Mols.gov.et

News

News

በከተማው ልማት ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘ ተቋም

በከተማው ልማት ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘ ተቋም
የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በከተማው ክህሎት መር አጫጭር እና መደበኛ ሥልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው።
ተቋሙ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት ዘርፍ ላይ ያደረገውን የሪፎርም ትግበራ ተከትሎ በአይሲቲ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ በእንጨት፣ በቆዳና እና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተጋ ይገኛል፡፡
ኮሌጁ ከሥልጠና በላይ ባለው ተልዕኮ የሥልጠና ጥራቱን የሚያረጋግጡና የውስጥ ገቢ አቅሙን የሚያሳድጉ ተግባራት እያከናወነ ነው፡፡
በዚህም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተኪ ምርቶችን እያመረተ ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት ደረጃቸውን የጠበቁ የፈርኒቸር ውጤቶችን እያቀረበ ይገኛል፡፡
የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ለሚገኘው የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዘመናዊ የቆሻሻ መጣያዎች እና ተንቀሳቃሽ የፈጣን ምግብ ማዘጋጃና መሸጫ ሱቆችን እያመረተ በማቅረብ በከተማው ልማት ላይ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
ይህም የኮሌጁ ሰልጣኞች የቴክኖሎጂ ሽግግርን ዕውን ለማድረግ ተጨማሪ አቅም እና የሥራ ባህል እንዲኖራቸው አስችሏል፡፡
በተመሳሳይ ኮሌጁ ከከተማ ውበትና እና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት እና ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማው በኮሪደር ልማት አረንጓዴ ሥራዎች ላይ ለሚሳተፉ ዜጎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን ኮሌጁ ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡

Read More »
News

ግብርናን በማዘመን በዘርፉ እየታየ ያለውን ውጤት ለማላቅ የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ግብርናን በማዘመን በዘርፉ እየታየ ያለውን ውጤት ለማላቅ የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ሁሉንም የግብርና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችል መርሃ ግብር በቅርቡ እንደሚጀምር ተጠቆመ
መርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት ተግባራዊ የሚያደርጉት ነው፡፡
ይህን በተመለከተ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችና አስፈላጊነቱ ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የግብርና ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴን ጨምሮ የክልል ግብርና ቢሮ፣ የግብርና ኮሌጆች እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ግብርናን በማዘመን በዘርፉ እየታየ ያለውን ውጤት ለማላቅ የባለሙያዎች አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡
ተግባራዊ የሚደረገው የግብርና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች የደረጃ ማሻሻያ ግብርና ሚኒስቴር የጀመረውን ውጤታማ ሥራ የሚያጠናክርና እየተገኘ ያለውን ውጤት በእጅጉ ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የቴክኒክና ሙያ ስርዓቱ እስከ ደረጃ 8 ድረስ እንዲዘልቅ መደረጉን ጠቁመው በዘርፉ ሥራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል የሙያ ደረጃና ሥርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን አመላክተዋል፡፡
በቀጣይ ከግብርና ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሰልጥነው የሚወጡ ዜጎች ዘርፉን ከማዘመንና ምርትና ምርታማነት እንዲረጋገጥ ከሚያደርጉት ሙያዊ ድጋፍ ባለፈ በሙያቸው ኩባንያ እንዲመሰርቱ የሚፈለግ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ለዚህም አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ላለው ውጤት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉት የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
ደረጃቸውን ለማሻሻል ያለመው ይህ መርሃ ግብር በዘርፉ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ከማሳደግ ባለፈ ተነሳሽነታቸውን እንዲጨምር የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
የግብርና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችለው መርሃ ግብር በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም ነው ክቡር ሚኒስትሩ የጠቆሙት።

Read More »
News

ከሀገር ውስጥ ባለፈ የዓለም የሥራ ገበያን ለመጠቀም ዜጎችን በክህሎት የማብቃት…

ከሀገር ውስጥ ባለፈ የዓለም የሥራ ገበያን ለመጠቀም ዜጎችን በክህሎት የማብቃት…
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በውጭ ሀገራት ከሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል አንዱ ነው፡፡
ዜጎች ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ ሀገራት እንዲጓዙ ከማድረግ ጀምሮ በመዳረሻ ሀገራት የሚኖራቸው ቆይታም ደህንነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ የውል ስምምነት ወደፈፀመባቸው ሀገራት የሚጓዙ ዜጎች በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ብቁ ለመሆን የሚያስችላቸው የክህሎት ሥልጠና በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የክህሎት ስልጠናውን እየሰጡ ከሚገኙ ተቋማት መካከል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት አንዱ ነው፡፡
ኢኒስቲትዩቱ ከሃምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሦስት ዙር ከአንድ ሺ ለሚነልጡ ሰልጣኞች የአረብኛ ቋንቋን ጫምሮ በቤት አያያዝ፣ በህፃናትና አዛውንት እንክብካቤና በምግብ ዝግጅት የክህሎት ሥልጠናን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሂደቱን ፈጣንና ቀልጣፈ ለማድረግ እንዲቻልም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጠና ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል ጋር በመተባበር ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የብቃት ምዘና በኢኒስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በቀጣይ ለ 400 ሰልጣኞች በአራተኛ ዙር ሥልጠናውን ለማስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ከኢኒስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፉ የክህሎት ድርጅት (World Skills) የሙሉ አባልነት ሰርተፊኬት ተቀበለች!

ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፉ የክህሎት ድርጅት (World Skills ) የሙሉ አባልነት ሰርተፊኬት ተቀበለች!
የአለምአቀፉ የክህሎት ድርጅት የኢትዮጵያን 88ተኛ የሙሉ አባልነት የማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሰጥቷል።
ኢትዮጵያ የአለምአቀፉ የክህሎት ድርጅት አባል መሆኗ በርካታ ፋይዳዎች ይኖሩታል። ከተለያዩ ሃገራት ጋር የኢንዱስትሪ ትስስር መፍጠር፣ በክህሎት ልማት ከተቀረው የአለም ክፍል ልምድ በመለዋወጥ እንዲሁም በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልምዶችን በመቅሰም በዘርፉ እየተሠራ ባለው ሥራ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት እና ከተቀረው የአለም የክህሎት ልቀት ጋር እኩል ለመራመድ ሰፊ ምህዳር የሚፈጥር ይሆናል።
አሁን እየተካሄደ በሚገኘው አለም የክህሎት ኦሎምፒክ ላይ ለመሳተፍ እና ከዓለም ጋር እርምጃችንን ለማስተካከል በእጅጉ የረዳን በመሆኑ ትልቅ የስኬት በር ከፋች እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።
ለዚህም ስኬት ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ!
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Read More »
News

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ነው

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ነው
47ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር በፈረንሣይ ሊዮን በሚካሄድ ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ በመድረኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች፡፡
የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ኢትዮጵያን 88ኛው አባል አድርጎ የተቀበላት ባለፈው ዓመት ሲሆን በውድድሩ በሦስት (ICT and Networking, CNC Machine, Furniture Making )የሙያ መስኮች ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እየተካፈሉ ይገኛል፡፡
በመድረኩ በ60 የሙያ መስኮች ከ70 አገራት የወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች እየተወዳደሩ ይገኛል።
የቴከኒክና ሙያ ስልጠና ለግላዊም ሆነ ሀገራዊ ልማት ያለውን ፋይዳ ማስተዋወቅና ወጣቶች ወደ መስኩ እንዲቀላቀሉ ማነሳሳት፣ ሀገራት የሥራ ገበያውን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ ስርዓቱን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና በትምህርትና ስልጠናና በኢንዱስትሪው መካከለ ትብብር እንዲጎለብት ማበረታታት እንዲሁም ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ማድረግ የውድድሩ ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው።
ኢትዮጵያ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ሲሆን የክህሎት ልማት ዘርፉ አካባቢያዊና ሀገራዊውን ብቻ ሳይሆን የዓለም የሥራ ገበያው ይዞ የሚመጣውን እድል መጠቀም እንዲቻል ታሳቢ ያደረገ ነው።

Read More »
News

ኢትዮጵያ በብሪክስ የሥራ ስምሪት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

ኢትዮጵያ በብሪክስ የሥራ ስምሪት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
ጉባኤው የወቅቱ የብሪክስ ሊቀመንበር በሆነችው በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል ።
በመድረኩ ከአባል ሀገራቱ የተውጣጡ ልዑካን በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጥራ፣ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤንነት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ምክክር እያደረጉ ይገኛል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ልዑካን እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ በበይነ መረብ መልዕት ያስተላለፉ ሲሆን በሠራተኞች ደህንነት እና በኢንዱስትሪ ግንኙነት ዙሪያ የኢትዮጵያን ተሞክሮንም አጋርተዋል።

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለሚኒስቴር መ/ቤቱና በሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ ለሚደረግላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ስጦታ አበረከቱ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለሚኒስቴር መ/ቤቱና በሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ ለሚደረግላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ስጦታ አበረከቱ፡፡
ክብርት ሚኒስትር የበዓል ስጦታውን ያበረከቱት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በየካ አካባቢ በቋሚነት ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ህፃናትና ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰራተኞች ነው፡፡
ጤፍ፣ ዶሮ፣ እንቁላልና ዘይትን ባካተተው የባእል ስጦታ ከ630 ሰላሳ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ ተጋርተዋል።
በስነሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በ2016 በጀት ዓመት የሚኒስቴር መ/ቤቱን ተልዕኮ ከማሳካት አንፃር ታላላቅ ስኬቶች የተገኙበት ዓመት እንደነበረ ገልፀዋል፡፡
‹‹ዓመተ ምርታማነት ›› ተብሎ በተሰየመው የ2016 በጀት ዓመት በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ረገድ ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
‹‹ዘመነ ማፅናት›› የሚል ስያሜ በተሰጠው የ2017 በጀት ዓመት የተገኙ ውጤቶችን በማፅናት ለዜጎቿ ምቹ የሆነችና ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ዕውን ለማድረግ በህብረት፣ በጋራና በአንድነት እንቁም የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Read More »
News

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ስርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አገኘ

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ስርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አገኘ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የሚሰጡት ስልጠና ለሥራ ገበያው ምላሽ የሚሰጥ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብቃት ምስክር ወረቀት የርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት ምልዕት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማሻሻል መሰረተ ሰፊ የሪፎር ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 20 ተቋማትን ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን እንዲያሟሉ በተያዘው ዕቅድ እስካሁን የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት ችለዋል፡፡
የሀዋሳ ፖሊቴክኒከ ኮሌጅ ሌላኛው የአይሶ ሰርተፊኬት ያገኘና በሀገራችን የISO 21001:2018 ሰርተፍኬት ያገኘ የመጀመሪያው ተቋም ነው ብለዋል፡፡
የሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ባለቤት መሆኑ የጥራት ሥራ አመራርን ከመተግበር አንፃር እንደ ሀገር ያለበትን ደረጃና እየተሰራ ያለውን ውጤታማ ሥራ የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ሁሉም የቴክኒክና ተቋማት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የሥልጠና እና የአስተዳደር ስርዓትን እያሟሉ በዚህ ስርዓት እንዲመዘገቡ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የሲዳማ ክልል የሥራ ፣ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው ኮሌጁ ከዚህ በፊት ከነበሩበት በርካታ ችግሮች በመውጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለውን ሰርቴፊኬት ማግኘቱ በዘርፉ የተገኘ ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል ።

Read More »
News

ሰመር ካምፕ ችግር ፈቺና ሀብት አመንጪ የሆኑ ፈጠራ የታከለባቸው ቴክኖሎጂዎች ማምረት የተቻለበት ነው ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ሰመር ካምፕ ችግር ፈቺና ሀብት አመንጪ የሆኑ ፈጠራ የታከለባቸው ቴክኖሎጂዎች ማምረት የተቻለበት ነው
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ኢንተርፕሪነርሺፕ ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ‹‹ሠመር ካምኘ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ›› የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ አስጀምረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት አምና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ላለፉት 12 ወራት ተኪ ምርቶችን የማምረት ሥራ በስፋትና በጥራት በሰመር ካምኘ ተሳታፊዎች ሲሰራ ቆይቷል።
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተወጣጥተውና በዓንድ ማዕከል ተሰባስበው ባለፈው አንድ ዓመት የፈጠራ ሥራቸውን የማዳበር ሥራ ሲሰሩ የቆዩት ወጣቶች ፋብሪካ ማምረት ጀምረዋል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ይህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን እራስን የመቻል ጉዞ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰመር ካምኘ ተሳታፊዎች በ11 ዘርፎች 81የሚሆኑ እጅግ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎች ማምረታቸውን ጠቁመው እነዚህ ፈጠራዎች በስፋት ተመርተው ለገበያ እንዲቀርቡ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top