Mols.gov.et

mols mols

News

ሪፎርምን ወደ ዘላቂ ተቋማዊ ለውጥ ማሸጋገር

ሪፎርምን ወደ ዘላቂ ተቋማዊ ለውጥ ማሸጋገር የቀጣዩ የሪፎርም ምዕራፍ ዋና ትኩረት ነው
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና በተቋሙ በተካሄደው የሥራ ባህል ጥናት (Ecosystem Survey) ውጤት ላይ የሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች ውይይት አካሂደዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሚፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፣ ሚኒስቴሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባካሄደው ሰፊ ሪፎርም ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ ይህም ሪፎርሙ በተግባር ምላሽ መስጠት መጀመሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የተመዘገበው ውጤት የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን ለቀጣይ የላቀ አፈፃፀም መነሻ መሆኑን ጠቁመው፣ “ያስመዘገብነውን ውጤት ወደ ዘላቂ ተቋማዊ ለውጥ እንዴት እንቀይራለን?” የሚለው ጥያቄ የቀጣዩ የሪፎርም ምዕራፍ ዋና ትኩረት መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዚህም ተቋሙ ለዜጎች እርካታን፣ ለሠራተኞች የሙያዊ ኩራትን እና ለሀገር የላቀ አፈፃፀምን የሚያመነጭ ተቋም መሆን እንዳለበት ገልፀው ይህንን ለማሳካት በየደረጃው ያሉ የአሠራር፣ የመዋቅርና የተቋማዊ ባህል ክፍተቶችን በመለየት ማረም፣ ማሻሻልና በተከታታይ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሪፎርሙ የመጨረሻ መለኪያም በዜጎች ሕይወት ላይ የሚፈጥረው የሚታይ፣ የሚለካና ዘላቂ ጠቀሜታ መሆኑን አስረድተዋል።
በመሆኑም የቀጣዩ የሪፎርም ትኩረት የተመዘገበውን ውጤት የሚያስቀጥል ተቋማዊ ባህል፣ ውጤታማነትን የሚያረጋግጥ ሥርዓት፣ የሚያስተሳስር አሠራር እና ዘላቂ ተቋማዊ አቅም መገንባት መሆኑን ገልፀዋል።
ለዚህም የሚኒስቴሩአመራርና ባለሙያዎች በጋራ ርብርብ ማድረግ እና በተጠያቂነት መንፈስ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን ገመገመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን በጋራ ገምግሟል።
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ በሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ የትኪረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

Read More »
News

ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ ተግባር ተኮር የሙያ ዘርፎች

ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ ተግባር ተኮር የሙያ ዘርፎች
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተሻሻለው የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ከተቀመጡ ቁልፍ ስትራቴጂዎች መካከል ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ዜጎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን እንዲያገኙ ማስቻል(vocationalization አንዱ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ፣ በመደበኛ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉት 11 የሙያ ዘርፎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች በተገኙበት ተካሂዷል፤
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ መስተዳድር የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አዲሱ አሰራር ተማሪዎችን በክህሎት በመቅረጽ አምራች ዜጋ ለማፍራት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ የዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ በበኩላቸው ገበያው የሚፈልገው በክህሎት የበቃ የሰው ኃይል ለማቅረብ የተቀናጀ ሥራ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለሙያ ዘርፎቹን ለመተግበር የሚያስችል የመርሃ ትምህርት፣ የተማሪ ሞጁል እና የመምህር መመሪያ ዝግጅት በትምህርት ሚኒስቴር ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
በዚሁ መሠረት ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ብረታ ብረት ፣ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ አልባሳት ቴክኖሎጂ፣ ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ ቧንቧ ሥራ፣ ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ ሰብል አመራረት፣ ጤና ክብካቤ አገልግሎት፣ ሆቴል አገልግሎት፣ ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እና ምግብ ዝግጅት የመደበኛ የትምህርት መርሃግብር አካል ሆነው እንደሚሰጡ ተነግሯል።
መረጃው የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው

Read More »
News

“ሥራ ፈጣሪዎች እንጂ ሥራ ፈላጊዎች እንደማትሆኑ ሙሉ እምነት አለኝ” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

“ሥራ ፈጣሪዎች እንጂ ሥራ ፈላጊዎች እንደማትሆኑ ሙሉ እምነት አለኝ”
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በደረጃ 6 እና 7 በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1,875 ስልጠና አጠናቃቂዎች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ ትምህርትና ስልጠና የሰውን አቅም ለማዳበርና ለተሻለ የወደፊት ሕይወት ለመዘጋጀት የሚያግዙ መሠረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
“ትምህርትና ስልጠና በየደረስንበት ምዕራፍ ሙሉ ሰው እንድንሆን፣ መጪው ጊዜያችን ብሩህ እንዲሆን የሚያዘጋጁን የስንቅ ማዕዶቻችን ናቸው” ብለዋል።
ክብርት ሚኒስትር ተመራቂዎቹ ዛሬ ለዚህ ደረጃ የደረሱት በቀላሉ እንዳልሆነ ጠቁመው፣ ብዙ ሌሊቶችን በማጥናት፣ ብዙ ሰዓታትን በመሥራት፣ በጽናትና በትዕግስት እንዲሁም ከቤተሰብና ከልጆች ናፍቆት ጋር በመታገል ያለፉት ሂደቶች የጽናት፣ የብርታትና የዲሲፕሊን ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
“ዛሬ ነጋችሁን ምን ያህል ብሩህ እንደሆነ አጉልቶ የሚያሳይ ዕለት ነው” ሲሉም ተመራቂዎቹን አበረታተዋል።
ስልጠናም ሆነ ትምህርት የሀገርን እምቅ አቅም ለማውጣት፣ የሀገርን ችግር ለመፍታት እንዲውሉ ማድረግ ከተቻለ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ጉዞ ውስጥ ዘርፉ የማይተካ ሚናውን መወጣት xንደሚችልም አብራርተዋል፡፡
በዚህ የለውጥ ጉዞ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ከማፍራት ባሻገር፣ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በመፍጠር የሀገር ልማትን እንዲያግዝ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የዘርፉን አቅም ለማሳደግም እንደ ክህሎት ፓርክ (Skill Park) ያሉ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ እነዚህ ልማቶች ዘርፉን ወደ ላቀ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግሩም ገልጸዋል።
“ሥራ ፈጣሪዎች እንጂ ሥራ ፈላጊዎች እንደማትሆኑም ሙሉ እምነት አለኝ” ሲሉም ለተመራቂዎቹ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ክብርት ሚኒስትር ለተመራቂዎች ስኬት የወላጆች፣ የቤተሰብ፣ የመምህራንና የኢንስቲትዩቱ አመራሮች አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ጠቁመው ምስጋና አቅርበዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላለፉት በርካታ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የሰላም ቴክኒክና ሙያ መሥራች ወ/ሮ ፀሐይ ሮሺሊ ልዩ የእውቅና ሽልማት ተበርክቷል።

Read More »
News

የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ለማሟላት የግብርና ኮሌጅ

የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ለማሟላት የግብርና ኮሌጅ አመራሮች የፕሮጀክት አስተዳደር አቅም መጠናከር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከSNV ኢትዮጵያ የሆርቲ-ላይፍ (Horti-LIFE Green Growth) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በሆርቲካልቸር ልማትና በክህሎት ማሳደግ ላይ ያተኮረ የስድስት ወር አፈፃፀም ግምገማ፣ ውይይትና የሥልጠና መርሃ-ግብር በአዲስ አበባ አካሄደ።
‎በመድረኩ ላይ ከሰባት ክልሎች የተወጣጡ የ60 የግብርና ቴክኒክና ሙያ (A-TVET) ኮሌጆች ዲኖች፣ ምክትል ዲኖች፣ የመንግሥት አካላትና አጋሮች ተሳትፈዋል።

የመርሃ-ግብሩ ዋና ዓላማ የ15ቱን ኮሌጆች የሥራ አፈጻጸም፣ ምርጥ ተሞክሮዎች፣ የተማሪዎች የልምምድ ማሳ እና የአርሶ አደሮች የመስክ ስልጠና እንቅስቃሴዎችን በጋራ መገምገም እንደሆነ ተገልጿል፡፡
‎በተጨማሪም የአመራሩን የፕሮጀክት አስተዳደር አቅም በማጠናከር ተወዳዳሪና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት የሚያሟላ የሰው ኃይል ለማፍራት መድረኩ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

‎በሁለት ምዕራፍ በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም በመጀመሪያው ቀን፤ በኮሌጆች የተከናወኑ የሥራ አፈጻጸሞችና የመልካም ተሞክሮ ልውውጦች የተካሄዱ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ባለሙያዎች አማካኝነት ለኮሌጅ አመራሮች የፕሮጀክት ቀረጻ፣ የሀብት፣ የጊዜና የአደጋ አስተዳደር እንዲሁም የክትትልና ግምገማ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
‎በመጨረሻም የኮሌጆቹን የ2018/19 ዓ.ም የጋራ የሥራ እቅድ በማጽደቅና ለሰልጣኝ አመራሮች የስልጠና ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት በመስጠት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

Read More »
News

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ፣ የወጣቶች ሚና እና የኢትዮጵያ መጻኢ ዕድገት

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ፣ የወጣቶች ሚና እና የኢትዮጵያ መጻኢ ዕድገት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ወጣቶች ያስተላለፉት የክረምት ወቅት የሥልጠና ጥሪ ሀገራችን ወደ ዕውቀት-መር የዲጂታል ዘመን እያደረገች ያለውን ጉዞ በግልጽ የሚያሳይ ነው።
የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን መሠረት ያደረገው ይህ መልዕክት ወጣቶች የዕረፍት ጊዜያቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ወደሚያደርጋቸው የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲቀይሩት የሚያስችል ግዙፍ ሀገራዊ ራዕይ ሰንቋል።
በ’ዩዳሲቲ’ በኩል በነጻ የሚሰጡት እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው የመሠረታዊ ኮዲንግ፣ የዳታ ሳይንስ፣ የመተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ልማት እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሥልጠናዎች ወጣቶች የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የመገንባት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ የተመቻቹ ወሳኝ ዕድሎች ናቸው።
በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት እና በፈጣን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕድገት ውስጥ በሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ፣ የዲጂታል ክህሎት ባለቤት መሆን የሕልውና እና የብቃት ማረጋገጫ ሆኗል።
ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፍ ተፎካካሪነት በመገንዘብ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025’ን በስኬት በማጠናቀቅ፣ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂን ወደ መተግበር ተሸጋግራለች።
የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት በማድረግ የኢንተርኔት ተደራሽነትን ማሳደጓ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከ48 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ዘንድ ማድረሷ፣ እንዲሁም የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን በማስፋፋት የነዳጅ ግብይትን ጨምሮ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በዲጂታል መንገድ እንዲዘዋወር ማድረጓ ለዚህ የክህሎት ግንባታ ዋና አስቻይ መሠረተ ልማት ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪም እነዚህን የተዘረጉ መሠረተ ልማቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ እሴት ሊለውጥ የሚችል ብቁ የሰው ኃይል የሚያፈራ በመሆኑ ከሀገራዊው የዲጂታላይዜሽን ግስጋሴ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው።
እስካሁንም ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ሥልጠናቸውን ማጠናቀቃቸው ፕሮግራሙ ያገኘውን ሰፊ ሀገራዊ ተቀባይነት በጉልህ የሚያረጋግጥ ነው።
ጥሪው ወጣቶችን ማዕከል ማድረጉ፣ የኢትዮጵያን የሥነ-ሕዝብ ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም የተቀየሰ ስትራቴጂያዊ እርምጃ መሆኑን ያሳያል።
ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝቧ ዕድሜው ከ25 ዓመት በታች በሆነባት ኢትዮጵያ፣ ወጣቱን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪ እና አልሚ ማድረግ የሀገራችንን መጻኢ ብልጽግና ይወስናል።
በነጻ የሚሰጡት ዓለም አቀፍ የምሥክር ወረቀቶች፤ ወጣቶች ያለ ክፍያ እና ያለ ቦታ ገደብ ባሉበት ሆነው በዓለም አቀፉ የጊግ ኢኮኖሚ (Gig economy) ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሰፊ ዕድል ይከፍታሉ።
በተጨማሪም ወጣቶች ሀገር በቀል ችግሮችን የሚፈቱ አዳዲስ የፊንቴክ፣ የአግሪቴክ እና የኤሌክትሮኒክስ ንግድ መተግበሪያዎችን በመገንባት የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ቢዝነሶች (ስታርት-አፖች) እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።
ይህ ሂደት ወጣቶችን ከሥራ ጠባቂነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት በማሸጋገር፣ የሀገራችንን የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት የሚያግዝ እና የወጣቶችን ተስፋ በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ የወቅቱን የዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ፍጥነት እና የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ በሚገባ ያገናዘበ ብስል የፖሊሲ አመራር ማሳያ ነው።
ወጣቶች የክረምቱን ጊዜ በከንቱ ከማባከን ይልቅ የነገውን የቴክኖሎጂ ዓለም ለመምራት የሚያስችል ክህሎት መጨበጣቸው፣ የየራሳቸውን ሕይወት ከመቀየሩም በላይ ሀገራዊ ብልጽግናን ያፋጥናል።
ከ5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተቀላቅለውት የሚገኘው ይህ ታላቅ የዲጂታል ንቅናቄ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የበለጸገች እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተፎካካሪ እንድትሆን የሚያስችላት መጻኢ ተስፋዋ ብሩህ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።
መረጃው የEBC ነው።

Read More »
News

በሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ላይ ያተኮረው ስምምነት

በሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ላይ ያተኮረው ስምምነት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ ከጣሊያኑ ማርኬ ክልል (Marche Region) መንግሥት እና ለአፍሪካ የልማት አጋርነት ከሚሠራው APA-CVM ከተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የ1 ቢሊዮን ብር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የዉጤት ተኮር ሥልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ዳግማዊት ግርማ፣ የAPA-CVM የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ተወካይ ጆናታን አስካኒ (Jonathan Ascani) እንዲሁም የማርኬ ሪጅን የዓለም አቀፍ ትብብር አስተባባሪ አቶ ናታሊኖ ባርቢዚ (Natalino Barbizzi) በይፋ ተፈራርመውታል።
ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚቆየውና በጣሊያን ማርኬ ሪጅን መንግሥት ሙሉ በሙሉ በገንዘብ የሚደገፈው ይህ የልማት ፕሮጀክት፣ በዋነኝነት በሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ላይ አተኩሮ እንደሚንቀሳቀስ ታውቋል።
እነዚህም የቴክኒክና ሙያ (TVET) ተቋማትን አቅም በማጎልበት የሰልጣኞችንና የአሰልጣኞችን የሙያ ክህሎት ማሳደግ፣ ለሥልጠና ተቋማቱ አስፈላጊ የሆኑ ዘመናዊ የመማሪያና የቴክኖሎጂ ግብአቶችን ማሟላት እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶችና ባለሙያዎች የሥራ ዕድልና የገበያ ትስስር ማመቻቸት ናቸው።
መረጃው የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው

Read More »
News

በቆዳ እና በቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ብቃት ያለው ሙያዊ ሥልጠና …

በቆዳ እና በቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ብቃት ያለው ሙያዊ ሥልጠና በመስጠት ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደረገ
የኦሮሚያ ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ከጣሊያን ማርቼ ክልላዊ መንግሥት(Marche region) ጋር በመሆን በቆዳ እና በቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ብቃት ያለው ሙያዊ ሥልጠና በመስጠት ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል።
የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ኤባ ገርባ እንደገለጹት፤ ይህ ውይይት በቆዳ እና በቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ጥራትና ብቃት ያለው ሥልጠና ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆችን የማስፈጸም አቅም ማጠናከር፣ የአገራችንን የማምረት አቅም ማሳደግ እንዲሁም የቆዳ እና የጫማ ምርት ዘርፍን የዘላቂ ሥራ ዕድል ምንጭ ለማድረግ የሚያስችል ትልቅ እርምጃ ነው።
ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ለመፍጠር፣ የኢንተርፕራይዞቻችንን የመነሻ ገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር ውይይቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ኢንጂነር ኤባ ተናግረዋል።
የማርቼ ክልላዊ መንግሥት ተወካይ አቶ ናታሊኖ ባርቢዚ በበኩላቸው፤ ክልላዊ መንግሥታቸው በቆዳና በጫማ ምርት ዘርፍ የሙያ ሥልጠናን ለማጠናከር፣ የሰው ኃይል አቅምን ለማሳደግ እና ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከሲቪኤም (CVM) ከሚባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እና ከዩኒዶ (UNIDO) ጋር በመሆን ከኦሮሚያ ሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ቢሮ ጋር ለመሥራት ማቀዱን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወኑ ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶችን ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማስፋፋት ይህ ውይይት ወሳኝ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
ዘገባው የኦሮሚያ ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ነው

Read More »
News

የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር …

የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችል አቅም መፍጠርን ያለመ ስልጠና
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራና ክህሎት ቢሮ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
በጣልያን ፕሮጀክትና በሴቭ ዘ ችልድረን የፋይናንስ ድጋፍ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና በዘርፉ አዲስ እሳቤ፣ በባዮሜትርክስ ምዝገባና በዕቅድና ሪፖርት ዝግጅት ላይ ያተኩራል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአፋር ክልል፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ኢብራሂም ስልጠናው በዋነኛነት በየእርከኑ የሚገኙ አመራርና ባለሙያዎች የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችላቸውን አቅም ለማጎልበት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በሚገኙ 30 የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊዎች የባዮ ሜትሪክስ ምዝገባ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ቢሮ ኃላፊው የምዝገባ ሂደቱን በሚጠበቀው ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ዕውቀትን ቢሮው ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በሥራና ክህሎት ዘርፍ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉ ከዕቅድ ዝግጅት የሚጀምሩ እንደመሆናቸው ‹‹አንድ ዕቅድ፣ አንድ ሪፖርት›› የሚለውን የሚኒስቴር መ/ቤቱን መርህ ለመተግበርና የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ ስልጠናው ጉልህ ሚና አንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡
የሥራ ማዕከላትን ለማጠናከር በተጀመሩ ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ወጣቶችን ከአዳዲስ የሥራ ዕድል ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ያነሱት የቢሮ ኃላፊው የማዕከላቱን ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ የሚሰጡ መሰል ስልጠናዎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የሆኑ የሥራ ማዕከላትን እውን ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው የክልሉን ሰፊ የተፈጥሮ ፀጋ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚኖርባቸውም የቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ብቁ ባለሙያዎች የሚፈልቁባቸው ማዕከላት ለማድረግ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም በአፅንኦት አንስተዋል፡፡

Read More »
News

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት …

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ቅንጅታዊ አሠራሮችን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ተገለጸ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መርህ መሠረት በማጠናከር፣ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ በሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ባካሄዱት የጋራ ውይይት ተገልጿል።
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር፣ ክቡር አምባሳደር አዲስዓለም መለሰ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ውይይቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ እስካሁን የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የቀጣይ የጋራ ትኩረት አቅጣጫዎችን በስፋት ገምግሟል። በተለይም የሁለቱ ሚኒስቴሮች የተቀናጀ አሠራር ሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ይበልጥ ምቹ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ መሠረት የመረጃ ልውውጥን፣ የተቀናጀ ክትትልን፣ የጋራ የተግባር አፈጻጸምን እና የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ይበልጥ በማጠናከር የሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ፣ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ክብር በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችንና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚያሳድጉ ተግባራት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
በውይይቱ ላይ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መርህ መሠረት በሀገር ውጭ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ሥርዓቱ የተቀናጀ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት እንዲሆን ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን ትብብር የበለጠ እንደሚያጠናክሩም ተገልጿል።
ይህ ቅንጅታዊ አሠራር ሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን የበለጠ ውጤታማ ከማድረጉ ባሻገር፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
tigTIG
Scroll to Top