማት ስራዎች መከናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ድጋፋም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው የትምህርት ቤት ማስፋፊያ እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በማከናወን ርክክብ መደረጉን ገልጸው ድጋፋ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ሁለት ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል።
የተደረገው ድጋፍም የርስበርስ የመተሳሰብና የመደጋገፍ ባህላችን የሚያጎለብት ከመሆኑ ባሻገር በተለይ የተገነቡት ቤቶች በአነስተኛ ዋጋ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሰሩ በመሆኑ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው አስተዋጽዎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቴክኖሎጂው ቤት በአነስተኛ ወጪ እና ባጠረ ጊዜ ማጠናቀቅ የሚያስችል በመሆኑ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ያስችላል ብለዋል።

በአሁን ወቅት በክልሉ በዚህ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰልጥነው የተደራጁ አራት ኢንተርኘራይዞች እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የ2016 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የ2016 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በባቢሌ ከተማ አስተዳደር “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሎ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
somSOM
Scroll to Top