Mols.gov.et

bini

News

‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም››

ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተሰታፊ የሆነበት የሴቶችና የወጣቶች የፋይናንስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም›› በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ፎረሙ አፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶች በፍጥነት እያደገ ከሚገኘው ከዲጂታል ኢኮኖሚ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ በዋነኝነት በማተኮር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Read More »
News

በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማትን አስፍቶ መተግበር ይገባል- ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማትን አስፍቶ መተግበር ይገባል-
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
በአፋር ክልል እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማት አስፍቶ መተግበር እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አሳሰቡ።
በሚኒስትሯ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ አሮሮ ላፍ ቀበሌ የሚገኘውን የእንሰሳት መኖ ልማት ምልከታ አከናውኗል።
በወቅቱም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንዳሉት በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማት አስፍቶ መተግበር ይገባል።
ክልሉ በእንስሳት መኖ ልማት ረገድ እምቅ ሃብት ያለው መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀው፥ እንደ አገር የወተት ልማት ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ የሚኖረው ሚና የጎላ በመሆኑ በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ መናገራቸውን የኢዜአ መረጃ ያመለከታል፡፡

Read More »
News

በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአፋር ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በመመልከት ላይ ናቸው፡፡
በመስክ ምልከታው ኪልበቲ ረሱ አፍዴራ ወረዳ የጨው ፋብሪካዎችንና የአፍዴራ የጨው ሀይቅን ጨምሮ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ላይ ክብርት ሚኒስትር ባስተላለፉት መልዕክት ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ሀብት እና የቱሪዝም መስህቦች እንዳሉት ጠቅሰው ይህን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል ብለዋል፡፡
እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ የማዕድንና የቱሪዝም ዘርፉን ጨምሮ የክልሉ የልማት አቅሞች ለበርካታ የክልሉ ወጣቶች ሥራ መፍጠር እንደሚያስችሉ ጠቅሰዋል፡፡
ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የልማት ሥራዎችን የበለጠ ማስፋት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም የባለድርሻ እና አስፈፃሚ አካላት በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ያሳሰቡት ክብርት ሚኒስትር ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን መጠቀም እንደሚገባም ገልፀዋል
ከልማት ሥራዎቹ ከጉብኝት በኋላም ከወረዳዎች፣ ዞኖችና የክልሉ አመራርና የህብረተሠብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።

Read More »
News

ሚኒስቴሩ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል አስተዳዳር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ

ሚኒስቴሩ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል አስተዳዳር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ከተወካዮቹ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ዘርፍ በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ መካከል የተፈረመውን የሁለትዮሽ ስምምነት አተገባበርና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዓላማው ባደረገው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ስልጠናና ምዘና ድረስ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ አብራርተዋል፡፡
ሥራውን ይበልጥ ለማዘመንና ከብልሹ አሰራር በማጽዳት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለሥራ ገበያው ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴታው ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል አስተዳዳር ተወካዮች ጋር የተጀመረው ተቀራርቦ የመስራት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያ ተወካዮች በበኩላቸው እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን አድንቀው ከመነሻ እስከ መዳረሻ ድረስ ያለውን ሂደት ጤናማ በማድረግ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

Read More »
News

ኢንስቲትዩቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ተጠቆመ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኢኒስቲትዩቱ ለሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በሥልጠናው የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት፤ የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ተወዳዳሪና የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን በዚህ መሰረትም ኢኒስቲትዩቱ እስካሁን ለበርካታ ዜጎች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠት ችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ላለው የሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
በስልጠናው ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች እንደተካፈሉም ገልፀዋል፡፡
በዚህ በጀት አመት 150 ሰልጣኞች በሦስት ዙሮች የሰለጠኑ ሲሆን የተሰጠው ሥልጠና በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በምግብ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር መሆኑንና ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን ስልጠና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ አመራሮች ጠቁመዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሥልጠና እና የተቋማት አቅም ግንባታ ዴስክ ሀላፊ አቶ ተመስገን በቀለ በሦስተኛው ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስልጠናውን ያገኙ አሰልጣኞች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ እንደሀገር የተሰጣቸውን ኃለፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

Read More »
News

ኢንስቲትዩቱ ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀመረ

ኢንስቲትዩቱ ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀመረ
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድርን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት የቴክኒክና ሚያ ሥርዓቱን አካታች ማድረግ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ውስጥ ሁሉም ዜጎች ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ሥራ ያስጀመርነው ይህ ማዕከል ኢንስቲትዩቱ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሥልጠና ማዕከል ለመሆን ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ እንደሆነም ገልፀዋል።
በኢንስቲትዩቱ ውስጥ አካል ጉዳተኝነት ከውጤታማነት ያላገዳቸው አሠልጣኞች፣ ተመራማሪዎች እና ቴክኖሎጂስቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡
በትምህርትና ሥልጠናው መስክ ማዕከሉ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ከሌሎች ልምድና ተሞክሮዎችን የሚቀስሙበት ቦታም እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከልና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከልና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለዜጎች ሰፊ ሥራ ዕድልን ለመፍጠር በሚያስችሉ አማራጮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት ዲጂታል ኢኮኖሚን በመጠቀም ዘላቂ ልማትንና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ሀገራችን ‹‹ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025›› ግብን ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል፡፡
የዲጂታላይዜሽን ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የዜጎችን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት ያለውን አስተዋፅኦ መነሻ በማድረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዲጂታል ኢንተርፕሪነርሺፕ እንቅስቃሴን መጀመሩን የገለፁት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባለማው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት ቁጥራቸው ከ26ሺ ለሚልቁ ዜጎች የርቀት ሥራ(remote job) መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2023 የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰዎች ከሀገራቸው ሳይወጡ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የሥራ መስኮች ላይ መሰማራት በሚያስችለው የአውትሶርሲንግ ቢዝነስ ከ1.2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ መንቀሳቀሱ ዘርፉ ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ያለውን አቅም የሚያመላክት መሆኑም ተብራርቷል፡፡
ዘርፉ አዲስ እንደመሆኑ በሚጠበቀው ደረጃ ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና የአሠራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ምህዳሩን ምቹ ከማድረግ አንፃር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ ኢንተርፕረነሮችና ወጣቶችን ከአሠሪዎች የሚያግናኙ የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም አልሚዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በጊግ ኢኮኖሚ የቁርጥ ሥራ እና ፍሪላንሲንግ ኢንዱስትሪ ላይ በሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከልን ጎበኙ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከልን ጎበኙ
የክህሎት ልማት ሥራችን በሥራ ገበያው ፍላጎት ጀምሮ በሙያ ብቃት ምዘና የሚጠቃለል ነው፡፡
በመሆኑም ከክህሎት ስልጠናው ባልተናነሰ መልኩ ወደ ሥራ ገበያው የሚቀላቀለው የሰው ሃይል ብቃቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የምዘና ስርዓቱ ወቅቱን በዋጀ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ እና ቀጣሪ ድርጅቶችም ለሚሰጠው የምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ዋጋ እንዲሰጡት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያውን ለመጠቀም በምናደርገው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ተቋማት የሚሰጡት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ወሳኝ በመሆኑ እነዚህ ተቋማት ለዜጎቻችን ተደራሽ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በዚህም ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከል ዓለም አቀፍ እውቅና ካላቸው የምዘና ተቋማት ጋር በመተባበር የከፈተውን የምዘና ማዕከል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጎብኝተዋል፡፡
ከማዕከሉ የሥራ አመራሮች ጋር በምዘና፣ ስልጠናና እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያም ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ ማዕከሉ በዚህ መልኩ ሥራ መጀመሩ በውጭ ሀገር ያሉ የሥራ ዕድሎችን ከማስፋት ባሻገር በትምህርትና ሥልጠናው መስክ ሙያዊ እድገትንና የዕድሜ ልክ ትምህርትን የሚያበረታታ እንዲሁም እንደ ሀገር ያለንን ተወዳዳሪነትን የሚጨምር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በመስኩ የግሉ ዘርፍ ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል::

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top