Mols.gov.et

ስምምነቱ የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የመመህራን አቅም በማጎልበት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

February 2, 2023
ስምምነቱ የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የመመህራን አቅም በማጎልበት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቻይና አፍሪካ የሙያ ትምህርት ትብብር( CHINA-AFRICA VOCATIONAL EDUCATION ALLIANCE) ጋር የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ማላቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ፊርማ ተፈራርመዋል፡፡ የስምምነት ሰነድ ፊርማ የተፈራረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) እና የቻይና አፍሪካ የሙያና ትምህርት ትብብርን ወክለዉ ማርክ ጎንግ(ዶ/ር) ናቸዉ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በፊርማ ስነ-ስራት ወቅት፤ ስምምነቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለዉን ትብብር ይበልጥ የሚያሳድግ እና በጋራ አብሮ መስራት ያሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቻይና መንግስት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሰፊ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይህ ስምምነትም የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የመመህራን አቅም በማጎልበት፣ የ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልምድ መለዋወጥ እና በሌሎችም ዘርፎች አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የቻይና አፍሪካ የሙያ ትምህርት ትብብርን ወክለዉ ንግግር ያደረጉ ማርክ ጎንግ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ ቻይና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና በእጅጉ መጠቀሟን ገልጸዉ ልምዷን ደግሞ ለኢትዮጵያ ለማካፈል እና በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ጥር 8/2015 ፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡ ለወቅታዊን ትኩስ የሥራና ክህሎት መረጃዎች ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols በመወዳጀት ይከታተሉን::
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills