Mols.gov.et

mols admin

News

በጅማ ከተማ አስተዳደር በትኩረት እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን …

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጅማ ከተማ አስተዳደር በትኩረት እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን ጎበኙ።
“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሼል ባህል እድገትና ምርታማነት!” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከናወነ ካለው የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት የአመቻችነት የአሰልጣኞች ሥልጠና ጎን ለጎን በከተማ መስተዳድሩ ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኤባ ገርባን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ መስተዳድሩ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Read More Âť
News

ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተቋም ለመገንባት…

“ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተቋም ለመገንባት ትጉህ እና ትሁት የሆነ አመራር ያስፈልጋል”
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
በውጤታማ አመራር ሰጪነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች ተሰጥቷል፡፡
ሥልጠናውን የሰጡት በአሜሪካን ሀገር በውጤታማ አመራር ሰጪነት (effective leadership) ላይ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ባላቸው አሰልጣኞች ነው፡፡
በሥልጠና መድረኩ ላይ የተሳተፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስተር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተቋም ለመገንባት ትጉህ እና ትሁት የሆነ አመራር ያስፈልጋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ከመሆኑም ባሻገር አገልግሎት የሚሰጡ አካላትንም የሚያሰለጥን በመሆኑ በየደረጃው ለዚህ ምላሽ መስጠት የሚችል አመራር ያስፈልጋል ብለዋል።

Read More Âť
News

ፀጋዎቻችንን አልምቶ ለመጠቀም…

ፀጋዎቻችንን አልምቶ ለመጠቀም…
ተቋማችን ፍላጎት፣ ብቃትና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶችን በማሰባሰብ ቴክኖሎጂ እንዲሰሩና የፈጠራ ሀሳባቸውን እንዲያዳብሩ በሚያስችለው መርሃግብር የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል ከማዕድን ሚንስትር ክቡር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል።
በውይይታችን የማዕድን ዘርፉ ጋር የተያያዙና የተጀመሩ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታን ተመልክተናል።
በክረምት ወራት የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያና የፈጠራ ሀሳቦች ማሻሻያ መርሃ ግብር የተሰሩ በማዕድን ልማት፣ በግብርና፣ በግንባታ ፣ በጤና እና በሌሎችም መስኮች የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎችን ጎብኝተናል፡፡
የማዕድን ሚንስትር ክቡር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ፀጋዎቻችንን አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችሉና በወጣቶቻች የተሰሩ ቴክናሎጂዎችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍና ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ሥራዎችን አልቆ ለማስቀጠል ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡

Read More Âť
News

የላቀ ስኬት ለዜጎች ተጠቃሚነት…

የላቀ ስኬት ለዜጎች ተጠቃሚነት….
የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የዜጎችን ድህንነትና ጥቅም በማስጠብቅ ህጋዊ የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ህጋዊ የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት ለዜጎች የተሻለ አማራጭ እንዲሆን የሚያስችሉ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆን ዜጎች ያለምንም እንግልት እንዲሁም ከፓስፖርት እና ከጤና ምርመራ ክፍያዎች ውጪ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ወደ ውጭ ሄደው ደህንነታቸው፣ መብታቸው እና ጥቅማቸው ተከብሮ መስራት የሚችሉበት ፈጣን አገልግሎት የሚያገኙበት በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል።
በመሆኑም በዘርፉ በማኑዋል አሰራር ይሰጥ ከነበረው አገልግሎት በወር ከ5.6 እጥፍ በላይ የዘረፉን አፈጻጸም ማሰደግ ተችሏል። ባለፈው በጀት ዓመት የነበረውን 127,000 ወደ ውጭ ሃገር የማሰማራት ከፍተኛ አፈጻጸም በያዘነው በጀት ዓመት ከ 144,000 በላይ ዜጎችን በ5 ወራት በማሰማራት በዘርፉ ሃገራችን ያላትን የሰራተኛ ስምሪት ታሪካዊ ቁጥር ከፍተኛውን ቁጥር ማሳካት ተችሏል። በዚህም በመካከለኛው ምስራቅ ከ14 ሃገራት በላይ ዜጎችን ለሥራ ከሚልኩ ሃገራት በ2ተኛ ደረጃ ላይ እንድንገኝ አድርጎናል፡፡
ከባለድርሻ አካላት ጋር በተፈጠረ ጠንካራ ቅንጅት፣ በሚንስቴር መስሪያቤቱ በተዘረጋው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአሰራር ስርዓት እንዲሁም በሚደረግ ክትትልና ድጋፍ በውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት በየወሩ እያደገ የሚገኝ አፈጻጸም እየተመዘገበ ይገኛል።

Read More Âť
News

ሁለተኛ ዙር Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB)…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሁለተኛ ዙር (Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB)) ውይይት ተካሄደ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ካውንስል አባላት በየወሩ ማለዳ 1፡00 ሰዓት ተገናኝተው ተቋማዊና አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ አፍላቂ ምክክር የሚያደርጉበት Innovation for Development Breakfast Meeting (I4DB) ሁለተኛ ዙር ውይይት ተካሄደ፡፡
በዕለቱ የኢንተርፕሪነርሺፕና የኢኖቬሽን ምህዳርን በማስፋት ረገድ መንግስትና የግሉ ዘርፍ ያላቸው ሚና እና በዚህ ረገድ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚያስችሉ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

Read More Âť
News

ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተወጣጡ…

ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸው በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ እና ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘውን የብየዳ ልህቀት ማዕከል እና በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችንና የሥራ እንቅስቃሴችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የሚዲያ ኃላፊዎቹም በጉብኝታቸው እና በተመለከቷቸው ሥራዎች መደሰታቸውንና በቀጣይ በጉዳዩ ላይ የባህሊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራዎችን እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

Read More Âť
News

“የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በኢንተርፕሪነርሺፕ …

“የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በኢንተርፕሪነርሺፕ እሳቤ የተቃኙ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየሠራን ነው።”
ክቡር ዶ/ር ተሸለ በሬቻ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን (Business Incubation Center) በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በማስፋፋት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በኢንተርፕሪነርሺፕ እሳቤ የተቃኙ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ችግርን ወደ ዕድል የመቀየርና አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው ሃሳቦችን የማፍለቅ አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ተግባራት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በማሰልጠኛ በተቋማት ውስጥ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን ማቋቋም አንደ አንድ ስልት የተወሰደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የኢንተርፕሪነርሺፕ ሥነ- ምህዳር በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ለማስፋት፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዕውን እንዲሆን ለማስቻል፣ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛና በቢዝነስ ተቋማት መካከል ትስስር ለመፍጠር እና ለምሩቃን ምቹ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላቱን መደገፍና ማሳደግ ወሳኝ ተግባር መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡
በቀጣይም ውጤታማ የሆኑ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በመላ አገሪቱ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለማስፋፋት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንጆይ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የቢዝነስ ማበልፀጊያ ማዕከላትን በማቋቋምና ውጤታማ በማድረግ አንፃር የተገኙ የተለያዩ ተሞክሮዎችና ማዕከላቱን በቀጣይ መስፋትና ማሳደግ የሚያስችሉ ገለፃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Read More Âť
News

የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ጥምረት… ለላቀ ስኬት !

የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ጥምረት… ለላቀ ስኬት !
የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት የዜጎቻችንን መብት፣ ደህንነትና ጥቅም በማስጠበቅ የሃገራችንን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የተጀመሩ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የወሩን አፈጻጸም ገምግመናል።
በዘርፉ የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጥን ሃገራችን በሰራተኛ ስምሪት ባለፉት አምስት ወራት ከ144,825 በላይ ዜጎችን ለስራ ወደ ውጪ ማሰማራት መቻሉ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑን እንዲሁም ለበርካታ ዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል አቅም መገንባቱን ተመልክተናል። በዚህም የተጀመሩ ስራዎች በጥሩ ደረጃ ላይ መሆናቸውን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የተጀመረውን ጠንካራ የቅንጅት ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ክቡር አምባሳደር ግርማ ለሥራው ውጤታማነት እያደረጉት ላሉት የቅርብ ክትትል እንዲሁም ርብርብ እያደረጉ ላሉ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

Read More Âť
News

ስምምነቱ ኢትዮጵያ በጋራ መልማትን …

” ስምምነቱ ኢትዮጵያ በጋራ መልማትን ያስቀደመች ሀገር መሆኗን ያረጋገጠ ነው”
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ምክንያት በማድረግ ደስታቸውን የገለጹበት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት የህዝብ ቁጥራችን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢኮኖሚያችንም ግዙፍ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ወደ መሆን እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡
ይህ በመሆኑም የቀይ ባህርንና የወደብ አስፈላጊነት አጀንዳ የህልውና ጉዳይ ሆኗል፡፡ መንግስት ለጉዳዩ ሌሎች እንደሚሉት በሀይል ሳይሆን ጥበብ በተሞላበት ዲፕሎማሲ እልባት ለመስጠት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ያደረጉት ስምምነት ለዘመናት ወደብ አልባ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለቀጣዩ ትውልድ ትርጉም ያለው የታሪክ እጥፋቶች መካከል አንዱ እንደሆነም ነው የጠቆሙት፡፡
በተገኘው ፍጹም ሰላማዊ እና የዲፕሎማሲያዊ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ክብርት ሚኒስትር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰጡት ጥበብ የተሞላበትና ቁርጠኛ አመራር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አሁን ላይ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ቢሆንም መነሻው ድህነት እንሆነ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከድህነት ጋር ያለንን ዝምድና ለማቆም ከመቼው ጊዜ በላይ መትጋት፣ መደማመጥ እና መከባበር የሚጠበቅብን ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ ለዚህም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

Read More Âť
News

የአብሮነት ሳምንት..

የአብሮነት ሳምንት (ከታህሳስ 20 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም)
በዓለም ለ26ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአብሮነት ቀን “ብዝሃነትን መኖር” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል፡፡
ለአምስት ተከታተይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግብር በህብረተሰቡ መካከል የመከባባር፣ መቻቻል፣ አብሮነት እና የሠላም ግንባታ አስተሳሰብ እንዲጎለብት የሚያስችሉ ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን በዓሉ አገራዊ አንድነትንና አብሮነትን በሚያጎላ መልኩ እንደሚከበር ተጠቁሟል።

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills