Mols.gov.et

mols admin

News

አዲሱ የጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ለሥራ ዕድል ፈጠራ

አዲሱ የጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ለሥራ ዕድል ፈጠራ አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር እና የዘርፉን ችግሮች በመቅረፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል።
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሰምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅንና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ ፖሊሲው ለዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር እና የዜጎችን ገቢ ትርጉም ባለው መልኩ ማሳደግ የሚያስችል ነው፡፡
የዘርፉ አዲሱ እሳቤ ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠርና ዳቦ በልተው እንዲያድሩ ከማድረግ የዘለለ መሆኑን ጠቁመው አዲሱ ፖሊሲ ይህንን ታሳቢ አድርጎ የተቀረጸ ነው ብለዋል።
በመድረኩ ፖሊሲውን ተከትለው የተዘጋጁ የሥራ ፈጠራ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የኢንተርኘራይዞች የኢኮኖሚ ቀውስ ጊዜ ምላሽ መስጫ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ እና ከፍተኛ የማደግ አቅም ያላቸው ኢንተርኘራይዞች ማበረታቻ ስርዓት ሰነዶች ለውይይት ቀርበው ተጨማሪ ግብዓት የሚሰባሰብበት ይሆናል፡፡

Read More »
News

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር…

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ ነው

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ኢኒሼቲቩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና የኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 5 ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ነው፡፡
ስልጠናውም በዋናነት በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
ከኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያው በተጓዳኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ኢኒሼቲቩ የትምህርት ዘርፉ ብቁ ትውልድ ለመገንባት በሚያከናውነው ስራ ላይ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል፡፡
በተለይ ትውልዱ በንድፈ ሃሳብ የሚያገኛቸውን እውቀቶች በቀላሉ ወደ ተግባር እንዲለውጥ ምቹ እድል በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው ቴክኖሎጂ ከስራ ፈጠራ ጋር የሚተሳሰር ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የወጣቶችን ዲጂታል አቅም ለመገንባት የተሰጠው ትኩረት ደግሞ ግብርናን ጨምሮ የተለያዩ መስኮችን ለማዘመን የተያዘውን ውጥን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው የተናገሩት፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስትን ወክለው በፓናሉ የተሳተፉት አብዱልአዚዝ አልጃዝሪ በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እውን በማደረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነት መኖሩን አንደታዘቡ ተናግረዋል፡፡
ይህ ደግሞ በኢኒሼቲቩ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
ቴክኖሎጂ የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በእጅጉ እየቀየረ ስለመሆኑ አንስተው፤ ከዚህ አኳያ ለዘርፉ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት አቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያብራሩት ደግሞ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
በእቅዱ ላይ ዲጂታል ክህሎትን መሰረት ያደረገ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት እንደተሰጠው ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም ይህን እውን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢኒሼቲቩ በኢትዮጵያ ክህሎት ያለው የሰው ሃይልን በመገንባት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአገልግሎቱ ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ዘመናዊና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እውን ማድረግ መንግስት እያከናወነ ያለው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች ዲጂታል ክህሎት ማደግ እንዳለበት ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያውን የሚያግዝ እንደሆነ ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Read More »
News

የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ግብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ግብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ

የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 እና 123/13 ለማሻሻል የሚያስችል የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ከውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲ ማህበራት ተወካዮች ጋር በሚኒስቴሩ አዳራሽ አካሄዷል፡፡
በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ዜጎች መብታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ አገር እንዲሰማሩ በማደረግ ዜጎችና እና ሀገራችን ከውጭ አገር ሥራ ሥምሪት የሚገባውን ጥቅም እንዲገኝ መሆኑን ገልጸው አሁን ሥራ ላይ ያለውን የዘርፉ አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት አሁን ካለንበት ጊዜ ጋር ሊያሰራ የሚችል ዘመናዊ ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት ያለመ ነው፡፡
የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት እንዲታገዝ በማድረግ እጅግ ውጤታማ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የሚሻሻለው አዋጅ ህጋዊ የስራ ስምሪቱን በማጠናከር የህገወጥ ሰዎች ዝውውርን በመግታት በኩልም ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አዋጁ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ሁሉ በውስጡ ያካተተ እንዲሆን ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉበት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Read More »
News

የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለፀ

የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር የሚመክርበት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና እና የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ የበለፀገ ማህበረሰብ እና ሀገር ለመገንባት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡
ከዚህ አንፃር ከስልጠና በላይ በሚል የክህሎት ልማት ዘርፉ አዲስ እሳቤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዜጎችን ክህሎት ከማስታጠቅ አልፈው የትምህርትና ሥልጠና ጥራቱን በሚያረጋግጥ መልኩ የተለያዩ ሥራዎችን እንዲሰሩ፤ ተኪ ምርቶችን እንዲያመርቱና ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እየተሰራ ያለው ሥራ እጅጉን የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉም ሚኒስቴሩ ሥራ ዕድል በመፍጠር ብቻ ሳይሆን ስነ-ምህዳሩንም ምቹ ከማድረግ እንዲሁም በሠላማዊ ኢንዱስትሪ ከመፍጠር አኳ እጅግ ወሳኝ የሚባሉ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዓመታት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል እና ሰላዊ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር በትኩረት ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡
የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር የተከበረው የምክርቤት አባላት ይህንን ከግምት በማሰገባት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያድጉ ጠይቀዋል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር በዘርፉ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች፤ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፤ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ረቂቅ ፖሊሲ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምክክር እያደረገ ይገኛል፡፡
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ የሰው ሃብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የተከበረው ምክር ቤት አባላትና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያና ኢራን በክህሎት ልማቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ኢራን በክህሎት ልማቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ክቡር አሊ አክባር ረዛኢ ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ በትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ የአቅም ግንባታ፣ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ጨምሮ ኢራን በዘርፉ ያላትን የካበት ልምድና ተሞክሮ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗ ተመላክቷል፡፡
ይህ ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እና የሀገራቱን ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል፡

Read More »
News

የሥራ ምህዳሩን ለማስፋት፣ ሁሉን አቀፍ ጥረት !

የሥራ ምህዳሩን ለማስፋት፣ ሁሉን አቀፍ ጥረት !
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ምቹ ምህዳር መፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ከእነዚህም ሥራዎች መካከል ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ሉሲ የተሰኘ የዲጂታል ሥርዓት በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ይህ ስርዓት በውስጥ አቅም በልጽጎ ወደ ሥራ የገባው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ውስጥ ከሚካተቱ 22 በላይ አገልግሎት መካከል አንዱ ሲሆን ለኢንተርፕራይዞች ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውና የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው፡፡
ስርዓቱ በበዓላት ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲሁም የሰንበት ገበያዎች ተወስኖ የነበረውን የኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎት የማስተዋወቅ ሥራን የሚያሳድግ እና ኢንተርፕራይዞቹ ወቅቱን የዋጁ የገበያ አማራጮች እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው፡፡
ከዲጂታል መሰረተ ልማቱ ጎን ለጎን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአይነቱ ልዩ የጥራት ሰርተፊኬት ያወጡና ከመላ ሀገሪቱ የተመረጡ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ የሚሸጡበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት የኢንተርፕራይዞች ህንፃ (Emporium) በመዲናችን አዲስ አበባ እያስገነባ ይገኛል፡፡
ይህ ስፍራ በከተማው አንዱ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆንም ታስቦ የሚገነባ ነው፡፡
ግንባታው አሁን የደረሰበትን ደረጃ ክብርት ሚኒስትር ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የጎበኘ ሲሆን ግንባታው በተያዘለት እቅድ በጥራት እንዲጠናቅ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Read More »
News

የዓለም የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ማህበር አባል መሆን የቻለው ኢኒስቲትዩት

የዓለም የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ማህበር አባል መሆን የቻለው ኢኒስቲትዩት
የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በማዘጋጀትና ከዘርፉ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር የስራ ትስስር በመፍጠርና ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ በበጀት ዓመቱ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑ ተገለፀ፡፡
የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 160 ከሚሆኑ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የሥራ ትስስር በመፍጠር በበጀት አመቱ ውጤታማ ስራዎችን መስራት ችሏል፡፡
በመደበኛ መርሃ-ግብር በደረጃ እና በዲግሪ ፐሮግራም ስልጠና መስጠት የሚያስችሉ 4 ኮርስ ካታሎግ ሲዘጋጅ ከዚህ ዉስጥ በቱሪዝም ማኔጅሜንት እና በሆቴል ማኔጅሜንት በዲግሪ መርሃ-ግብር በራስ አቅም ስልጠና ለመጀመር የስርዓተ-ትምህርት ክለሳ አድርጓል፡፡
የISO-21001:2018 የጥራት ሥራ አመራርን የተቋሙ አሰራር ማዕቀፍ አድርጎ በመዘርጋት ከሚመለከተዉ አካል እዉቅና ያገኘ ሲሆን ቴክኒካል ኮሚቴ እና አስፈጻሚ ግብረ-ሀይል በማቋቋም በተሰራው ስራ አፈጻጸሙን 86% ማድረስ ችሏል፡፡
የተቋሙ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በምግብና መጠጥ ዝግጅት፣ በቤት አያያዝ፣ በጉብኝት ሥራ እና በምግብና መጠጥ መስተንግዶ ላይ ትኩረት በማድረግ 11ኛዉ የክህሎትና የመስተንግዶ ሳምንት በድምቀት አካሂዷል፡፡
ተመራቂ ሰልጣኞችን ከአሰሪዎች ጋር ለማገናኘት አሰሪና ሰራተኛ የሚያገናኝ ጆብፌር ተዘጋጅቶ 40 የሚሆኑ የዘርፉ ተቋማት በመገኘታቸዉ ለምሩቃኑ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ለባህላዊ ምግብ ዝግጅት ልዩ ትኩረት በመስጠት በተለያዩ አካባቢዎች ከአስተዳደር አካላት እና ከልዩ ልዩ ብሄረሰብ አባላት ጋር በመቀናጀት የባህላዊ ምግቦች ተለይተዉ የምግብ አዘጋጃጀት ሰነድ የመቀመር ስራ ተሰርቷል፡፡
ባህላዊ ምግቦችን ወደ ኢንደስትሪዉ ለማሸጋገር ከባለ ኮከብ ሆቴሎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት በማድረግና የባህላዊ ምግብ ፌስቲቫል በማዘጋጀት ሆቴሎች አማራጭ የምግብ ሜኑ አድርገዉ እንዲጠቀሙበት እና በዚህ ዙሪያ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት አግባብ ላይ ሰፊ ግንዛቤ የማስረጽ ስራ ተሰርቷል፡፡
የማሰልጠኛ ተቋሙ ቀደም ብሎ ከዓለም ቱሪዝም ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እና ከጀርመን ልማት ባንክ ጋር መልካም ግንኙነት በመፍጠር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ደግሞ 175 አባላት ካሉት የዓለም የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ማህበር አባል መሆን ችሏል፡፡
በመሆኑም ከነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የመሰረተዉን ግንኙነት የስልጠና እና የምርምር አቅሙን ለማሳደግ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በምስራቅ አፍሪካ የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ልህቀት ማዕከል የመሆን ርዕዩን ለማሳካት እየተጋ ይገኛል፡፡

Read More »
News

የተዘጋጁት የአሰራር መመሪያ እና ደንቦች ተቋማቱ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያግዝ እንደሆነ ተገለፀ

የተዘጋጁት የአሰራር መመሪያ እና ደንቦች ተቋማቱ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያግዝ እንደሆነ ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለክህሎት ልማት ዘርፉ የተዘጋጁ ረቂቅ የአሰራር መመሪያ እና ደንቦች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተዘጋጁት ረቂቅ የአሰራር መመሪያና ደንቦች ተቋማቱ የሚሰጡትን አገልግሎት በማቀላጠፍ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ያስችላል ብለዋል፡፡
የተዘጋጁት ረቂቅ የአሰራር መመሪያና ደንቦች ዘርፉ ከተሰጠው አዲስ ተልዕኮ እና ሀገራዊ የአሠራር ስርዓቶ ጋር እንዲጣጣም በጥንቃቄ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Read More »
News

ፕሮጀክቶችን ወጥና ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ዲጂታል ሲስተም መልማቱ ተገለፀ

ፕሮጀክቶችን ወጥና ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ዲጂታል ሲስተም መልማቱ ተገለፀ፡፡
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ተልዕኮዎች ለማሳካት ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በትብብር የሚተገበሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሥር የሚገኙ ፕሮጀክቶቹን ወጥና ግልፅ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር እንዲቻል በሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ የለማው ሲስተም ላይ ገለጻ ተደርጎ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መከለያ በርጊቾ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፣ ፕሮጀክቶችን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ ለመምራትና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ይተገበራል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችል ዲጂታል የሆነ ወጥ የሆነ አሠራር መዘርጋቱ ስራዎችን ከማቀላጠፍና ግልፅነትን ከማስፈን ባለፈ የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም ከማላቅ አንፃር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የስትራተጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም አሥራት ጠቁመዋል:

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top