
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የለውጥ ሥራው ላይ ውይይት ማድረግ ጀምረዋል፡፡
በመድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራዎች የተግባር ምዕራፍ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በስኬት ማጠናቁን አውስተው ይህን ስኬት ያለሠራተኛው ንቁ ተሳትፎና ርብርብ ማምጣት አይቻልም ነበር ብለዋል፡፡
ሥራው ሀገርን የመገንባት ጉዞ አንዱ አካል በመሆኑ ለብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይዞ መውጣት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ሁሉም ይህን ተገንዝቦ የትግበራ ምዕራፉን እቅድ በማዳበር በባለቤትነት አልቆ ለመፈፀም መዘጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የውይይት መድረክ በመደበኛውና የሪፎርም ሥራዎች የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ነገም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡








