Mols.gov.et

ባለፉት 6 ወራት ከ 1.4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ

February 2, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከክልልና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ አካሄዷል፡፡ በመድረኩ ባለፉት 6 ወራት 1.8 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ የዕቅዱን 81 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተመላክቷል፡፡ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ55 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተገለፀው፡፡ የሥራ ዕድሉ የተፈጠረዉም 70 በመቶ ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም እና 30 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ በቅጥር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ከክህሎት ልማት አኳያም ነባር የሙያ ደረጃዎችን የመከለስና አዳስ የማዘጋጀት፣ አዲስ የምዘና መሳሪያዎች እና ተጨማሪ ቨርሽን፣ የስርዓተ ስልጠና እንዲሁም የማሰልጠኛ መሳሪያዎች የማዘጋጀት ሥራዎች በትኩረት መከናወናቸው ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በፌዴራል 5 እንዲሁም በክልሎች 525 ድርጅቶች ላይ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራ አመራር ሥርዓት ለመዘርጋት ታቅዶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የዕቅዱን 95 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ ነው የተጠቆመው። ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያም ስርዓቱን ቀልጣፋ፤ ውጤታማ፣ የዜጎችን ክብር አስጠብቆ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከመዳረሻ ሀገራት ጋር ሁለትዮሽ ስምመነት መፍጠር ላይ ሲሰራ የቆየ 77 የሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጀችን ለስራ ዝግጁ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የስርዓተ ስልጠና ክለሳ እና የማሰልጠኛ መሳሪያ ዝግጅትም እንደተከናወነ ነው በመድረኩ የተገለፀው።
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills