Mols.gov.et

News

News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ጋር በትብብር መስራት…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ስነ- ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፤ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ፤ ተወዳዳሪ እና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራ ውጤታማ እንዲሆን የአመራር ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ስለሆነም ከአመራር ልማት ሥራ ባለፈ አካዳሚው የኢንተርፕረነርሺፕ ባህል ለመገንባት ከሥርዓተ ሥልጠና ቀረጻ ጀምሮ፣ ተወዳዳሪ የሆኑ፣ አምራች ዜጎችን መፍጠር የሚያስችል ምቹ አውድ እስከ መፍጠር ድረስ የሚከናወኑ ተግባራትን በማላቅ ረገድ ያለው ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብረሃ በበኩላቸው፤ ስምምነቱ በዋናነት የአመራር ልማት፣ የሥራና ክህሎት ልህቀት ሽልማት፣ የሥራ ባህል ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ግንባታ እና የጥናትና ምርምር ሥራዎችን አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Read More »
News

የጋራ ትብብሩ ፓን አፍሪካኒዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡

የጋራ ትብብሩ ፓን አፍሪካኒዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ልዩ አማካሪ ትራወሬ አኖውሳ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በክህሎት ልማት፣ ኢንተር ፕሪነርሺፕ እና መሰል ዘርፎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥና በትብብር ለመስራት ባለመው ውይይት ቡርኪና ፋሶ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመስራት እንደምትፈልግ አማካሪው ጠቁመዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ በሚሰጠው የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ቀጠናውን በልማት ሊያስተሳስሩ በሚያስችሉ ጉዳዮች በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳንና ለሱማሊያ በሰጠቸው የትምህርትና ስልጠና ዕድል ከ250 በላይ ሰልጣኞች በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛል ብለዋል፡፡
በኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስር በሚገኘውና ዓለም አቀፍ እውቅና ባገኘው የቴክኖሎጂ ፋብሪኬሽንና የብየዳ ልህቀት ማዕከል ውስጥ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን እየወሰዱ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ከቡርኪና ፋሶ ጋር መሰል ትብብር እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
ይህም በጋራ አብሮ ከመልማት ባሻገር ፓን አፍሪካኒዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነም ክብርት ሚኒስትር አመላክተዋል፡፡

Read More »
News

ከአርባ ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

ከአርባ ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከ40ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ጋር ተፈራርሟል፡
ስምምነቱ በቀጣዩ ዓመት የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ በሚያካሄደው የግብርና ናሙና ቆጠራ/Agricultural sample survey/ ላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎችን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰራተኞች ለምቶ ወደ ሥራ የገባውን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓትን በመጠቀም ለመቅጠር የሚያስችል ነው፡፡
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፣ የሥታስቲክስ አገልግሎቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሄደው የግብርና ናሙና ቆጠራ ባለፉት ዓመታት በገጠርና በከተማ ግብርና እንዲሁም በሌማት ትሩፋት የተሠሩ ሥራዎች ያስገኙትን ውጤት በትክክል ለመለካት የሚያስችል በመሆኑ ለሀገር በቀል ሪፎርም ሥራችን ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡
ከ22 ዓመታት በሁዋላ በሚሰበሰበው በዚህ ሥራ መረጃውን የሚያሰባስቡ ዜጎች ምልመላና ቅጥር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሠራተኞች ለምቶ ወደ ሥራ በገባው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (ELMIS) አማካኝነት እንዲፈፀም ለማስቻል ስምምነቱ መደረጉን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ይህም ፍትሃዊ፣ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የቅጥር ሂደቱን በማጠናቀቅ በፍጥነት ሥራውን ለማስጀመር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያውያን ወጣቶች የለማው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የሥራ ገበያውን ማዘመን ፣ ገበያው የሚፈልገውን የክህሎት አይነት መለየትና በርካታ የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች በፍትሃዊነት የመፍጠር ዓላማ ያለው መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ሥርዓቱን ለመጠቀም ያሳየው ተነሳሽነት ለሌሎችም ተቋማት አርአያ እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በመላ ሀገሪቱ የሚተገበርና መረጃዎችን በአጭር ጊዜና በጥራት ለማሰባሰብ የሚያስችል መሆኑ የሥታስቲክስ አገልግሎቱ ለሚያካሄደው የግብርና ናሙና ቆጠራ በላቀ ደረጃ ተመራጭ እንዳደረገው ገልፀዋል፡፡
በመረጃ ማሰባሰብ ሥራው ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ወጣቶች በየአካባቢያቸው በሚገኙ የሥራ ዕድል ፅ/ቤት በመገኘት የባዮሜትሪክ መረጃቸውን በመስጠት መመዝገብና በሥራው ላይ መሰማራት እንደሚችሉም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

Read More »
News

በምዘና ብቃታቸው ለተረረጋገጠ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጠ

በምዘና ብቃታቸው ለተረረጋገጠ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጠ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር (GIZ) ጋር በጋራ ሲተገብረው በቆየውን STEP (Sustainable Training and Education Program) ፕሮግራም አፈፃፀም አስመልክቶ ከተለያዩ ዘርፎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር) ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ፕሮግራሙ ለቴክኒክና ሙያ ምሩቃን በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
በዕለቱ ክህሎትና ብቃት ያላቸው ሰልጣኞችን ከማፍራት፣ የትብብር ሥልጠናዎችን ከመስጠት ፣ ዲጂታላይዜሽን ከማሳደግ አንፃር በፕሮግራሙ በተከናወኑ ተግባራትና በተገኙ ውጤቶች ላይ ውይይ ተደርጓል፡፡
የመንግሰትና የግሉ ዘርፍ በትብብር ለሚሰጡት ተግባር ተኮር የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠውም በውይይቱ ተመላክቷል፡፡
ከውይይቱ ጎን ለጎን የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ምርታቸውን ለዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን የተዘጋጀ ሲሆን በኮንስትራክሽንና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ለበርካታ ዓመታት በልምድ ሲሰሩ ለነበሩና ከግል ዘርፍ ጋር በመተባበር በምዘና ብቃታቸውን ላረጋገጡ በቀለም ቅብ፣ በአናጺነት፣ በግንባታ፣ በለሳኝነት ሙያ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የዕውቅና ሰርትፍኬት ተሰጥቷል፡፡

Read More »
News

ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ
የደቡብ ኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ላለፉት አምስት ቀናት ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ደቡብ ኮሪያ ቴክኒክና ሙያን ከእድገታቸው ጋር አስተሳስረው በመሥራታቸው በዘርፉ ስኬት ማስመዝገባቸውን ገልጸው አመራሩ በዚህ ስልጠና ያገኙትን እውቀትና ልምድ ለሀገራችን በሚሆን መልኩ መተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
መንግስት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና ጥራት የሚያሻሽሉ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን የጠቆሙት ሚ/ር ዴኤታው መሰል ድጋፎች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትን ለማሻሻል እያደረገ የሚገኘው የግብዓት እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን በመገለጽ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ኮርያና ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ፣ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ትምህርትና ሌሎች ዘርፎች ለይ በአጋርነት እየሰሩ መሆኑንም ተገልጿል።

Read More »
News

አዲሱ የጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞ

አዲሱ የጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ለሥራ ዕድል ፈጠራ አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር እና የዘርፉን ችግሮች በመቅረፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል።
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሰምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅንና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ ፖሊሲው ለዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር እና የዜጎችን ገቢ ትርጉም ባለው መልኩ ማሳደግ የሚያስችል ነው፡፡
የዘርፉ አዲሱ እሳቤ ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠርና ዳቦ በልተው እንዲያድሩ ከማድረግ የዘለለ መሆኑን ጠቁመው አዲሱ ፖሊሲ ይህንን ታሳቢ አድርጎ የተቀረጸ ነው ብለዋል።
በመድረኩ ፖሊሲውን ተከትለው የተዘጋጁ የሥራ ፈጠራ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የኢንተርኘራይዞች የኢኮኖሚ ቀውስ ጊዜ ምላሽ መስጫ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ እና ከፍተኛ የማደግ አቅም ያላቸው ኢንተርኘራይዞች ማበረታቻ ስርዓት ሰነዶች ለውይይት ቀርበው ተጨማሪ ግብዓት የሚሰባሰብበት ይሆናል፡፡

Read More »
News

በኢትዮጵያ የስታርትፕ ስነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ …

በኢትዮጵያ የስታርትፕ ስነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው የሕግ ማዕቀፍ ላይ ውይይት ተካሄደ
እንደ ሀገር ፈጠራ በታከለበት አግባብ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ አንድን ችግር ለመፍታት የሚቋቋሙ ስታርታፖች የሚበረታቱበትና የሚደገፉበት የሕግ ማዕቀፍ አልነበረም፡፡ ይህን በመገንዘብ መንግስት ስታርት አፖችን በአግባቡ ማስተናገድ የሚያስችል ስነ-ምህዳር ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የረቂቅ አዋጅ ዝግጅቱ የደረሰበት ደረጃ ማየት እና ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ታሳቢ ባደረገው ውይይት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና ብሩክ ታዬን(ዶ/ር) ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር…

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ ነው

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ኢኒሼቲቩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና የኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 5 ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ነው፡፡
ስልጠናውም በዋናነት በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
ከኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያው በተጓዳኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ኢኒሼቲቩ የትምህርት ዘርፉ ብቁ ትውልድ ለመገንባት በሚያከናውነው ስራ ላይ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
በተለይ ትውልዱ በንድፈ ሃሳብ የሚያገኛቸውን እውቀቶች በቀላሉ ወደ ተግባር እንዲለውጥ ምቹ እድል በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው ቴክኖሎጂ ከስራ ፈጠራ ጋር የሚተሳሰር ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የወጣቶችን ዲጂታል አቅም ለመገንባት የተሰጠው ትኩረት ደግሞ ግብርናን ጨምሮ የተለያዩ መስኮችን ለማዘመን የተያዘውን ውጥን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው የተናገሩት፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስትን ወክለው በፓናሉ የተሳተፉት አብዱልአዚዝ አልጃዝሪ በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እውን በማደረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነት መኖሩን አንደታዘቡ ተናግረዋል፡፡
ይህ ደግሞ በኢኒሼቲቩ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
ቴክኖሎጂ የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በእጅጉ እየቀየረ ስለመሆኑ አንስተው፤ ከዚህ አኳያ ለዘርፉ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት አቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያብራሩት ደግሞ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
በእቅዱ ላይ ዲጂታል ክህሎትን መሰረት ያደረገ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት እንደተሰጠው ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም ይህን እውን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢኒሼቲቩ በኢትዮጵያ ክህሎት ያለው የሰው ሃይልን በመገንባት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአገልግሎቱ ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ዘመናዊና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እውን ማድረግ መንግስት እያከናወነ ያለው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች ዲጂታል ክህሎት ማደግ እንዳለበት ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያውን የሚያግዝ እንደሆነ ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Read More »
News

የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ግብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ግብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ

የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 እና 123/13 ለማሻሻል የሚያስችል የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ከውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲ ማህበራት ተወካዮች ጋር በሚኒስቴሩ አዳራሽ አካሄዷል፡፡
በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ዜጎች መብታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ አገር እንዲሰማሩ በማደረግ ዜጎችና እና ሀገራችን ከውጭ አገር ሥራ ሥምሪት የሚገባውን ጥቅም እንዲገኝ መሆኑን ገልጸው አሁን ሥራ ላይ ያለውን የዘርፉ አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት አሁን ካለንበት ጊዜ ጋር ሊያሰራ የሚችል ዘመናዊ ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት ያለመ ነው፡፡
የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት እንዲታገዝ በማድረግ እጅግ ውጤታማ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የሚሻሻለው አዋጅ ህጋዊ የስራ ስምሪቱን በማጠናከር የህገወጥ ሰዎች ዝውውርን በመግታት በኩልም ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አዋጁ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ሁሉ በውስጡ ያካተተ እንዲሆን ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉበት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Read More »
News

የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለፀ

የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር የሚመክርበት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና እና የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ የበለፀገ ማህበረሰብ እና ሀገር ለመገንባት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡
ከዚህ አንፃር ከስልጠና በላይ በሚል የክህሎት ልማት ዘርፉ አዲስ እሳቤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዜጎችን ክህሎት ከማስታጠቅ አልፈው የትምህርትና ሥልጠና ጥራቱን በሚያረጋግጥ መልኩ የተለያዩ ሥራዎችን እንዲሰሩ፤ ተኪ ምርቶችን እንዲያመርቱና ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እየተሰራ ያለው ሥራ እጅጉን የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉም ሚኒስቴሩ ሥራ ዕድል በመፍጠር ብቻ ሳይሆን ስነ-ምህዳሩንም ምቹ ከማድረግ እንዲሁም በሠላማዊ ኢንዱስትሪ ከመፍጠር አኳ እጅግ ወሳኝ የሚባሉ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዓመታት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል እና ሰላዊ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር በትኩረት ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡
የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር የተከበረው የምክርቤት አባላት ይህንን ከግምት በማሰገባት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያድጉ ጠይቀዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top