Mols.gov.et

News

News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓት ግንባታ (system thinking) ላይ ተወያዩ፤

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓት ግንባታ (system thinking) ላይ ተወያዩ፤
በሪፎርም አስተሳሰብ ውስጥ የተወለደው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዳዲስ እሳቤዎችንና አሠራሮችን በመቅረፅ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ አዳዲስ አሰራሮች መካከል ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓትን (system thinking) በሚኒስትር መ/ቤቱ ለማስጀመር የሚያስችል የፐብሊክ ሰርቪስ ላብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ነው ፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአስተሳሰብ ሥርዓትን (system thinking) ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተካሄደ ጥናት ለካውንስል አባላቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ወጥ የሆነ እሳቤን ቀርፆ በየደረጃው የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚስችል ሥራ ሲሰራ ቆይቷል።
የዲጂታል አማራጮችን ጭምር በመጠቀም ዘርፉን ተናባቢ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት የተሰጠውን ተልዕኮ በሚመጥን መልኩ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተናባቢ የሆነ ሥርዓትን ለመገንባት እያንዳንዱ አመራር ኃላፊነቱን በትኩረት መወጣት እንደሚኖሩበትም በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡

Read More Âť
News

በተሟላ መልኩ መተግበር በጀመረው ሪፎርም እየመጣ ያለውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲቪል ሰርቫንቱ የማይተካ ሚና አለው፡፡

በተሟላ መልኩ መተግበር በጀመረው ሪፎርም እየመጣ ያለውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲቪል ሰርቫንቱ የማይተካ ሚና አለው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራር እና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
በዚህም ክብርት ሚኒስትር ዓበይት ሀገራዊ ክንውኖች እና ተግባራዊ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች እና ነባራዊ ሁኔታ አዝማሚያዎች ላይ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብብራሪያም ሰጥተዋል፡፡
መድረኩ መላው ሠራተኛ በጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረው እና ድርሻውን እንዲወጣ የተዘጋጀ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር እንደ ሀገር የተደረገው የተሟላ ሀገራዊ ሪፎርም የምንፈልገውን ውጤት እያመጣ ነው፡፡
በተሟላ መልኩ መተግበር በጀመረው ሪፎርም እየመጣ ያለውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲቪል ሰርቫንቱ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙም በተሰጠ ቆራጥ አመራር መሰረተ ሰፊ የሆነ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መደረጉን ጠቁመው ጊዜንና ጉልበትን እሴት በሚያክሉ፣ ሰላምን በሚያጸኑ ተግባራት ላይ ማዋል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የሰው ሀይል ምርታማነት ለማሳደግም ሲቪል ሰርቪሱ ሙስንናን የሚጠየፍ፣ ግዜውንና ጉልበቱን በአግባቡ የሚጠቀም አድርጎ መገንባት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የመድረኩ አመራርና ሠራተኞች በበኩላቸው በትልልቅ ሀገራዊ ጉዳች ላይ ሠራተኛውን ባለቤት ማድረግ መጀመሩ መጀመሩ አዲስ ባህልና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ የተደረገው ውይይትም ጊዜውን የጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
አፈፃፀሙ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትልቅ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የጠቆሙት የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደ ዘርፍ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጅ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

Read More Âť
News

352ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት የበላይ አካል (Governing Body) ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

352ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት የበላይ አካል (Governing Body) ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ትልቅ መድረክ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
በጄኔቫና ኦስትሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው እና ሌሎች የቴክኒክ ባለሙያዎችም ሃገራችን በመወከል በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና አሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አኳያ ተቀርፀው ተግባራዊ በተደረጉ የሪፎርም ሀሳቦች ማህበራዊ ፍትህን በማንገስ ዘላቂ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅትን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ተቀራርባ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡
ባሳለፈው ዓመት በጄኔቭ በተካሄደው 112ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሥራ ድረጅት ምክትል የበላይ አካል (ILO governing body) ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡

Read More Âť
News

በበጀት ዓመቱ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላትን በቴክኖሎጂና በአሠራር የማዘመን ሥራ ይሰራል፡፡

በበጀት ዓመቱ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላትን በቴክኖሎጂና በአሠራር የማዘመን ሥራ ይሰራል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ከሰዓት በፊት የደቡብ ምዕራብ እና የትግራይ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የክልሎቹ ሁሉም ከፍተኛና መካከለኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይቱ የክልሎቹ የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአሠሪና እና ሠራተኛ ግንኙነት እና የተቋም ግንባታ የሦስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የተያዘው በጀት ዓመት በዘርፉ በተተገበሩ የሪፎርም ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን በማጽናትና በማላቅ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የምናሳድግበት ነው፡፡
ለዚህ ግብ ስኬት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለየ የድጋፍና የክትትል ሥራዎችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ በየደረጃው መሰል የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡
በዚህ ዓመት በትኩረት ከተያዙ ሥራዎች ዋነኛው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከላት መሆናቸውን ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ማዕከላቱ የሚሰጡት አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ግልጽ፤ ፍትሃዊና ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡
የሚሰጡት ሰርተፊኬት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ማዕከላቱ ራሳቸው አውቅና ማግኘት እንደሚኖርባቸውም አንስተዋል፡፡
በዚህም ማዕከለቱ በቴክኖሎጂና በአሠራር የማዘመን እንዲሁም የሰው ሃይሉን አቅም የማሳደግ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ ክብርት ሚኒስትር ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read More Âť
News

ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተባለ፡፡

ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተባለ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የክልሎች አፈፃፀም ግምገማን ቀጥሎ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የሱማሌ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኮቹ ላይ ባስተላለፉት መልዕት፣ እንደ ዘርፍ በጀት ዓመቱ በስፋትም ሆነ በይዘቱ የተለየ ሥራ የምንሰራበት እንደሆነ ተግባብተን ወደ ተግባር ገብተናል፡፡
በዚህ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከተለመደው አሰራር የተላቀቀ አካሄድ እንዲሁም የተለየ የድጋፍና የክትትል ሥራ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በሦስቱም ዘርፎች የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የተጀመሩ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ጋር ተወያዩ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ጋር ተወያዩ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ውይይቱ በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂያዊ ግንኙነትን ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያና ቻይና በትምህርትና ስጠናው ዘርፍ የረዥም ጊዜ ትብብር እንዳላቸው የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር አሁን ላይ በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴክኒክና ሙያ ልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገ ያለው የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በቻይና መንግስት ድጋፍ የተሰራ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የተጀመረው ውይይት ስትራቴጂያዊ አጋርነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡
የቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ሪፎርም አድንቀው በሁለቱ ሀገራት መካከል በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የነበረውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡
በቀጣዮቹ ዓመታት ዘርፉን በቴክኖሎጂና በሰው ሃይል ማጠናከርና ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዘርፉን ሪፎርም መደገፍ የሚያስችሉ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር መስኮች ተለይተው ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ከውይይቱ በኋላ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የሚገኘውን የሉባን ወርክሾፕ ጎብኝተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከቲያንጅን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዣንግ ጂንጋንግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

Read More Âť
News

ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ

ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ
ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡
ክብርት ሚኒስትር ይህን የገለፁት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዘርፉን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በተገመገመበት መድረክ ላይ ነው፡፡
ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በበጀት ዓመቱ እንደ ዘርፍ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የተቀናጀና የተናበበ ርብርብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡
በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ መሰረት ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡
እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራ ግብዓትና ግብይት መስኩ ላይ ለበርካቶች ሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚቻል የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በየደረጃው ያለውን ፀጋ መሰረት ያደረገ እና ያለውን ፍላጎት ያማከለ ሥራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

Read More Âť
News

የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆመ

የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ቀጥሎ የሲዳማ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በዚህ ዓመት የሚደረገው የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን ይፈልጋል ብለዋል፡፡
ዜጎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከመደበኛ እና አጫጭር ስልጠናው በተጨማሪ በልምድ የተገኘ ሙያ ላይ ግብ አስቀምጦ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

Read More Âť
News

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ደ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጻ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ተሻለ በመግለጫቸው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ እንደሚዘጋጅ ገልጸው በዚህ ዓመትም የ12 ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 526,683 የሚሆኑት ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ ስልጠና ለመሰልጠን ተቋማቱን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡
ገበያ ተኮር በሆኑ በአጫጭር ስልጠናዎች ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተቋማቱ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሰልጣኞች በተቋማቱ በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ በክረምቱ የአሰልጣኞች የአቅም ግንበናታ ስልጠና፣ የማሽነሪዎች ጥገና እና አስፈላጊ የማሰልጠኛ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ይህንን የመቁረጫ ነጥብ መነሻ አድርገው ሰልጣኞችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል፡፡
ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ የተቀመጡ የመቁረጫ ነጥቦች ዝርዝር ከታች ይመልከቱ

Read More Âť
News

የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የክልሎችን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምን ግምገማን ቀጥሎ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የአማራ ክልል የዘርፉ እቅድ አፈፃፀምን ተመልክቷል፡፡
በመድረኩ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የማህበራዊ ጉዳይ እና የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ የሦስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ በዘርፉ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የተደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ ያለው የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት የመፍጠር ሥራ የተለየ አካሄድን፣ የክትትልና ድጋፍ ሥራን የሚጠይቅ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የተጀመሩ ስራዎችን ለማላቅ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ለክህሎት ልማት፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ድጋፎችን ለማመቻቸት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ እንደ ሀገር ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top