Mols.gov.et

News

News

የሀገር ህልውና እና እድገት የሚረጋገጠው ሥራ በሚፈጥሩ ግለሰቦች ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

የሀገር ህልውና እና እድገት የሚረጋገጠው ሥራ በሚፈጥሩ ግለሰቦች ነው፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
“ፈጠራን በክህሎት” በሚል መሪ ሀሳብ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ የመጀመሪያ በሆነው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ባለፈው አንድ ዓመት በተሳታፊ ወጣቶች የተሠሩ ቴክኖሎጂዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የቴክኖሎጂ ኤክስፖውን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በአንድ ዓመት ውስጥ ተግባራዊ የተደረጉ ቴክኖሎጂዎች እንደ ሀገር ብልጽግና ለማረጋገጥ ከተቀመጡ ፒላሮች በእጅጉ የተሳሰሩ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሀገር ህልውና እና እድገት የሚረጋገጠው ሥራ በሚፈጥሩ ግለሰቦች መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ጠየቅላይ ሚኒስትር ፕሮግራሙ ወጣቶች እጃቸውን፣ አዕምሮአቸውን እና ልባቸውን አገናኝተው ከሰሩ አስደማሚ ነገር መስራት እንደሚችሉ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡።
ቴክኖሎጂዎቹ ኢትዮጵያ ፋብሪካ መፍጠር የምትችል ሀገር መሆኗን ያረጋገጡ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቀጣይ የማባዛትና ማስቀጠል ሥራ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል። መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ፕሮግራሙ በዘርፉ የመጀመሪያና ፋና ወጊ ነው ብለዋል፡፡
የመጀመሪያው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ላለፉት 12 ወራት በተለያ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳብ ውድድሮች አሸናፊ የነበሩ 400 ገደማ ወጣቶችን ከመላ ሀገሪቱ ክፍል ያሰባሰበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ተሳታፊዎች በቆይታቸው ቴክኖሎጂያቸውንና የፈጠራ ሀሳባቸውን ሊያሳድግ የሚችል የንድፈ ሀሳብና የተግባር ሥልጠና እንዲያገኙ መደረጉንና በ12 ወር ቆይታቸው በ11 ዘርፎች ችግር ፈቺና ሀብት አመንጪ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን መስራት እንደተቻለም ነው ክብርት ሚኒስትር የገለጹት፡፡
ከዚህ ውስጥ 45 የሚሆኑት የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያገኙ ሲሆን ቀሪዎቹም ሂደቱን እየጨረሱ ይይገኛሉ ብለዋል፡፡
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች የተናጠል ጉዟቸውን አቁመውና ኩባንያ የመሆን ርዕይ ሰንቀው በ78 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው የተወሰኑት ምርቶቻቸውን እስከ ውጭ ሀገር እስከ መላክ መድረሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ይህ ሥራ ኢትዮጵያ የጀመረችው ራስን የመቻል ጉዞ እንዲሳካ ተኪ ምርቶችን በብዛትና በጥራት እንድናመርት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በሰጡን አመራር ተግባራዊ የተደረገ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር በርካታ ባለድርሻና አጋር አካላትም የተሳተፉበት ነው ብለዋል፡፡
ኤክስፖው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጁት ሲሆን እስከ ጳጉሜ 4 ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

Read More Âť
News

ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው ማዕከል

ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው ማዕከል
በብየዳ ስልጠና ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው እና በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያና ብቸኛ የሆነው የምህንድስና ልህቀት ማዕከል አዲስ ህንፃ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡
ማዕከሉ በሀገራችን በብየዳ ሙያ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ሲሆን “ፈጠራን በክህሎት” በሚል መሪ ሀሳብ በትላንትናው ዕለት በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተከፈተውን የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡

Read More Âť
News

ቦርዱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ውጤታማነት በየጊዜው እያደገ እንዲሄድ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስተር

ቦርዱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ውጤታማነት በየጊዜው እያደገ እንዲሄድ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስተር
የፌዴራል ቋሚ የአሠሪና ሠራተኛ አማካሪ ቦርድ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቦርዱ የሚያከናዉናቸውን ተግባራት ውጤታማነት ለማሳደግ ሚኒስትር መ/ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ መንግስት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በአሠሪዎችም ሆነ በሠራተኞች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በበኩላቸው በ2017 በጀት ዓመት የሦስትዮሽ ግንኙነቱን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን ሚኒስትር መ/ቤቱ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቀዋል ።
በመድረኩ በአማካሪ ቦርዱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እና በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

Read More Âť
News

#ለ2ኛ ዙር የሠመርካምፕ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር ምዝገባ ተጀመረ።

#ለ2ኛ ዙር የሠመርካምፕ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር ምዝገባ ተጀመረ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ያዘጋጁት በአይነቱ ልዩ የሆነ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ወጣቶች የፈጠራ ሐሳባቸውን እና ችሎታቸውን ወደ ተጨባጭ ሥራ እንዲለውጡ በማስቻል ለአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ አበርክቶ ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ማስገኘት የሚያስችል ነው።
በዚህ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል። ስለሆነም በማንኛውም መስክ የቴክኖሎጂ እና የሥራ ፈጠራ ሐሳብ ያላችሁ በሙሉ ከነሐሴ 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።
https://forms.office.com/r/CNMFUUSZZe
#ማሳሰቢያ
📌 ምዝገባው የሚካሄደው በተቀመጠው ድህረገጽ ብቻ ነው
📌ከምዝገባ በኋላ በሚካሄድ ልየታ መሠረት ለሚመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የሠመር ካምፕ ፕሮግራሙ የሚካሄደው አዲስ አበባ ላምበረት መነሀሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ካምፓስ ነው።

Read More Âť
News

በጀት ዓመቱ ሚኒስቴሩ የጀመራቸው ትላልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ውጤት ተቀይረው ማየት የጀመርንበት ነው። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በጀት ዓመቱ ሚኒስቴሩ የጀመራቸው ትላልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ውጤት ተቀይረው ማየት የጀመርንበት ነው።
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
ሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚኒስቴሩ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አፈጻጸሙን አስመልክተው ባቀረቡት ገለጻ፤ ሚኒስቴሩ በ2016 በጀት ዓመት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የተጀመሩ ትላልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ተግባር ተሸጋግረው ውጤት ማስመዝገብ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በክህሎት ልማት ዘርፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተኪ ምርት በማምረት የኩባንያ መፈልፈያ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች፣ ኢንተርኘሪነሪያል የሆኑ ተቋማት ለመገንባት የተሄደበት ርቀት፣ ተቋማቱ አካባቢያዊ ጸጋ መሠረት አድርገው እንዲለሙ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች እንዲሁም ውጤታማ አጫጭር እና መደበኛ ስልጠናዎች ላይ የሚቆጠር ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።
ከሥራና ሥራ ሥምሪት አኳያ ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ያረጋገጠ ጥራት ያለው የሥራ ሥምሪት በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገር የተመዘገበበት በጀት ዓመት ነበር ብለዋል።
በተለይ በጀት ዓመቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት በተጨማሪ መዳረሻ ሀገራት በማስፋት የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች በተዘረጋው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመላክ ስምምነቶች የተደረጉበት ወደ ሥራም የተገባበት መሆኑንም ተናግረዋል።
በአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍም የኢንዱስትሪ ሰላም ለማረጋገጥ እና ምርታማነትን መሠረት ያደረጉ ጅምር ጥረቶች የተደረጉበት፣ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤንነት እንዲሁም የመደራጀት ምጣኔ የመሣሰሉ ተግባራት ላይ አበረታች ስኬት መመዝገቡንም አብራርተዋል።
በበጀት ዓመቱ በየዘርፋ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ በዚህ መድረክ ለውይይት ቀርበው የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በቀጣይ የእቅድ አካል አድርጎ ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።

Read More Âť
News

ስምምነቱ በግብርና ልማት ዘርፉ የተሰማሩና ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንተርፕራይዞችን የፋይናነስ አቅርቦት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ስምምነቱ በግብርና ልማት ዘርፉ የተሰማሩና ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንተርፕራይዞችን የፋይናነስ አቅርቦት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች ፋይናንስ ማቅረብ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈራረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ አያሌው(ዶ/ር) ናቸው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ስነ-ስርዓት ወቅት እንደገለጹት፤ ግብርና በዘመናዊ መንገድ ለመስራት እየተደረገ ባለው ጥረት የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅሙ ማደጉን ገልጸው ይህ ስምምነትም በግብርና ልማት ዘርፍ የተሰማሩ እና ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ ችግር መቅረፍ ላይ ትኩረቱ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለስራ ፈጣሪዎች ምቹ ምህዳር ለመፍጠር እያደረገ የሚገኘውን ጥረት አድንቀው በግብርናው ዘርፍ የወጣቶችን አቅም ለመጠቀምና፣ እራስን ለመቻል እና አለፍ ሲልም ኤክስፖርት ለማድረግ እየተደረገ የሚገኘውን ጥረት የፋይናነስ አቅርቦቱ በእጅጉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው ባንኩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የሚያቀርበው ይህ የፋይናንስ አቅርቦት የወጣቶች ኢንቨስትመንት ለማበረታታት እና በግብርና ሥራ ፈጠራ የተሰማሪ ኢንተርፕራይዞች የአዕምሮ ውጤታቸውን ያለምንም የፋይናንስ ተግዳሮት ወደ መሬት ማውረድ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
የፋይናንስ አቅርቦቱ ከተያዘው በጀት አመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ለአጠቃላይ ስራው 43 ሚሊዮን ዶላር ተመድቧል።

Read More Âť
News

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በአጋርፋ

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በአጋርፋ እየተሰጠ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ስልጠና በፎቶግራፍ

Read More Âť
News

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በባህዳር

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በባህዳር እየተሰጠ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ስልጠና በፎቶግራፍ

Read More Âť
News

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በቴፒ

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በቴፒ እየተሰጠ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ስልጠና በፎቶግራፍ

Read More Âť
News

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በደሴ

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ #በደሴ እየተሰጠ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ስልጠና በፎቶግራፍ

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
somSOM
Scroll to Top