Mols.gov.et

mols admin

News

የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የክልሎችን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምን ግምገማን ቀጥሎ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የአማራ ክልል የዘርፉ እቅድ አፈፃፀምን ተመልክቷል፡፡
በመድረኩ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የማህበራዊ ጉዳይ እና የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ የሦስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ በዘርፉ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የተደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ ያለው የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት የመፍጠር ሥራ የተለየ አካሄድን፣ የክትትልና ድጋፍ ሥራን የሚጠይቅ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የተጀመሩ ስራዎችን ለማላቅ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ለክህሎት ልማት፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ድጋፎችን ለማመቻቸት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ እንደ ሀገር ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read More Âť
News

በድጅታል ክህሎት የሰለጠኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሴት ሰልጣኞች ተመረቁ

በድጅታል ክህሎት የሰለጠኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሴት ሰልጣኞች ተመረቁ፡፡
ስቴም ፓወር(STEM power) ከፊንላንድ ኤምባሲ እና ከ IBM SkillsBuild ጋር በመተባበር በጅታል ክህሎት ላይ ላለፉት ሶስት ወራት በኦንላየን ያሰለጠናቸው አንድ ሺህ ስልሳ ዘጠኝ(1069) ሴት ሰልጣኞች አስመርቋል፡፡
ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ የሚገኘው ስቴም ፓወር ትጋት ፕሮጀክት በሁለተኛ ዙር ፕሮግራሙ ያሰለጠናቸው እነዚህ ሴት ሰልጣኞቹ በሶፍትዌር ዲቨሎፕንት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI)፣ በሳይበር ሰኩሪቲ እና በዳታ ቤዝ የመሳሰሉ ድጅታል ክህሎቶች ላይ ስልጠናቸውን እንደተከታተሉ ተጠቁሟል፡፡
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፤ የድጅታል ክህሎት ዘርፍ እጅግ ውስብስብ፣ተገማች ያልሆነ፣ተለዋዋጭ፣ አሻሚ እና ድንበር የለሽ ቢሆንም ክህሎት እና እውቀትን ባልተቋረጠ መልኩ ማሻሻል ከተቻለ በሠፊ ዕድሎች የተሞላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዘርፉ ዕድሎች ለመጠቀም ልዩ ትጋት በሚጠይቀው በዚህ ስልጠና አልፈው ለተመረቁ ሴት ተመራቂዎችም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ተመራቂዎችም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባመቻቸው በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ተመዝግበው በሪሞት ጀብስ፣ በውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት እና በተለያዩ አማራጮች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ሰፊ ዕድል እንዳላቸው አማላክተዋል፡፡

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት …

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
በሩብ ዓመቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት በሚገመገሙበት በዚህ መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ እና የዘርፉ አመራርና ሰራተኞች እየተሳተፉ ይገኛል።
በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎች፣ የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር በመለየት የዘርፉን ዓመታዊ ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ የቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read More Âť
News

በተወዳዳሪዎች የቀረቡት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች…

በተወዳዳሪዎች የቀረቡት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን የሚያመላክቱ መሆኑ ተጠቆመ
የሴቶች ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
ለአስር ተከታታይ ቀናት በተካሄደው በዚህ ውድድር 37 ሴት የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ አስር ተወዳዳሪዎችም እያንዳንዳቸው የአንድ መቶ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ የሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ከሆኑት ሴቶች ተሳትፎ ውጭ የሚታሰብ አይደለም፡፡
በመሆኑም ሴቶችን በልዩነት ለመደገፍና ለማብቃት የሚስችሉ አሰራሮች በስፋት እየተተገበሩ ይገኛ፡፡በዚህም በዲጂታል ዓለም ላይ ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማጎልበትን መነሻ በማድረግ ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው፤ ተወዳዳሪዎች በኢኮሜርስ፣ በትምህርት፣ በጤና በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ይዘው የቀረቧቸው ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ማሳያ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ እየተከተለች ያለችው ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ዲጂታላይዜሽንን የሚያበረታታ መሆኑ በዘርፉ ለተሰማሩ ዜጎች መልካም አጋጣሚ ነው፡፡
ሴቶች የዘርፉን ተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማችና ድንበር የለሽ ባህሪ በመረዳት ራሳቸውን ብቁ አድርገው ለመገኘት መትጋት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
ከተናጠል ይልቅ በጋራ አቅምን አስተባብሮ መስራት ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ቁልፍ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማሳደግ የሚያስችላቸውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
ውድድሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት፣ ከኔስት ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ፣ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅትና ሌሎችም አጋር አካላት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

Read More Âť
News

የተናበበ ትብብር- የተጠናከረ አጋርነት

የተናበበ ትብብር- የተጠናከረ አጋርነት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የሥራ ኃላፊዎችና የፕሮግራም አስተባባሪዎች ጋር በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተከናወኑ አበይት ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም የዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎችን የሚያመላክት ሰነድ በክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ቀርጓል፡፡
በዚህም በሦስት ዓመታት ውስጥ በሀገር ውስጥ ከ9 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር በውስጥ አቅም ለምቶ ወደ ሥራ በገባው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት ከ517 ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል መፈጠሩ ጠቁመዋል፡፡
ዜጎች ከሀገራቸው ሳይወጡ በውጭ ሀገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት የርቀት የሥራ ዕድል 83ሺ ለሚሆኑ ዜጎች መፈጠሩንና 26ሺ ያህሉ በተጨባጭ ወደ ሥራ መግባታቸውን አንስተዋል፡፡
አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን የዲጂታል አማራጮችን ጭምር በመጠቀም የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኢምፖሪየም ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
የኢንተርፕረነርሺፕ ልማትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ችግር የሚፈቱ ሚሊዮን ኢንተርፕሪነሮችን ለማፍራት የሚያስችል ሥርዓት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተዘረጋ እንደሚገኝም ነው ክብርት ሚኒስትር የገለጹት፡፡
በክህሎት ልማት ረገድ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በሰጠው ልዩ ትኩረት 7.2 ሚሊዮን ዜጎችን በአጫጭር ስልጠና ማብቃት መቻሉንም ክብርት ሚኒስትር አስረድተዋል፡፡
በልምድ የክህሎት ባለቤት የሆኑ ዜጎችን በማብቃትና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ፕሮግራም በይፋ መጀመሩን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ፕሮግራሙ ‹‹አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ›› በሚል መሪ ቃል ዜጎችን ለማብቃት የተያዘውን ዕቅድ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
የተቋማዊ ግንባታ ሥራውን ጥራት ለማረጋገጥ እንዲቻልም በሚኒስትር መ/ቤቱ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራርን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝም በመድረኩ ተብራርቷል፡፡
በዚህ መልኩ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮግራሞችን ከሚኒስትር መ/ቤቱ እሳቤ ጋር የተቀናጀ እንዲሆኑ ለማስቻል ብሎም በተጨማሪ መስኮች ላይ ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

Read More Âť
News

‹‹የሴት ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን›› ውድድር

‹‹የሴት ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን›› ውድድር
ወጣት ሴቶች የሚሳተፉበት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን የፈጠራ ሃሳብ ውድድሩ መስከረም 28ቀን 2017 መጀመሩ ይታወቃል ፡፡
ውድድሩ ወጣት ሴቶች የፈጠራ ዕምቅ አቅማቸውን ተጠቅመው የማህበረሰባቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ማመንጨት የሚያስችላቸውን ዕድል ለመፍጠር ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ‹‹ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን›› በሚል ስያሜ ላለፉት 9 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ለተወዳዳሪዎቹ የአንተርፕሪነርሺፕ ስልጠና የተሠጠ ሲሆን የመወዳደሪያ ሀሳብና ስራዎቻቸውን ያቀረቡበት የእንዲሁም ልምድና ተሞክሮ ያገኙበት መርሃ ግብሮች ተካሂዷል፡፡
ውድድር በነገው ዕለት ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን የውድድሩ አስር አሸናፊዎች የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ላይ ይገኛል።
በዘርፉ ደረጃ እየተደረገ በሚገኘው የግምገማ መድረክ የሥራና ከሀሎት ሚኒስትር ክብረት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የሥራና ከሀሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምረትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት 4.2 ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥ እንዲሁም 700 ሺህ ደግሞ በውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የአካል ጉዳተኞችንና…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የአካል ጉዳተኞችንና የሌሎችም የጋላጭ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተያዙ ዕቅዶችን ለማናበብ የሚያስችል የውይይት መድረክ ከተጠሪና ከክልል የዘርፉ አስፈፃሚ ተቋማት ጋር ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት መነን መለሰ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማትና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፎች የሚስፈፅማቸው ተልዕኮዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከቱ እንደመሆናቸው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚታቀዱ ዕቅዶች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ማካተታቸውን የማረጋገጥ ሥራ በቋሚነት እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመደበኛ ዕቅዶቹ ከሚያስፈፅማቸው ተልዕኮዎቹ ጎን ለጎን በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎቹ በሶማሌ ክልል የመማሪያ ክፍሎችንና ግንባታና የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤት የማደስ ሥራ ማከናወኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በአዲስ አበባ ከተማ 54 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ባለ አራት ወለል ህንፃ የመኖሪያ ቤት አስገንብቶ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከቡንም ገልፀዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪና የክልል የዘርፉ አስፈፃሚ ተቋማት ከህብረተሰቡ ጋር በቀጥታ የሚገናኙ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ የዘርፉን አካታችነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ጉዳዮችን በጥናት ከመለየት፣ በዕቅድ ከማካተትና ከማስተግበር አንፃር ያሉበትን ደረጃ ለመፈተሸና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሃንስ በበኩላቸው ከጠቅላላው የሀገራችን የህዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ ድርሻ ያላቸውን ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ያላካተተ ማንኛውም ሀገራዊ ዕቅድ የዜጎችን ሙሉ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ስለማይጠበቅ በየደረጃው ያሉ የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት ዕቅዳቸውንና አፈፃፀማቸውን በየጊዜው መፈተሽና የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የላቀ ጥረት ማድረግ እንደሚኖርባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Read More Âť
News

ስምምነቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል

ስምምቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከቬክና ቴክኖሎጂ እና ከኦርቢት ሄልዝ ጋር በመተባበር ዲጂታላይዝ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ ‹‹ብራት ቦክስ›› የተሰኘ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በማምረት በገጠር አካባቢዎች ዲጂታላይዝ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ አምራችነት የሚሸጋግር እና አዳዲስ ዕውቀትንና ክህሎትን ለመታጠቅ ያስችላል፡፡
ይህም በሂደቱ ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የሥምምነቱ ተግባራዊነት በጤና ቴክሎጂ ምርት፣ በሮቦቲክስና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ብቁ የሰው ኃይል ለማልማት የሚያስችል ዕድልን የሚፈጥር መሆኑም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡

Read More Âť
News

የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክርን በመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ለማስጀመር የሚያስችል የአስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክርን በመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ለማስጀመር የሚያስችል የአስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን ለማጠናከር ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ምክክሮችን ማካሄድ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምክክር በኢንዱስትሪዎች ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚያግዝ ዋነኛ ስልት እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ምቹ የሥራ አካባቢን ከማረጋገጥ አንስቶ ምርታማነትን በማሳደግ በሀገር ቀጣይ እድገት ላይ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል አዲስ እሳቤ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ማኀበረሰብ የምርታማነት ምክክር የሚመረበት ማንዋል በማዘጋጀት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልሎች በተመረጡ ተቋማት ለአመቻቾችና አስተባባሪዎች ስልጠና መስጠቱ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አዲስ እሳቤን እና የኢንዱስትሪ ማህበረሰብ ምክክር የሚመራበት ማስፈፀሚያ ማኑዋልን የተመለከቱ ገለፃዎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top