Mols.gov.et

bini

News

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤ ከማሰልጠንና ዳቦ በልቶ ከማደር ያለፈ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል በመገንባት ምርታማነትን መጨመር እና ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር ነው

ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ዘላቂ ጉዞን በአዲስ አስተሳሰብ መቃኘትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ጀምረዋል።
በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሀገረ መንግስት እና የሀገረ ብሔር ግንባታ ችግሮችን አበይት ተግዳሮቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሀገረ መንግስት ግንባታ በዋናነት ነፃና ገለልተኛ ተቋማት መገንባትን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ተቋማትን የስርዓት ሳይሆን የዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የለውጡ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ሀገርና ህዝብ ዘመን ተሻጋሪ በመሆናቸው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ገልፀዋል።
ሀገር እና ህዝብን ማዕከል በማድረግ በተሰሩ ሥራዎች ሩቅ የነበሩ ተቋማትን ማቅረብ መቻሉን የተናገሩት ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት የሰው ኃይልን ዝግጁ አድርጎ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ምን አይነት መዋቅራዊ ችግርን መፍታት ይጠበቃል ለሚለው መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ሀገር ወዳድ እና ዝግጁ ትውልድ መገንባትም ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ሲገልፁ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከማሰልጠንና ዳቦ በልቶ ከማደር ያለፈ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል በመገንባት ምርታማነትን መጨመር እና ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር ነው ብለዋል ።

Read More »
News

“የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለቁመና በመመልከታችን ተደስተናል።”

“የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለቁመና በመመልከታችን ተደስተናል።”
ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር)
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፎች ከደህንነት ተቋማት ጋር መስራትን መሰረት ያደረገ ጉብኝት አካሂዷል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዋናውን መስሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የመከላከያ ዋናው መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያውያን አልፎ አፍሪካውያንን የሚሰበስብ የሁሉም ቤት ነው።
ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት እና በሥራ ቦታ ደህንነት በለየናቸው መስኮች ጠንካራ ሥራዎችን በጋራ መስራት ጀምረናል ያሉት ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለ ቁመና በመመልከታችን ተደስተናል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሠራተኞችም ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በታጠቀው እና የኢትዮጵያን ልክ በሚያሳይ መልኩ በተደራጀው መከላከያ ሠራዊት ዋና መስሪያ ቤት ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

Read More »

ኢትዮጵያ ትሰራለች

#Ahun Round 2 High Growth Digital Startups Incubation Program

Ministry of Labor and Skills in collaboration with the UNDP invites digital startups with innovative business solutions for the #Ahun2022 round 2 call.

Read More »
Announcements

Call for application

#Ahun Round 2 High Growth Digital Startups Incubation Program
Ministry of Labor and Skills in collaboration with the UNDP invites digital startups with innovative business solutions for the #Ahun2022 round 2 call.
#Ahun is a 4-month incubation program for digital business ideas to be incubated and secure a seed funding.
Please follow the link to apply: https://enkopa.org/high-growth/
Or use P.O. Box 25534
Application Deadline: July 31, 2022

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገልግሎቱን ለማዘመን ያደረገውን ዝግጅት ለተለያዩ ዘርፎች የክልል አመራሮች አስጎበኘ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች ተቋሙ የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ በማድረግ ለአገልግሎት ምቹ የሆነውን ህንፃ እና ያበለፀጋቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለክልል አመራሮች እና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች አስጎብኝቷል።
በአዲስ አበባ በተለምዶ ላምበረት በሚባለው አካባቢ ከዚህ ቀደም ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ሲገለገልበት የነበረውን ሕንፃ ለሥራው በሚመች መልኩ መዘጋጀቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የገለፁ ሲሆን ቦታው ዘመናዊ የቢሮ አስተሳሰብን የያዘ እና ደረጃውን ለጠበቀ የቢሮ አደረጃጀት ምቹ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ሕንፃ አገር በቀል ቁሳቁሶችን እና የወጣቶችን ፈጠራ በመጠቀም የሥራ ባህል ማዳበርን እና የክህሎት ፅንሰ ሃሳብን በማጎልበት መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል ፡፡
ምርታማነትን እና ፈጠራን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀው የህንፃው ይዘት ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አኳያ የተደራጀ እንዲሁም ግልፅነት የተላበሰ መሆኑ ለሠራተኛውም ሆነ ለተገልጋዩ እርካታ የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የበለጸጉት የቴክኖሎጂ ውጤቶችም ተቋሙን ከማስተዋወቅ ባሻገር ለውስጥም ሆነ ለውጭ ተገልጋይ በቀላሉ መገናኘት እና ጉዳይን መፈፀም የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የክልል ቢሮ ኃላፊዎቹ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮቹ ላምበረት ከሚገኘው ዋናው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሕንፃ ባሻገር የሠራተኛ ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጥበትን እና እንደ አዲስ እየተገነባ የሚገኘውን ጊቢ ጎብኝተዋል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አሰግድ ጌታቸው እየተገነባ የሚገኘው ቢሮዎችን ከቴክኖሎጂ ያቀናጀ እና ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን የሚፈታ ቴክኖሎጂን ያጣመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለኤጀንሲዎችም ሆነ ወደተለያዩ አገራት ለሚደረግ ጉዞ ይፈጅ የነበረውን 30 ቀን ወደ 15 ቀን ለማምጣት የአሰራር ለውጦችንም ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Read More »
News

በአገር አቀፍ ደረጃ የአንተርፕርነርሺፕ ስልጠናን በወጥነት ለመስጠት የሚረዳ መመሪያ ርክክብ ተካሄደ

ድጋፉ የተገኘዉ ከጀርመን መንግስት (Kfw) ልማት ባንክ እና ከኖርዌይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን ርክክቡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የጀርመን ልማት ባንክ ኬ ኤፍ ደብልዩ (Kfw) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋማቱ አስረክበዋል፡፡
የግብዓት ርክክብ በተደረገበት ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የጀርመን መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ ልዩ ቦታ የሚሰጠዉ መሆኑን ገልጸዉ ባንኩ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዉጤታማ ለማድረግ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለዉም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብዙ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ አሁን የተደረገዉ ድጋፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ ስርዓተ ስልጠና ለማዘመን እንደሚያግዝ እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባደረገዉ ሪፎርም ስርዓተ ስልጠናው ከገበያ ፍላጎት የሚመነጭ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የጀርመን ልማት ባንክ (Kfw) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬከተር ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ በበኩላቸዉ ላለፉት ሃያ ዓመታት ጀርመን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ገልጸዉ በዘርፉ አመርቂ የሚባል ዉጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጉብኝት በባንኩ የሚደረገው ድጋፍ ምን ያህል ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጣቸውንም ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ኢንስትቲዩት ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ ከዚህ ቀደም ከሚደረጉ ድጋፎች ይህንን ለየት የሚያደርገዉ በዘርፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልፀው ድጋፉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በገፅ ለገፅ የስልጠና አሰጣጥ ስርዓት ሳይወሰን በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡
ከድጋፍ ርክክቡ ጎን ለጎን ከጀርመን መንግስት የ32 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚያስችል ስምምነትም ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች በአግሮ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ሥልጠና እንዲገኙ ለማስቻል ነው፡፡ ስምምነቱ በፓይለት ደረጃ በሦስት ክልሎች ማለትም በሲዳማ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ፓርኮች ውስጥ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡

Read More »
News

The five finalists of the Agro-Business Idea Competition received awards for their successful proposals

Ministry of Labour and Skills co-hosted the first National Agro-Business Ideas Competition (ABIC 2022) in partnership with GIZ (Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit) and the Mastercard Foundation.
The ABIC 2022 initiative implemented under the project “Enhancing the skills of youth and women in the catchments of the Integrated Agro-Industrial Parks (IAIPs) of Ethiopia” and is co-funded by the BMZ and the European Union under the ‘Ethio-German Sustainable Training and Education Programme’ (STEP)’ and the ‘Promotion of Sustainable Ethiopian Agro-Industrial Development (PROSEAD)’ program.
The initiative, implemented by GIZ, aims to promote self-employment for young university graduates to solve key gaps in the agro-industrial sector in Ethiopia.
State Minister of Ministry of Labour and Skills H.E. Nigusu Tilahun, give award for Five team from competent of four universities. H.E Nigussu praised the producers and coordinators for running a creative imaginary contest to alleviate farmers life.
Candidates were young potential entrepreneurs trained and supported through the Business Incubation component of the project of the two hundred participants in the competition, sixty were selected for further support based on their business ideas, and 17 were selected to go into a further round of competition, leading to the group of finalists recognised for their achievements
This is a collaborative initiative with the Universities of Bahirdar, Debremarkos, Adama and Hawassa.

Read More »
News

በአገር አቀፍ ደረጃ የአንተርፕርነርሺፕ ስልጠናን በወጥነት ለመስጠት የሚረዳ መመሪያ ርክክብ ተካሄደ

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በኢንጆይ ኮንሰርቲየም አማካኝነት ያዘጋጀው መመሪያ የሥራ ዕድልን ለማስፋፋት ዋና መንገድ የሆነውን የአንተርፕርነርሺፕ ስልጠናን ወጥ በሆነ መንገድ ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

ኢንጆይ ኮንሰርቲየም የተዘጋጀውን መመሪያ ባስረከበበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር በከር ሻሌ (ዶ/ር) የህይወት ክህሎት እና የአንተርፕርነርሺፕ ስልጠና ወጣቶችን ከትምህርት ወደ ሥራ እንዲሸጋገሩ በማድረግ በኩል ትልቅ ጥቅም እንዳለው በመግለፅ የሚሰጡ ስልጠናዎችም ወጥ በሆነ ካሪኩለም እና መመሪያ መታገዛቸው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የስልጠና መመሪያው ድግግሞሽን በማስወገድ ወጥ የሆነ ሥርዓት በመዘርጋት ለሥልጠና ሥርዓቱ የሚያበረክተው ሚና ትልቅ በመሆኑ ያዘጋጁትን ድርጅቶች እና ባለሙያዎች አመስግነዋል፡፡

የአንተርፕርነርሺፕ ፣ የሥራ ዝግጅት እና የህይወት ክህሎት ስልጠና መመሪያው በዋናነት ታላሚ ያደረገው የዩኒቨርሲቲ እና የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎችን እንዲሁም ሥራ ፈጣሪዎችን በመሆኑ በርካታ ወጣቶች ላሏት ኢትዮጵያ ጠቃሚ መሆኑን የተናገሩት የካሪታዝ ስዊዘርላንድ የቀጠናው ዳይሬክተር የንስ ስትራንግል ናቸው፡፡
በአገሪቱ እየጨመረ ለመጣው የሥራ ፈጠራ ፣ ስልጠና እና አዎንታዊ የህይወት ለውጥ እንቅስቃሴ አስተዋፃኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት በአውሮፓ ህብረት የግሪን ዲል ቡድን መሪ ዶሚኒክ ዳቮክስ እንዲህ ዓይነት መመሪያዎች ለውጥ የሚያመጣ ስልጠና ለመስጠት ያግዛሉ ብለዋል፡፡
በማንዋል ርክክብ ሥነስርዓቱ ላይ በአገሪቱ ስላለው የሥራ ዕድል እና ስልጠና ገለፃ የተደረገ ሲሆን መመሪያውን ያዘጋጀው ኢንጆይ ፕሮጀክት ሴቶች እና ወጣቶችን በተመለከተ ያከናወናቸውን ተግባራት አብራርቷል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top