Mols.gov.et

mols mols

News

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የለውጥ ሥራው ላይ ውይይት ማድረግ ጀምረዋል፡፡
በመድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራዎች የተግባር ምዕራፍ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በስኬት ማጠናቁን አውስተው ይህን ስኬት ያለሠራተኛው ንቁ ተሳትፎና ርብርብ ማምጣት አይቻልም ነበር ብለዋል፡፡
ሥራው ሀገርን የመገንባት ጉዞ አንዱ አካል በመሆኑ ለብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይዞ መውጣት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ሁሉም ይህን ተገንዝቦ የትግበራ ምዕራፉን እቅድ በማዳበር በባለቤትነት አልቆ ለመፈፀም መዘጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የውይይት መድረክ በመደበኛውና የሪፎርም ሥራዎች የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ነገም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Read More »
News

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ…

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ሀገር የመሥራት ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ የሚያግዝ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆው የአፈፃፀም ግምገማ፣ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ምዕራፍ እቅድ ትውውቅ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መድረክ አመራርና ሠራተኛው ለቀጣይ ሥራዎች ያላቸውን የላቀ ቁርጠኝነት ያሳዩበት ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫና ቃለ መሐላ በመፈፀም ተጠናቋል፡፡
በማጠቃለያ ላይ የቀጣይ ሥራዎች መመሪያ የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የራሱን አዳዲስ እሳቤዎች ቀርፆ በለውጥ አስተሳሰብ መቋቋሙ የመንግስት አስተዳደር ሪፎርምን በተገቢው ደረጃ ለመተግበር መሰረት መጣሉን አስረድተዋል፡፡
አዳዲስ እሳቤዎቹ በክህሎት ልማት ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር የሪፎርሙ ትግበራው ሀገር የመሥራት ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረትም ሚኒስቴር መ/ቤቱን የጥራት አመራር (ISO 9001 : 2015) ሰርተፍኬት ባለቤት ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡
የዜጎችን ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰፋፊ ሥራዎች የሚጠብቁ እንደመሆኑ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም መደበኛ ሥራዎችን በተቀላጠፈና በተፋጠነ መንገድ በማሳካት የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
በሪፎርሙ ሂደት ራሳችንን ለማስተማር የነበረን ዝግጁነት የዝግጅት ምዕራፉን በስኬት ለማጠናቀቅ አስችሎናል ያሉት ክብርት ሚኒስትር የተግባር ምዕራፍ ሥራዎች ግልፅነትንና ባለቤትንትን በሚያጎለብት መልኩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች እንደሚተገበሩ አብራርተዋል፡፡
የሪፎርም ትግበራው ሠራተኞች በሠሩት ልክ ዕውቅና የሚያገኙበት፣ የማትጊያ ሥርዓት የሚተገበርበትና፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች የበለጠ ተጠናክረው የሚቀጥሉበት መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስረድተዋል፡፡
ሪፎረሙን በውጤታማነት መተግበር እንዲቻል ለሠራተኞች የተሰጡ የቅድመ ምዘና ውጤቶችን መሰረት ያደረጉ ሥልጠናዎች በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚሰጡና ጠንካራ የሜንቶርሺፕ ስርዓት እንደሚተገበርም ተገልጿል፡፡
የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ትግበራውን በውጤታማነት ማስቀጠል፣ ችግር ፈቺና መፍትሔ አመንጪ ሃሳቦችን በማፍለቅ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት ለመተግበር በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተቋቋመውን (public service innovation lab) የማጠናከር ሥራ በትኩረት እንደሚሠራም አሳውቀዋል፡፡

Read More »
News

ብሩህ ሀገር አገፍ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር መካሄድ ጀመረ

ብሩህ ሀገር አገፍ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር መካሄድ ጀመረ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከኤስ ኤን ቪ ሊዌ ፕሮግራም ጋር በትብብር ያዘጋጀው 6ኛው ሀገር አቀፍ ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የቡት ካምፕ ስልጠናና ውድድር መድረኩ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር ከአካባቢያቸው አልፈው ሀገርን የመቀየር አቅም ያላቸው፣ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ትላልቅ ሃሳቦች የሚለዩበት እና አሸናፊ የሆኑ ሀሳቦች በተደራጀ መንገድ ወደ ካምፓኒ እንዲሸጋገሩ አቅማቸው የሚገነባበት ነው ብለዋል፡፡
ባለፉት 5 ዓመታት በተካሄዱ የፈጠራ ሃሳብ ውድድሮች ከ12 ሺህ በላይ አዳዲስ ሃሳቦች በፌዴራል ደረጃ ቀርበው ችግር ፈቺና መፍትሄ አምጪ ሆነው የተገኙ 1ሺህ 350 የሚሆኑ የፈጠራ ሃሰቦች ለሽልማት መብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡
በማወዳደር እና በመሸለም የማይቆመው ብሩህ-ኢትዮጵያ፤ በውድድሩ ከተሸለሙት መካከል 580 የሚሆኑ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው በአሁን ወቅት ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር እንደቻሉም አስታውቀዋል፡፡
በዘንድርሮ ብሩህ- ኢትዮጵያ 2018 ከመላው የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ 251 የሚሆኑ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች እንደሚሳተፉ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዘርፉ ባለሙያዎች ተገምግመው የሚያሸንፉ የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ካምፓኒ እንዲሸጋገሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ለቀጣይ 10 ቀናት በሚቆየው በዚህ የቡት ካምፕ ስልጠናና ውድድር የሚሳተፉ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች ሃሰባቸውን ይበልጥ ማበልጸግ የሚያስችላቸው ስልጠና፣ የልምድ ልውውጥ እና የኢንዱስትሪ ጉብኝቶችም የተካተቱበት መሆኑን ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

የሀገር ብልጽግናን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ለመደገፍና ኮትኩቶ ወደ ውጤት ለመቀየር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

የሀገር ብልጽግናን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ለመደገፍና ኮትኩቶ ወደ ውጤት ለመቀየር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች መደገፍና ወደ ውጤት መቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከፋይናንስ ተቋማት እና ከልማት አጋሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ሀገር ወደ ብልጽግና የሚያሻግሩ ትላልቅ ካምፓኒዎች ለመፍጠር መሰረት የሚጥሉ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን ለመደገፍ እና ወደ ውጤት ለመቀየር በተናጠል ከመሄድ ይልቅ ተቀናጅቶ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ብሩህ ኢትዮጵያ- የፈጠራ ሃሳቦች በሚል ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው አወዳድሮ በመለየት ወደ ፌዴራል የሚያልፉ ሀሳቦች ላይቶ የማሰልጠን፣ የመሸለም እና የማብቃት ስራ ሲሰራ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር እየፈለቁ የሚገኙ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች በርካታ ከመሆናቸው የተነሳ ሃሳቦች በሚፈለገው ልክ ደግፎ እና ኮትኩቶ ለሀገር እድገትና ብልጽግና ለመጠቀም የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ሥራውን በማገዝ ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደገባ ጠቁመዋል፡፡
ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ5 መቶ በላይ የፈጠራ ሃሳቦች መለየታቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ከነዚህ መካከል 251 የሚሆኑ የፈጠራ ሀሳቦች ከህዳር 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ አቅማቸው የሚገነባበት ቡትካምፕ ይገባሉ ብለዋል፡፡
በዘንድሮ ብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳቦች ውድድር ላይ ተወዳድረው ከሚያልፉት መካከል የተወሰኑት ሀሳባቸውን ወደ ውጤት እንዲቀይሩ በኤስ ኤን ቪ ሊዌ ፕሮግራም(SNV, LIway program) ለመደገፍ መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡
የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች ቀሪ የፈጠራ ሀሳቦች ወደ ውጤት እንዲቀየሩ በመደገፍ ሀገራዊ ሃላፊነታቸው እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

በታዳሽ ኃይል ዙሪያ የሥልጠና ፕሮግራሞችን መክፈትና አዋጪነት

በታዳሽ ኃይል ዙሪያ የሥልጠና ፕሮግራሞችን መክፈትና አዋጪነት
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የታዳሽ ሃይል ቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚያስችል የሥልጠና ፕሮግራም ለመክፈት የእሴት ሰንሰለት ትንተናን መሰረት አድርጎ በተሠራ የዳሰሳ ጥናት ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
በጥናቱም ታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ የሚገኝባቸው አምስት ተፈጥሯዊ ሃብቶችን በተመለከተ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ወንዞቿን በመጠቀም 45ሺ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከ5-6 ኪሎዋት ፐር ሀወር ስኩዌር ሜትር የፀሀይ ሃይል፣ 10ሺ ሜጋ ዋት የንፋስ ሀይል፣ 10ሺ ከጂኦተርማል እና ከ2.8-8.8 ሚሊዮን ቶን በአመት ቆሻሻን ወደ ሀይል በመቀየር ማምረት የምትችል ቢሆንም እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው እጅግ ውሱን መሆኑ ተነስቷል፡፡
በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖር፣ የመሰረተ ልማት እጥረት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ታዳሽ ኃይልን በበቂ መጠን ጥቅም ላይ ላለመዋሉ ዋንኛ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች ‹‹የአለም አቀፍ የነዳጅ ገበያዎች ላይ ጥገኛ መሆንን ትተን በተለይ በአሁኑ ሰአት ኤሌክትሪክ መኪኖችን መጠቀም መጀመራችን ተለዋጭ ኃይሎችን እንድንጠቀም ያስገድደናል በተጨማሪም ታዳሽ ኃይሎች ዘላቂ እና በአጠቃቀም የማይሟጠጡ ስለሆኑ እና ለኢኮኖሚው እድገትም ወሳኝ ሚና ስላላቸው ተመራጭ ናቸው›› የሚል ሃሳብ በስፋት አንስተዋል፡፡
በመሆኑም በሀገራችን የሚገኙ የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማጥናት በአጭር እና በረጅም ጊዜ የሥልጠና ፕሮግራሞችን መክፈት አስፈላጊ መሆኑ በአፅንኦት ተነስቷል፡፡

Read More »
News

ምቹ የፋይናንስ ሥርዓት ለስታርት አፕ ቢዝነሶች…

ምቹ የፋይናንስ ሥርዓት ለስታርት አፕ ቢዝነሶች…
መንግስት ለስራ ፈጣሪዎችና ስታርት አፕ ቢዝነሶች ምቹ የፋይናንስ ስርዓት ዘርግቷል አሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል።
ሚኒስቴሩ በሥራ ዕድል ፈጠራ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አዳዲስ የፈጠራ ሐሳብ የሚያመነጩ ስራ ፈጣሪዎችና ስታርት አፕ ቢዝነሶችን መደገፍና ለውጤታማነት ማብቃት አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዘርፉ ተዋንያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉና የፋይናንስ ስርዓቱ ለስራቸው ምቹ እንዲሆን የኢንቨስትመንት ልማት ባንክን ጨምሮ ዘርፉን የሚያጠናክር ስርዓት መዘርጋቱን ጠቁመዋል።
ይህም የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ አቅርቦት ተግዳሮቶችና ስጋቶችን ለመቅረፍ እንደሚያስችል አስረድተዋል።
ወጣቶች ክህሎታቸውንና የፈጠራ ስራዎቻቸውን የሚያጎለብት፣ ሐሳቦቻቸውንም እስከ ትላልቅ ፋብሪካዎች ማድረስ የሚያስችል ድጋፍ እየተሰጣቸው መሆኑን አንስተዋል።
ወጣቶች ያላቸውን የፈጠራ አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት አንዲያሸጋግሩ የሚያስችል ምቹ ምህዳር እየተገነባ መሆኑን ጠቅሰው÷ መንግሥትም ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ስታርት አፕ ቢዝነሶች ወሳኝ ሚና በመጫወት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ሚኒስትሯ አመላክተዋል። ዘገባው የፋና ብሮድካስቲንግ ነው።

Read More »
News

ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት

ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት
ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተከብሯል፡፡ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ በአቶ አብዱሠላም ሸንገል የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት የሚከበርበት ዋና ዓላማ ሥራ ፈጣሪ ትውልድን ለመፍጠር የሚያስችል ግንዛቤን በሥፋት ለማሰጨበጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሥራ የዝግጁነት መጓደል በስፋት የሚስተዋል ችግር መሆኑን የገለፁት የቢሮ ኃላፊው ‹‹የኢንተርፕረነርሺፕ እሳቤን በመላበስ ራሳችንና አካባቢያችንን መለወጥ ይጠበቅብናል›› የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩም በኢንተርፕረነርሺፕና ሥራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ገለፃ ቀርቦ ውይይት እንደተካሄደበት ከክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል፡፡

Read More »
News

የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ትልቅ ልብ እና ደፋር አመራር የስፈልጋል ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ትልቅ ልብ እና ደፋር አመራር የስፈልጋል
ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ዓለም አቀፍ ኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የመክፍቻ ስነ-ስርዓት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ አለም አቀፍ ተሳታፊ እንግዶች እና የዘርፉ ተዋንያን በተገኙበት ተከፍቷል፡፡
መርሃ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ መንግስት በኢትዮጵያ የኢንተርፕረነርሺፕ ስነ-ምህዳር እንዲሰፋ ካለው ከፍተኛ ቁርጠኝነት በመነሳት ዘርፉን የሚመራ ተቋም ከማቋቋም ጀምሮ አዳዲስ አሰራሮችን እየተገበረ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ጀምሮ ለዘርፉ እድገት በተሰጠ ቆራጥ አመራር ኢትዮጵያ በአለም መድረክ በዘርፉ ባስመዘገበችው ውጤት ስሟ ከፊት እንዲነሳ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ኢንተርፕረነርሺፕ ለግሉ ዘርፍ የተተወ ከነበረበት ወደ መንግስት ተቋማት በማምጣት፤ ኢንተርፕረነር የሆኑና ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የጀመሩ ተቋማት መታየት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ትልቅ ልብ እና ደፋር አመራር የስፈልጋል ያሉት ክብርት ሚኒስትር የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩትም በዚህ ቅኝት ስለተመራ በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ በርካታ በአይቻልም አስተሳብ የታሰሩ አዕምሮዎች ነጻ እንዲወጡ በር ከፍቷል ብለዋል፡፡
የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እጅ ለእጅ ተያይዘን ከተጓዝን ኢትዮጵያን የኢንተርፕረነሮች መፍለቂያ እናደርጋታለንም ብለዋል፡፡

Read More »
News

በሥራ አውደ ርዕዩ ከ20 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ

በሥራ አውደ ርዕዩ ከ20 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ
በከተማዋ ሰሞኑን ሲካሄድ የቆየው የሥራ አውደ ርዕይ በስኬት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው በከተማዋ በሚገኙ አስራ አንዱም ክፍላተ ከተሞች ቀጣሪ ድርጅቶችን ከስራ ፈላጊ ዜጎች ጋር በማገናኘት እንደየ ክህሎታቸውና እንደ ቀጣሪ ድርጅቶች የሰው ኃይል ፍላጎት የተካሄደው አውደ ርዕይ ተጠናቋል።
አውደ ርዕዩ ስራ ፈላጊ እና ቀጣሪ ድርጅቶችን በአንድ ቦታ በማገናኘት የከተማዋን ሥራ አጥ ዜጋ ወደ ሥራ በማሰማራት ሂደት ትልቅ ድርሻ አለው።
በከተማዋ 17ሺ600 ዜጎችን በስራ አውደ ርዕዩ ለማሳተፍ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ በመፈፀም 20ሺ522 ወይም የዕቅዱን 117 በመቶ መፈፀም መቻሉ ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ በአውደ ርዕዩ ከ100 እስከ 200 ቀጣሪ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ዝቅተኛው የደመወዝ መጠን 4ሺ እንዲሁም ከፍተኛው የደመወዝ መጠን ደግሞ 10ሺ እና ከዚያ በላይ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
የሥራ አውደ ርዕዩ መጠናቀቁን ተከትሎ በአንድ ጀንበር ለ20ሺ900 ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Read More »
News

የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት፤ ለምርታማነት!

የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት፤ ለምርታማነት!
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠ ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ውጤታማ በማድረግ ለሀገራዊ የልማት ፍጎት በቂ ምላሽ መስጠት እንዲችል መሠረተ ሰፊ የሪፎም ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
በዘርፉ ተለይተው ወደ ሥራ ከገቡ 11 አዳዲስ እሳቤዎች መካል የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት አንዱና ዋነኛው ነው።
ይህ እሳቤ ለሥራ ገበያው ፍላጎት ምላሽ መስጠትን፣ የየአካባቢውን ፀጋዎችን በአግባቡ ማልማትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማላቅን፣ የሥራ አጥነትን ምጣኔን ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስን እና የዜጎችን የኑሮ ጥራት ደረጃና ምርታማነትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻልን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
በዚህ አደረጃጀት ስምንት ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዞኖች ያሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተቋማት የየአካባቢያቸውን የመልማት ፀጋን እና አንፃራዊ ጠቀሜታን መሰረት አድርገው ስልጠና እንዲሰጡ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ይህም የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገው የክህሎት ልማት አቅጣጫ ማዕቀፍ የሚመራ ነው፡፡
ለምሳሌ በአዋሳና አካባቢዋ የሚገኙ ተቋማት በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማትና እሴት በማከል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነለት በሚያልቁ፣ በአካባቢው ለሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና የሰለጠነ የሰው ሀይል አቅራቢ በሚያደርጋቸው እንዲሁም አካባቢያዊ የልማት ፀጋን መሰረት በማድረግ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር በሚችሉ የስልጠና መስኮች ላይ እንዲያተኩሩና በዛው መስክ የልህቀት ማዕከል እንዲሆኑ የሚያበረታታ ነው፡፡
በዚህ ባህሪውም ዘርፉን ለሀገራዊ የልማት ፍላጎቶች ምላሽ ሰጪ እንዲሆን ለማድረግ ከተቀረፁ አዳዲስ እሳቤዎች መካከል ጠንካራ አመራርና ውሳኔ ሰጭነትን ከሚፈልጉት ሥራዎች መካከል ዋናው ነው ማለት ይቻላል፡፡
ባለፉት ዓመት የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀትን ጨምሮ በዘርፉ የተለዩ የሪፎርም እሳቤዎችን በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች መሬት ለማስነካት ሰፊ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችንም ማየት ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት ስትራቴጂን ለመተግበር ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡
በዚህም ተቋማት በአካባቢያዊ የመልማት ጸጋ ልየታ መሰረት የስልጠና ዘርፋቸው በመዘጋቱ ወደሌላ ተቋማት የተዛወሩ አሰልጣኞችን የመቀበልና በምስጋና የመሸኘት ሥራ ጀምረዋል፡፡
የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም ከተቋሙ ወደ ሌላ ቦታ ለተዛወሩ የሽኝት እንዲሁም ወደ ተቋሙ ለመጡ አዳዲስ አሰልጣኞች ደግሞ የአቀባበል መርሃ ግብር አዘግጅቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በዚህም በተቋሙ አንፃራዊ የልማት አቅም ልየት መሰረት 136 አሰልጣኞች ወደ ሌላ ተቋም የተዛወሩ ሲሆን 55 የሚሆኑ አዳዲስ አሰልጣኞችን የተቀበሉ መሆኑን የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ገልፀዋል፡፡
ለዕድገትና ሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑን ያነሱት አቶ መለሰ ከተቋሙ ለተሸኙ አሰልጣኞች የምስጋና፤ ተቋሙን ለተቀላቀሉ ደግሞ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በኮሌጁ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና አሁን ላይ በጡረታ ለተሰናበቱ ባለውለታዎች፣ በ2017 ዓ.ም ምርጥ ቴክኖሎጂ ለሰሩ አሰልጣኞች እንዲሁም ችግር ፈቺ ጥናት እና ምርምር ላደረጉ አሰልጣኞች የሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
somSOM
Scroll to Top