Mols.gov.et

የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ

July 11, 2026
የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አምራች ኃይልነት መቀየር ተችሏል ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የሚተገበረውን “የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ” ፕሮግራም በላቀ ጥራትና ተጠያቂነት ለመተግበር የሚያስችል የማስፈጸሚያ መመሪያ ሥልጠና በይፋ ተጀመረ። የሥልጠና መድረኩን በይፋ የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የሥራ፣ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምታከናውናቸው ታሪካዊና መዋቅራዊ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሪፎርሞች ዋና ማዕከል ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ” መሆኑን ጠቀሰው የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አምራች ኃይልነት እየተቀየሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ መንግስት በመደበኝነት ከሚያከናውናቸው የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች ጎን ለጎን ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በመተባበር እየተገበራቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችም ለወጣቶች ሰፊ የሥራ መፍጠሪያ አማራጭ በመሆን እያገለገሉ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። በዚሁ መሰረት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በሚተገብረው ‹‹የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ›› ፕሮግራም በሦስቱ ዙር 54,913 ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ እንዲሁም 52,786 ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን አስታውቀዋል፡፡ የተገኘው ውጤት የመንግሥት የሥራ ዕድል ፈጠራ ፖሊሲ በተግባር በዜጎች ሕይወት ላይ የሚታይና የሚዳሰስ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የሚያሳይ ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የሥራ ዕድል ፈጠራ ለከተሞች ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን ጠቅሰው ‹‹የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› መተግበር ከጀመረ በኋላ ወደ ከተሞች የሚደረግ ፍልሰትን ጨምሮ በተለያ ምክንያቶች ለሥራ አጥነት ችግር የተጋለጡ ወጣቶችን ህይወት በእጅጉ መቀየር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡ የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ በበኩላቸው በክልሉ በፕሮግራሙ ከስምንት መቶ በላይ ወጣቶችን በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ተሳታፊዎች ስልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ ብቁ የሆኑ አለማማጅ ድርጅቶችን መለየት እና መመልመል፣ የሥልጠናና የሙያ መስኮችን በጥናት መወሰን፣ተጠቃሚ ወጣቶችን በግልጽነትና በአድልዎ አልባነት መመዝገብ፣ የቴክኒክና ሙያ (TVET) ተቋማትንና የግሉን ዘርፍ በተቀናጀ መልኩ ማስተሳሰርና የከተማ አመራርን በሙሉ የሚያሳትፍ የኦሪየንቴሽን መድረክ በአጭር ጊዜ ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸውም ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top