Mols.gov.et

mols admin

News

ዕምቅ አቅሞችን በራስ አቅም …

ዕምቅ አቅሞችን በራስ አቅም …

የጎለበተ ህዝባዊ የሥራ ፈጠራ ባህል መዳበር የስራ ተነሳሽነትን ከማሳደጉም ባለፈ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ዘላቂ ልማትና ሰላም ለማምጣት ትልቅ አሻራ ይኖረዋል::
ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በያዘው የክልል አቅም ግንባታ ፕሮግራም አካል በሆነው ጥምረት በተጠሪ ተቋሙ የኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት በኩል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራር በአዲስ እሳቤ ህዝብ-መር የሥራ ባህል ንቅናቄን በመፍጠር የክልሉን ፀጋ አልምቶ የሀገር ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያለመ የፐብሊክ ሴክተር ኢተርፕሩነርሺፕ ፕሮግራም አስጀምረናል::
ስልጠናው የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብን ለማስረጽ እና የፈጠራ ባህልን ለማሳደግ ውጤታማ የጎንዮሽ ትስስር እንዲሁም የአመራር እና ህዝብ አሻግሮ የጋራ ግብን የማየትና ቅንጅት የመፍጠር አስፈላጊነትን በአንክሮ ያስገነዘበ ነው::
የኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን እና ባልደረቦቻቸው ይህንን አይን ገላጭና የራስ ዕምቅ አቅምን ተጠቅሞ ሀብት የማፍራት፤ ከራስ አልፎ የሀገር ምሰሶ መሆን የመቻል መንገድን የሚያመላክት፤ የሥራ ፈጠራ ክህሎትን የሚያዳብር እና የሚያነሳሳ ስልጠና ለክልሉ አመራር እንዲደርስ በማድረጋቸው ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው::
የቤንሻንጉል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሌ ሀሰን ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ካቢኔያቸውን አስተባብረው በስልጠናው ተሳታፊ በመሆናቸው እንዲሁም የክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በአትኩሮት ለመስራት ለሰጡት አመራርና ላሳዩት ቁርጠኝነት ላቅ ያለ አድናቆቴና ምስጋናዬ ይድረሳቸው::

Read More Âť
News

“ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም…

“ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የወጣቶችን የሥራ ብቃትና ተነሳሽነት ለማጎልበት የሚያስችሉ በርካታ ተሞክሮዎች ተገኝተውበታል፡፡”

ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

‹‹ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› ሁለተኛ ዙር ትግበራ በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ተጀመሯል፡፡
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራሙ ወጣቶች በሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አቅም ከመገንባት አንፃር በርካታ ተሞክሮዎች ተገኝተውበታል ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙ በአንደኛ ዙር ትግበራ በአስር ከተሞች ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን ከነዚሁ ከተማ አንዱ በሆነው የወላይታ ሶዶ ከተማ የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መንግስትና የግሉ ዘርፍ ተቀራርበው ከሠሩ ለወጣቶች ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ማመቻቸት እንደሚቻል በተጨባጭ መስተዋሉንም አስረድተዋል፡፡
ወጣቶቹ የሥራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ ዕድል ያመቻቹ የግል ተቋማት ባለቤቶች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ከመወጣት አንፃር ላበረከቱት ሚና ያላቸውን ምስጋና ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በመድረኩ ገልፀዋል፡፡
ሁለተኛውን ዙር የፕሮግራሙን አፈፃፀም በተሻለ ሁኔታ ማሳካት እንዲቻልም የሚመለከታችው መንግስታዊ አካላት ሁሉ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡም አሳስበዋል፡፡
በወላይታ ሶዶ ከተማ ሲተገበር በቆየው አንደኛው ዙር ‹‹ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› ተሳታፊ ከነበሩ 396 ወጣቶች መካከል 384 ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

Read More Âť
News

“መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን አዲስ ገፅ ለዓለም ለመግለጥ የሚያስችል ነው፡፡“

“መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን አዲስ ገፅ ለዓለም ለመግለጥ የሚያስችል ነው፡፡“
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የ2024 ግሎባል የአፍሪካ የስታርትአፕ ሽልማት መድረክን በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንተርፕሪነርሺፕ ኢንስቲትዩት መርሃ ግብሩን ከሚያዘጋጀው ግሎባል ኢኖቬሽን ኢንሸየቲቭ ግሩፕ ጋር ነው የተፈራረመው፡፡
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልክዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ ሃሳብ ማመንጨት የሚችሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ያሉባት አገር መሆኗን በመጥቀስ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን አዲስ ገፅ ለዓለም ለመግለጥ የሚያስችል ነው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንተርፕሪነርሺፕና ኢኖቬሽን ምህዳርን ለማስፋት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃ፡፡
መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና የፋይናንስ ተቋማትን በአንድ ላይ በማሰባሰብ በተፈጠረው ኔስት (NEST) በተሰኘው ስርዓት አማካኝነት ለኢንተርፕሪነሮች ምቹ መደላድል ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል ብለዋል ክብርት ሚንስትሯ፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ መልክ ለኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት የሰጠችው ትኩረት የአፍሪካ ስታርታፕ የሽልማት መድረክን ለማዘጋጀት እንዳስመረጣትም ነው ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የገለጹት፡፡
ከዚህ መልካም አጋጣሚ በርካታ ስታርታፕ ቢዝነሶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባው የጠቆሙት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአህጉርና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ላይ ቀርበው ተሸላሚ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሞክሯቸውን ለመሰል ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እንዲያካፍሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Read More Âť
News

የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ልየታ…

የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ልየታ፣ በሂደት ላይ ያሉ የሁለትዮሽ የሥራ ስምምነቶችን ማጠናቀቅ እና የተፈረሙትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቆመ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓመታዊ የአምባሳደሮች ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተገኝተው እየተከናወነ ባለው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና የክህሎት ልማት ስራዎች እንዲሁም ዘርፉን ለማዘመን የተዘረጋው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ልየታ፣ በሂደት ላይ ያሉ የሁለትዮሽ የሥራ ስምምነቶችን ማጠናቀቅ እና የተፈረሙትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ ገልፀዋል፡፡
ዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የአቅም ማጎልበቻ መርሃ ግብሮችን በማመቻቸት ረገድ ከሚስዮንዎቹ ብዙ እንደሚጠበቅም ነው ክብርት ሚኒስትር የጠቆሙት፡፡

Read More Âť
News

የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ተጀመረ

የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ተጀመረ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በአሥር ከተሞች ላይ የሚተገብረው ‹‹ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም›› ሁለተኛ ዙር ትግበራ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የሥራ ፣ የሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በሁለተኛው ዙር ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ ወጣቶች በሥራ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ ከመሆን አንፃር የለባቸውን ክፍተት የሚሞላ የሥራ ላይ ልምምድ አድርገው የቅጥር ሥራ እንዲያገኙ ለማስቻል ተግባራዊ የተደረገ ፕሮግራም ነው›› ብለዋል፡፡
ወጣቶችን በአመለካከትና በክህሎት በመቅረፅ በቅጥር ሥራ ላይ እንዲሠማሩ ከማስቻል አንፃር በአንደኛው ዙር የፕሮግራሙ አፈፃፀም በርካታ ተሞክሮዎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከዚህ አንፃር በሁለተኛው ዙር የፕሮግራሙ ትግበራ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል፡፡
የፕሮግራሙን ተጠቃሚዎችን በአግባቡ ከመመዝገብ፣ ሥልጠናውና የሥራ ላይ ልምምዱ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ተግባራዊ መደረጉን በንቃት ከመከታተልና የሥራ ላይ ልምምድ ያደረጉ ወጣቶች በቅጥር ሥራ ላይ እንዲሠማሩ ተገቢውን ርብርብ ከማድረግ አንፃር ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ክቡር አቶ ንጉሡ በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡
በአንደኛው ዙር የፕሮግራሙ ትግበራ የሥራ ላይ ልምምድ ላደረጉ 12, 452 ወጣቶች የቅጥር ሥራ በማመቻቸት የዕቅዱን 93 በመቶ ማሳካት የተቻለ መሆኑ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በሁለተኛው ዙር የፕሮግራሙ ትግበራ 23, 773 ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ አድርገው በቅጥር ሥራ ላይ እንዲሠማሩ የሚያስችል ዕቅድ መያዙም ተገልጿል፡፡

Read More Âť
News

በአቪየሽን እንዱስትሪው ያለንን ተወዳዳሪነት ለማላቅ…

የኢትዮጵ አየር መንገድ ሃገራችን በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ ያስቻለ የስኬት ገፅ እና የመላው አፍሪካውያን ኩራት ነው።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬቶች ጋር አብሮ የሚነሳው የአቪየሽን ማሰልጠኛ በርካታ ባለሙያዎችን በማፍራት ሃገራችን በአቪየሽን እንዱስትሪው አንፀባራቂ ታሪክ እንድታስመዘግብ ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡
ብቁ የአቪየሽን ባለሙዎችን በማፍራት ይህንን የአገራችን የአቪየሽን እንዱስትሪ ስኬት ለማስቀጠል የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና መንክር አቪየሽን ኮንሰልታንሲ ‹‹ኢሮ ክለብ›› በሚል ጥላ ሥር በመሰባሰብ በጋራ የፈረምነው የመግባቢያ ሰነድ አየር መንገዳችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ሥኬት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፤ ብቁ፣ በቂ እና ተወዳዳሪ ሙያተኞችን ለማፍራት ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የመንክር አቪየሽን ኮንሰልታንሲ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በአቪየሽን እንዱስትሪው ያለንን ተወዳዳሪነታችንን ለማላቅ በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ላሳያችሁት ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

Read More Âť
News

“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሼል ባህል እድገትና ምርታማነት!”

“የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሼል ባህል እድገትና ምርታማነት!”
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በየደረጃው ለሚያካሂደው የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ያዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር የአመቻችነት የአሰልጣኞች ሥልጠና መድረክ በጅማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ ከ400 በላይ ሰልጣኞች እየተሳተፉበት ይገኛል።

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills