Mols.gov.et

mols mols

News

ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ……

መንግስት የነገውን አለም እጣ ፈንታ የሚወስነውን ድጅታል ኢትጵያ እውን ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
ክቡር ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ የቢዝነስ ፕሮሰስ አውቶሶርሲንግ ኢኮሲስተም ኢንሼቲፍ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት መልዕክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ መንግስት የነገውን አለም እጣ ፋንታ የሚወስነውን ድጅታል ኢትጵያ እውን ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ የተለየውን የአይሲቲ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና የቴሌኮም ዘርፍ ለገበያ ክፍት ማድረግን ጨምሮ የመንግስት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ በድጅታል አማራጭ በማቅረብ ድጅታል 2030 እውን ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የድጅታል ቴክኖሎጂ በመስፋፋቱ ምክንያት ለወጣቶች ዘርፈ ብዙ በረከቶች እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ከነዚህ በረከቶች መካከል ወጣቶች ባሉበት ቦታ ሆነው በየትኛውም አለም ክፍል የሚገኝን ሥራ በርቀት እንዲሰሩ በር ተከፍቷል ብለዋል፡፡
በዚህ የእርቀት ስራ ባለፉት ዓመታት በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ተሰማርተው ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ከማግኘት ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደቻሉ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ በቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ስራ ተደራጅተው የተሰማሩ ተቋማት ከትላልቅ የአለማችን ኩባንያዎችና ድርጅቶች የተወሰነውን የሥራ ሂደት ሥራ ወስደው በመተግበር ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ዘርፍ ሀገራችን ተወዳዳሪ ለማድረግ የኢትየዮጵያ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ማህበር ተቋቁሞ ዉጤታማ ተግባራት በማከናወን እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
ሸገር ከተማም በዛሬው ዕለት የነገውን የሥራ ዓለም የሚወስነውንና ለበርካታ ወጣቶች ጥራት ያለው የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችለውን የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ሥራ በይፋ መቀላቀሉን ገልጸዋል፡፡
ወጣቶች በመሰል ድጅታል ሥራዎች ተጠቃሚ ለመሆን ድጅታል ክህሎት መታጠቅ አማራጭ የሌለው በመሆኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገውን የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ጨምሮ በሌሎችም የድጅታል ክህሎቶች እራሳቸውን ብቁ አድርገው ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከ4 መቶ 54 ሺህ 106 በላይ ዜጎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከ4 መቶ 54 ሺህ 106 በላይ ዜጎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለዜጎች ተግባራዊ እውቀትና ክህሎትን በማስታጠቅ የሥራ ፈጠራ አቅምና ችግር ፈቺ አስተሳሰቦችን ያለውን ቁልፍ ሚና በመገንዘብ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራበት ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ መስጠት እንዲችል የሥራ ገበያውን መሰረት ያደረገ የክህሎት ልማት አቅጣጫ ነድፎ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በመደበኛና አጫጭር ስልጠና ተደራሽ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህ መሠረት 2017 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን፣ የሥራ ገበያው ፍላጎት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቅበላ አቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት የ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት መቀበያ መቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፉት ሦስት ዓመታት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ከ1,500 ባላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በአካባቢያቸው ያለውን ተፈጥሯዊ ፀጋ መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲደራጁና ስልጠና እንዲሰጡ መደረጉን ክቡር ሚኒስትር ድኤታው አስታውቀዋል፡፡
የተቋማቱን የቅበላ አቅም ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የውስጥና የዲጂታል መሰረተ ልማትን የማስፋፋት ሥራ ሲሠራ መቆየቱን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በ2017 ዓ.ም በመደበኛ ከ5መቶ ሺ በላይ፣ በአጫጭር ስልጠና ደግሞ ከ4ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከ1መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ በልምድ የሙያ ባለቤት የሆኑ ዜጎች ተመዝነው ዕውቅና ማግኘታቸውን ብሎም ከ5መቶ ሺ የሚልቁ ደግሞ ለውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ብቁ የሚያደርጓቸውን ስልጠናዎች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት መከታተላቸው ተገልጿል፡፡
በ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ከ4መቶ 54ሺ1መቶ ስድስት የሚሆኑ ዜጎችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ለማሰልጠን፣ 4ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች አጫጭር ስልጠና በመስጠት ለሀገር ውስጥ የሥራ መስኮች ለማብቃት እንዲሁም ቁጥራቸው እስከ 8መቶ ሺ የሚሆኑ ዜጎችን ደግሞ በስልጠና አብቅቶ ለውጭ ሀገር የሥራ ገበያ ዝግጁ ለማድረግ የሚያስችል ዕቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡
ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

Read More »
News

ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል የሚገኙ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በዘርፉ እያከናወኑአቸው የሚገኙ ተግባራት ውጤታማ ተግባራት አሰመልክቶ ተሞክሮአቸውን ያቀርባሉ ተብሏል
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ የካምፓላ ውሳኔን ተከትሎ ኢትዮጵያ ስደተኞችን ከተረጂነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሸጋግሩ ተጨባጭ የሆኑ ተቋማዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች ብለዋል፡፡
ለአብነትም ለሥራ ብቁ የሆኑ ሥደተኞች እና ከስደት ተመላሾች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት እንዲመዘገቡ በማድረግ የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ይህም በቀጠናው የሚገኙ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የመሆን መብታቸውን የሚያረጋግጥ፣ የጋራ ትስስርና ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያም ስደተኞችና ከስደት ተመላሾችን አስመልክቶ የተወሰነው የካምፓላ ውሳኔ አርዓያ በሆነ መልኩ መተግበሯን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
በኢጋድ ጥላ ስር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ስደተኞችንና ከስደት ተመላሾችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፈጠራ የታከለባቸው ተግባራት ያለ ልዩነት በመተግበር የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
በመድረኩ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመለሾች አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን፣ የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች እና የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

Read More »
News

ስታርታፕ ለስራ ዕድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው – ሚኒስቴሩ

ስታርታፕ ለስራ ዕድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው – ሚኒስቴሩ
ስታርታፕ ለስራ ዕድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለፁ።
መንግሥት ስታርታፕን በማሳደግ ኢኮኖሚውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችሉ አሰራሮችና የህግ ማዕቀፎችን አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የስታርታፕ ስነ ምኅዳሩን ማስፋት የሚያስችል የክህሎት ልማትና አዳዲስ የስራ ዕድል ፈጠራን የሚያበረታቱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች የሚወዳደሩበት “ብሩህ ኢትዮጵያ” የክህሎት ውድድር ሀገራዊ ልማትን የሚያሳልጡና ስታርታፖችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1ሺህ 350 የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ዜጎች እውቅና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ የሚኖረውን ፋይዳ አሟጦ ለመጠቀም አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ስታርፖች የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የአቅም ግንባታና ሌሎች ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት፡፡
የዜጎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ስታርታፕ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት፤ ስታርፖች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታርታፕ ዘርፍ ኃላፊ ሙልጌታ ውቤ በበኩላቸው፤ የወጣቶች የስራ ፈጠራ ዝንባሌ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
መንግስት የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የስታርታፕ አዋጅ በማጽደቅ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡
የፈጠራ ሀሳቦች ስታርፕ መሆናቸው በህጉ ተለይቶ ምዝገባና ስያሜ ከተጠሰ በኋላ አስፈላጊው የፋይናንስና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡
አዋጁን ገቢራዊ ለማድረግ ሀገር አቀፍ የስታርታፕ ፖርታል እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ የማስፈጸሚያ ደንቦችና መመሪያዎች ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል ሰል ኢዚያ ዘግቧል::

Read More »
News

የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት…

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤት ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በህጋዊ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቺፍ ኦፍ ሚሺን አቢባቱ ዋኔ ጋር ተወወያዩ።
ክቡር አቶ ዳንኤል በውይይቱ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ህጋዊ የሥራ ስምሪቱን ማጠናከር ዋነኛው መፍትሄ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ አገር የሥራ ስምሪትን አዋጅ አሻሸሎ ወደ ተግባር መግባቱን ገልፀዋል።
የዜጎችን መብት ደህንነት ለማስጠበቅ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቺፍ ኦፍ ሚሺን አቢባቱ ዋኔ በበኩላቸው በፍልሰት ለስራ ወደ ተለያዩ ሃገራት ለሚሄዱ ሰራተኞች መብትን የሚያሰጠብቁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቀረጽ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚሰራው ሥራ አሰፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

Read More »
News

የክህሎቶች ልማት፤የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር

የክህሎቶች ልማት፤የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር
አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ።ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል።
ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል።በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል።
ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል።
ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው።
የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል።
ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል።
አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት።
ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው።
የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው።
ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው።
የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው።
በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል እንደሚገመት ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው።

Read More »
News

በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልሱና መጪውን ጊዜ መዋጀት እንዲቻል የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ።

በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልሱና መጪውን ጊዜ መዋጀት እንዲቻል የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም ሳምንታዊ የጥናትና ምርምር ሴሚናሩን አካሂዷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በ2017 ዓ.ም 37 ያልተቆራረጠ የጥናትና ምርምር ሰሚናሮች መካሄዳቸውን አመላክተዋል።
በዚህም 110 የሚደርሱ ለሥልጠና ጥራት እና ለቴክኖሎጂ እንዲሁም ለተጨማሪ ጥናት መነሻ የሆኑ ግብአቶች መገኘታቸውን ገልፀዋል።
የጥናትና ምርምር ሴሚናር አስፈላጊነት አመራሮቻችን፣ አሰልጣኞች፣ እና ሰልጣኞቻችን እንደተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ራሳቸውን የሚያድሱበት፤ ጥያቄ የማንሳትና ራሳቸውም ለመጠየቅ ዝግጁ የመሆን ባህልን እንዲለመድ ያደረገ መሆኑንም ነው ያመላከቱት።
ሁሉም የሥልጠና ፕሮግራሞች በጥናት በተደገፈ እና የሥልጠና ፕሮግራሞች በዘልማድ ከመከፈት ይልቅ ነገን መሰረት ያደረጉ እና የሀገርን ጥቅም በለየ አግባብ መከለሳቸውን አመላክተው አዳዲስ ፕሮግራሞች መከፈታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በዚ ዓመት የሚካሄዱ ሴሚናሮች የባለፈውን ዓመት የሚደግም ሳይሆን በአዲስ መልክና አቀራረብ ያላቸው መሆኑን ያመላከቱት ዶ/ር ሀብታሙ በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልሱና መጪውን ጊዜ መዋጀት እንዲቻል የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዚህ ዓመት የሀገርና የዓለምን አበይት ክስተቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ሥራ እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

በዘርፉ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ላይ ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በዘርፉ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ላይ ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዘርፎች አፋጻጸምን ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት መገምገም ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የክህሎት ልማት ዘርፉ አፈፃፀም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎቶቻችን ምላሽ መስጠት እንዲችል በአዲስ እሳቤ ተቃኝቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በሩብ ዓመቱ በዘርፉ የተሰሩ ሥራዎች አበረታች ቢሆኑም ዘርፉ ከተሸከመው አገራዊ እና ተቋማዊ ተልዕኮ አኳያ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎቶቻችን ምላሽ መስጠት መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ አመላክተው፤ ፈጠራንና ፍትነትን ያማከለ ተቋማዊ ዝግጁነትን ጨምሮ አቅማችንን እና ቅንጅታችንን ይበልጥ ማጠናከር ይገባናል ብለዋል፡፡
ዘርፉ ለሀገር ውስጥም ይሁን ለውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት መሰረት የሆኑ ስራዎች የሚሰሩበት በመሆኑ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ለፈጠራ እና ፍጥነት እንዲሁም ለጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት፤ የቀጣይ ሦስት ወራትን እንደ ዘጠኝ ወር አድርጎ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
ለዚህም ከተለመደው አሰራር መውጣት፣ በርካታ ሥራ በአንድ ጊዜ ላቅ ባለ ደረጃ መከወን እራስንና ጊዜን ማሸነፍ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በርካታ የሰው ሀይል ፍላጎቶ እየመጣ መሆኑን የገለጹት ክብርት ሚኒስትር ፍላጎቱን በሚመጥን ደረጃ የበቃ የሰው ሀይል ለገበያው ማቅረብ ዋነኛው የዘርፉ ተልዕኮ ነው ብለዋል፡፡
የበቃ የሰው ሀይል በማቅረብ ሂደት ትልቅ እንቅፋት እየሆነ ያለው ከምዘና ጋር ተያይዞ የሚስተዋል ብልሹ አሰራር በመሆኑ ዘርፍን ሪፎርም ማድረግን ጨምሮ ይህንን ፈር የሚያሲዝ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
ዘርፉ ብቁ የሆኑ ሰልጣኞች እንዲያፈራ እና ለገበያው እንዲያቀርብ የዘንድሮ የሰልጣኝ ቅበላ አስቀድሞ ዝንባሌን በሳይኮሜትሪክ ምዘና በመለየት ለማሰልጠን ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

‹‹የአፍረካ ክህሎት ልማት ስትራቴጂ CTVET 2025- 34 ››

‹‹የአፍረካ ክህሎት ልማት ስትራቴጂ CTVET 2025- 34 ››
ከጥቅምት 3- 7/2018 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ዋና መ/ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የክህሎት ሳምንት መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክህሎት ልማትን በአፍሪካ ለማስፋት የተዘጋጀው ‹‹የአፍረካ ክህሎት ልማት ስትራቴጂ (CTVET) 2025- 34 ›› የማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል፡፡
የስትራቴጂውን ተግባራዊነት አስመልክቶ በተካሄደው ውይይት ሰነዱ ቀጣይነት ያለው እድገትና ማህበራዊ ፍትህ በአህጉሪቱ ለማረጋገጥ የቴክኒክና ሙያ ያለውን እምቅ አቅም በጥቅም ላይ ለማዋል የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የስትራቴጂው መዘጋጀት አፍሪካውያን በተለይም ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎችም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜው የሚፈልገውን ክህሎት እንዲላበሱ ብሎም የሥራውን ዓለም በስፋት እንዲቀላቀሉ ከማድረግ አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡
ስትራቴጂው ከ’አጀንዳ 2063′ እና ‘ከተባበሩት መንግስታት የልማት ግቦች’ ጋር በማጣጣም አካታችነትን፣ እኩል ተጠቃሚነትን እና ኢኖቬሽንን መሰረት ያደረገ ዕድገት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ተቀርጿል፡፡
በመሆንም የሀገራት ፖሊሲ፣ አስተዳደር፣ የፋይናንስ ስርዓት፣ ጥራትና አካታችነት ፣ አጋርነት፣ ዕውቀትና ሀብትን መጋራት በስትራቴጂው ውስጥ ልዩ ትኩረትየተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸው በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡
የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ፣ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የልማት አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ስትራቴጂውን ወደ ሥራ ከማስገባት ረገድ የየድርሻቸውን መወጣት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሥርዓትን በማሳደግ ዜጎችን ተገቢውን ክህሎት ማላበስ መጪው ጊዜ ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን በመልካም ዕድልና ተስፋ የተሞላ እንዲሆን የሚያስችል ቁልፍ አጀንዳ መሆኑም በውይይቱ ላይ በአፅንኦት ተነስቷል፡፡

Read More »
News

በሲዳማ ክልል ክህሎት መር የሥራ ዕድል

በሲዳማ ክልል ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አብርሃም ማርሻሎ ገለፁ።
አቶ አብርሃም የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ባካሄደው የዘርፍ ጉባኤ እንደገለጹት ወጣቶች ተወዳዳሪ በመሆንና የተሻለ ሀብት በመፍጠር ረገድ ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውንም ነው የገለጹት።
‎የአካባቢን የልማት አቅም በመለየትና ወጣቶችን በቂ ክህሎት በማስጨበጥ እሴት በሚጨምሩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ የሚሆኑበት መደላድል የመፍጠር ሥራው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በጉባኤው የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት እንደ ሀገር ብቁ የሰው ኃይል በማፍራትና ዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል በመፍጠር ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።
ክህሎት መር በሆነ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ እንዲሁም በተቋም ግንባታ ላይ የሪፎርም አጀንዳዎችን በመቅረጽ የተለያዩ ሥራዎች እተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በዚህም ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በአማካይ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ጠቅሰው፣ በቀጣይም ይህን ለማጠናከር ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
በሲዳማ ክልል ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሀገረፅዮን አበበ ከ2015 ዓ.ም በፊት የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው ክህሎትን ዋነኛ ትኩረት ያደረገ ባለመሆኑ በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት ሳይመዘገብ ቆይቷል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት አንድም ዜጋ ያለ በቂ ክህሎትና ሥልጠና ወደ ሥራ እንዳይገባ አቅጣጫ ተቀምጦ ሲሰራ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
ይህም ቀደም ሲል የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ላይ ይስተዋል የነበረው የውጤት ማጣት፣ የመበተን፣ የመሰላቸትና ሀብት መፍጠር ያለመቻል ችግር ተፈትቶ ውጤት መታየት መጀመሩን ገልጸዋል።
በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ ሥልጠና ከ30ሺህ በላይ እንዲሁም በአጫጭርና ገበያ ተኮር ሥልጠናዎች ከ61ሺህ በላይ ዜጎችን ማሰልጠን ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በሥልጠና ተቋማት፣ በአገልግሎት መስጫ እና በሥራ ማዕከላት ላይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥርዓትን በመዘርጋትም ዘርፉን የማዘመን ሥራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል።
በመድረኩ በተያዘው ዓመት በዘርፉ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ባለፈው በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማትና አጋር አካላት የዕውቅናና የማበረታቻ ሽልማት መሰጠቱን የገለፀው ኤዜአ ነው።

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top