Mols.gov.et

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየዘረጋ መሆኑ ተጠቆመ።

February 2, 2023
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየዘረጋ መሆኑ ተጠቆመ። በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ምክክርና ጉብኝት አካሂደዋል። አምሳደሮቹ በተቋሙ መሰረታዊና ለውጥ አምጪ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ የዜጐችን ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። በመድረኩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየተዘረጋ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጠቁመዋል።
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills