Mols.gov.et

mols mols

News

ድህነትን የምናሸንፈው በእውቀት፣ በክህሎት እና በጠንካራ ሥራ ነው! — ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ

ድህነትን የምናሸንፈው በእውቀት፣ በክህሎት እና በጠንካራ ሥራ ነው! — ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
ድህነትን በዘላቂነት ማሸነፍ የሚቻለው በእውቀት፣ በክህሎት እና በጠንካራ የሥራ ባህል መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን የገለጹት፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎችና መመሪያዎች ዙሪያ በአማራ ክልል በጎንደር እና በደብረብርሃን ክላስተር ለሚገኙ የዘርፉ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫና የሥልጠና መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ በሥራ ዕድል ፈጠራ መስክ የተቀረጹ አዳዲስ እሳቤዎች፣ የአሠራር ሥርዓቶችና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሥራ አጥነት ችግር ዋነኛው የማክሮ ኢኮኖሚ ፈተና መሆኑን በማንሳት፣ መንግሥት የሥራ አጥነት ምጣኔውን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያውያን ፖለቲካዊ ነፃነታችንን በማስከበር ረገድ ደማቅ ታሪክ ያለን ሕዝቦች ነን ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችንን ሙሉ በሙሉ ባለመጎናጸፋችን፣ ድህነት በዓለም አደባባይ አንገታችንን ቀና እንዳናደርግ አድርጎን ቆይቷል ብለዋል።
ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ መንግሥት ትልቅ ርዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የቀረጻቸው አዳዲስ እሳቤዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት መስኩ ተስፋ ሰጪና ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አመላክተዋል።
በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ የታቀዱ የሪፎርም አጀንዳዎችን ውጤታማ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ባለሙያ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ስቡህ ገበያው በበኩላቸው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎች ላይ ለአመራሩና ለባለሙያዎች ተቀራራቢ ግንዛቤ ለመፍጠር መድረኩን በባዘጋጀቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

በዲጂታል አሠራር ዙሪያ ለኤጀንሲዎች ሥልጠና ተሰጠ

በአዲሱ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅና በዲጂታል አሠራር ዙሪያ ለኤጀንሲዎች ሥልጠና ተሰጠ

‎በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የውጭ ሀገር አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች ያዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ።

ኤጀንሲዎች ዕውቀትና ክህሎትን መሠረት ያደረገ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ ማስቻል የስልጠናው ዋንኛ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
‎በውጭ ሀገር ሥምሪት ሥርዓት ውስጥ አስፈላጊና መሟላት የሚገባቸው ሂደቶች ማለትም የሲስተም አጠቃቀም፣ የኤሌክትሮኒክስ ትኬቲንግ (Booking & Re-booking)፣ የሥራ መደቦች የምደባ ሥርዓት(Job Position)፣ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC) ቅሬታ አቀራረብ እና የውልና የQR ኮድ ጥያቄዎችን አፈጻጸም የተመለከቱ የቴክኒክ ሥልጠናዎችም በመርህግብሩ መካተታቸው ተጠቁሟል፡፡

‎ወደ ውጭ ሀገር ለሥራ የሚሄዱ ብቻ ሳይሆን የተመላሽ ሠራተኞችን አያያዝ የተመለከቱ ውይይቶችም ተካሂደዋል፡፡

‎በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው አዲሱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ዙሪያ ኤጀንሲዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ለሥራው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡
በተለይም በአዲሱ አዋጅ መሠረት የፈቃድ አሰጣጥ ሂደትና ሌሎች ሕጋዊ መስፈርቶች ላይ ግልጽነት በመፍጠር፣ በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን በጋራ ለመከላከል በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

‎ይህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ኤጀንሲዎች ያላቸውን የሲስተም አጠቃቀም ክፍተት በመሙላት፣ የዜጎችን መብትና ደኅንነት ባከበረ መልኩ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

Read More »
News

በሀረሪ ክልል ሀገር በቀል እውቀቶችን …

በሀረሪ ክልል ሀገር በቀል እውቀቶችን በማጎልበት ሙያዊ በሆነ የምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ቅድመ ዝግጅት ስራ ተጀመረ
የሀረሪ ክልል የልህቀት ማእከልና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሀገር በቀል ሙያዎችን ለማሳደግና በምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ሥራ አስጀምረዋል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ ሀገር በቀል እውቀቶችን በማሳደግ በሀገር ብልፅግና ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሀገር በቀል እውቀቶችን በማጎልበት ሙያዊ በሆነ ምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞች ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል።
በክልሉም የኢናይ አቢዳ ማሰልጠኛ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የሙያዎቹን ምዘናና ደረጃ (level) የማውጣት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
የሀረሪ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ሃላፊ አቶ በዳሳ ገመዳ፤ ሀገር በቀል የሙያ ደረጃዎችን በተከተለ መልኩ እየተሰጡ የሚገኙ ስልጠናዎችን በማጠናከር ወደ ኢንዱስትሪው እንዲገቡ የማስቻል ስራዎች በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃግብሩ ላይም የሀረሪ ክልል ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለሞያዎችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል።

Read More »
News

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ለወጣቶች

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ለወጣቶች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው
በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ለወጣቶች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ “የኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት ለአዲስ ብልፅግና’’ በሚል መሪ ሀሳብ ሲያካሂድ የቆየው የነባር ኢንተርፕራይዞች ንቅናቄ ማጠቃለያ መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።
በየዓመቱ አዳዲስ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥልጠናዎችን ወስደው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ወጣቶቹ በተሰማሩበት ዘርፍ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ዕድል ፈጥሮላቸዋል ብለዋል።
ነባር ኢንተርፕራይዞችም ተከታታይ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በከተማው እየተፈጠሩ ያሉ የሥራ ዕድሎች ውጤታማ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በመድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሚሊዮን ማቲዎስ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የኢንተርፕራይዝ አባላት ተገኝተዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው።

Read More »
News

ፍትሃዊ የፋይናንስ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው የማለዳ ውይይት

ፍትሃዊ የፋይናንስ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው የማለዳ ውይይት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን፣ ፈጠራን ማዕከል ያደረገና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የፐብሊክ ሴክተር ኢኖቬሽን ላብ አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል፡፡
ይሀንን መነሻ በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመለየት፣ አዳዲስ ሃሳቦችን ለማመንጨት እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማመላከት በየወሩ የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማትየሥራ ኃላፊዎች እና የማኔጅንት አባላት የሚሳተፉበት የማለዳ ውይይት ይካሄዳል፡፡
የዛሬው ውይይት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርቡ የተፈራረማቸውን የትብብር ስምምነቶች ወደ መሬት ማውረድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አተኩሮ ተካሂዷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ምንም እንኳን ኢንተርፕራይዞችና ስታርታፖች የሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ቢሆኑም ሥራቸውን በሚጠበቀው ልክ እንዳያሳኩ የፋይናንስ አቅርቦት ዋነኛው ማነቆ ሆኖ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትር ባቀረቡት ማብራሪያ በሀገራችን 70 በመቶ የሚሆኑ የሥራ ዕድሎች በኢንተርፕራይዞች እንደሚፈጠሩ ጥናቶችን ጠቅሰው ልፀዋል፡፡
ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ኢንተርፕራይዞች 80 በመቶ የሚሆኑት ማደግ እና መስፋፋት ቢፈልጉም በብድር አቅርቦት ምክንያት እድገታቸው እንደሚገታና የፋይናንስ ተደራሽነት ችግር የብዙ ሥራ ፈጠራሪዎች ችግር መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
የኢንተርፕራይዞችና የስታርታፕ ቢዝነሶችን የፋይናንስ ችግር በመፍታት በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ሲያካሄድ በቆየው ውይይት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ ስምምነቶቹን ወደ ዕቅድ ቀይሮ የሚጠበቀውን ውጤት ለማሳካት በየደረጃው ከተለወጠው ሁኔታ ጋር የተለወጠ አካሄድ መኖር እንዳለበት ጠቁመው ለተግባረዊነቱ ሁሉም አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስምምነቶቹ ለሥራ፣ ለፈጠራ እና ለኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ጠቅሰው የትብብር ማዕቀፎቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያሳኩ ያስችላሉ ያሏቸውን ሀሳቦች በዝርዝር አንስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

Read More »
News

ክልሉ አሸናፊ ለሆኑ ሴት ስራ ፈጣሪዎች…

ክልሉ አሸናፊ ለሆኑ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የ1.8 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከተ
የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን በማወዳደር የገንዘብ ድጋፍ አበርክቶላቸዋል፡፡
የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሴት ወጣቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቢሮው በብዙ ሴቶች አይደፈሩም ሲባሉ በቆዩ የሙያ ዘርፎች በማሰልጠን የሥራ ባለቤት እንዲሆኑና በክህሎታቸውና በንግዳቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አደርጓል ብለዋል፡፡
በሴቶች ባለቤትነት የሚመሩ የ19 ኢንተርፕራይዞችን የቢዝነስ ሀሳብ በማወዳደር አሸናፊ ለሆኑ ዘጠኝ ኢንተርፕራይዞች 1.8 ሚሊዮን ብር በሽልማት እንዳበረከተላቸውም ተጠቁሟል፡፡
የማህበረሰብ ምሰሶ ተብለው የሚጠቀሱት ሴቶች በሥራ ሥምሪት ሲሳተፉ የሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡
በተለይ በግብርና፣ በንግድ እና በአገልግሎት በመሳሰሉ ዘርፎች ትልቅ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
በተጨማሪም ሴቶች የሚያገኙት ገቢ 90 በመቶ ለቤተሰብ፣ ለልጆች፣ ለትምህርት እና ለቤተሰብ ምግብ ዋስትና እንሚያውሉትም እንዲሁ፡፡
ይህ ተጨባጭ ሁኔታ “ሴቶችን ማብቃት ማህበረሰብን ማብቃት ነው” የሚለውን መርህ ያጠናክራል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት…

ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት ተጉዘው እንዲሠሩ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ባለፉት አምስት ወራት በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ1 ሺህ 300 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ለየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅና ለመከታተል መንግሥት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ባለፉት አምስት ወራት ብቻ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 300፣ እንዲሁም በሳውዲ ዓረቢያ የነበሩ 26 ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጸዋል።
ዜጎቹን ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለማውጣት ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ ባለበት ሁኔታ፤ አሁንም በደላሎች ያልተጨበጠ መረጃ የሚታለሉ ዜጎች በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ እየሄዱ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በመሆኑም ዜጎች ለሕይወት አስጊ ከሆኑ ሕገ-ወጥ ጉዞዎች ሊታቀቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ሄደው እንዲሠሩ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል። በተለይም በአረብ ሀገራት በሚገኙ ቆንስላዎች ዜጎችን የሚከታተሉ ዲፕሎማቶች ተመድበው የቅርብ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።
ከአሠሪዎቻቸው ጋር ችግር ለሚገጥማቸው ዜጎች የሕግ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሩ ጨምረው አብራርተዋል፡፡
ዘገባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ነው

Read More »
News

ታለንት ወሳኝ መሰረተ ልማት በመሆኑ ከሌሎች ልማቶች እኩል ኢንቨስት ማድረግ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ታለንት ወሳኝ መሰረተ ልማት በመሆኑ ከሌሎች ልማቶች እኩል ኢንቨስት ማድረግ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠቃለያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በይፋ የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራርያ፤ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ተወዳዳሪዎቻቸውን የሚበልጡበት አንዱ አቅም ተሽሎ መገኘት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መንግስት በጤና እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰሩ ፈጠራዎችን እንደሚያበራታታ እንዲሁም አግዞ እንደሚጠቀምም አረጋግጠዋል፡፡
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዋነኛ ዓላማ ቢያንስ ሀገር በቀል ሮቦት፤ ስልክ እና አይፓድ መፍጠር የሚያስችል የሀርድዌር ማምረቻ የመገንባት አቅም መፍጠር መሆኑን ገልጸው ይህም ከሶፍትዌር ወጥተን ሀርድዌር የመገንባት እድል ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የቡና ኤክስፖርት በ3 እጥፍ ማደጉን በመግለጽ ይህንን በዲጂታል ማገዝና እሴት ጨምሮ መላክ እንደሚገባ እና ለዚህም መንግስት አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
መንግስት ከኢትዮጵያ ገበያ አልፈው ወደ አፍሪካ ገበያ ምርቶቻቸውን የሚወስዱ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን በሙሉ አቅሙ እንደሚደግፍም ተናግረዋል፡፡
መንግስት እንደ ኤሌክትሪክ፤ መንገድና ቴሌኮሙኒኬሽን ሁሉ ታለንት ወሳኝ መሰረተ ልማት ነው ብሎ ያምናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አብራርተዋል፡፡
በኢንሳ የተጀመረውና ተጠናክሮ የቀጠለው የሰመር ካምፕ፣ በአብርሆት ቤተመጽሀፍት በየዓመቱ የሚሰናዳው የሮቦት ውድድር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ ያስጀመረው የስታርታፕ መሰረተ ልማት የተሟላለት ህንጻ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ጥራት ያላቸው የመንግስት መስርያ ቤቶች እና ለስታርታፕ ተብለው የተዘጋጁ ቦታዎች መፈጠራቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከምንሰራው ስራ እኩል ታለንት ላይ ኢንቨስት ልናደርግ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ትናንሽ ስታርታፖች እንዲያድጉና እንዳይጠፉ ማድረግ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ድርብ ኃላፊነት መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው አስገንዝበዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው።

Read More »
News

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ የሶማሊ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀመሩ

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ የሶማሊ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀመሩ
የሶማሊ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ እና ‎በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮችና የሴክተሮች ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
በ9 ተቋማቶች 32 አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር የሚሰጠው ሶማሊ መሶብ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተጠቁሟል።
በምረቃው ወቅት የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ፤ ማዕከሉ የሰውን ክብር የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል ዘመናዊ መሰረተ ልማት እና የሰው ሀይል መሟላቱን ተናግረዋል።
በቀጣይም በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ 13 ከተሞች ላይ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው የገለፁት።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮችና የሴክተሮች ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ፤ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመንግስት አገልግሎት ዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ዝለት በማስቀረት ሰው ተኮር የአገልግሎት ልህቀትን የማረጋገጥና ዜጎችን የማክበር ማሳያ ነው ብለዋል።
በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር በማካተት፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ያግዛልም ሲሉ ተናግረዋል።
ማዕከሉ አገልግሎት ፈላጊ ዜጎች በፍትሀዊነት እና በውጤታማነት የሚስተናገዱበትን ስርዓት ለመዝረጋት የሚኖረው ፋይዳ የላቀ መሆኑም ተጠቁሟል። ዘገባው የኢቢሲ ነው።

Read More »
News

በፈጠራ ሥራው ለብዙኃን ብርሃን የፈነጠቀው ወጣት

በፈጠራ ሥራው ለብዙኃን ብርሃን የፈነጠቀው ወጣት
ብዙዎች ችግርን ሲያማርሩ ጥቂቶች ግን ወደ ዕድል ይቀይሩታል።
ወጣት ፌደሳ ሹማ ከእነዚህ ጥቂት ባለ ራዕይ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው፡፡
ወጣቱ በኢትዮጵያ የተሰራ በሚል ስም ድምጽና ጭስ አልባ ዘመናዊ ጄነሬተሮችን የሚያመርተው “ፌዶ ፓወር ሶሉሽን” (Fedo Power Solution) ባለቤት ነው፡፡
የወጣቱ የጥረትና የፈጠራ ውጤት ዘመናዊና ለአካባቢ ተስማሚ ጄኔሬተር ሲሆን፤ ወጣት ፌዴሳ ምርቱን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ሕልም ሰንቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወጣቶች በሰመር ካምፕ የሰሯቸውን የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች በተመለከቱበት ወቅት፤ ሀገር የምትሻገረው ከትንሽ ተነስተው ወደ ትልቅ ኩባንያዎች በሚያድጉ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የፈጠራ ስራዎቹ ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሰረት እንደሚጥሉ ጠቅሰው፤ የተመለከቱት ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደረጎ ተጨማሪ ነዳጅ ሳይጠቀም ለበርካታ ሰዎች ብርሃን መስጠት የሚያስችል ድንቅ የፈጠራ ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንዲህ ያሉ የፈጠራ ስራዎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ተሻለ አኗኗር የሚያሸጋግሩ ናቸው ነው ያሉት፡፡
የፌዶ ፓወር ሶሉሽን መስራች ወጣት ፌደሳ ሹማ ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ እንደገለጸው፤ የፈጠራ ስራውን የጀመረው በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በስራው ላይ በፈጠረበት ተግዳሮት የተነሳ ነው፡፡
ከዚህ ባለፈ ለስራው ይጠቀምበት የነበረው ጄኔሬተር ነዳጅ የሚጨርስ፣ ድምፁ የሚረብሽና ጭስ የሚያወጣ መሆኑ ለወጣቱ ትልቅ ራስ ምታት ሆኖበት እንደነበርም ያስታውሳል፡፡
ይህንኑ ችግር ለማቃለል መፍትሄ መፈለግ የጀመረው ወጣት ፌደሳ በ2014 ዓ.ም የራሱን ጄኔሬተር በመሥራት የፈጠራ ሕልሙን ዕውን ማድረጉን ተናግሯል፡፡
ወጣቱ በፈጠራ ሥራው ለመጀመሪያ ጊዜ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀ ውድድር አሸናፊ በመሆን የፈጠራ አቅሙን መረዳት እንደቻለ ያስታውሳል፡፡
ከዛም በዞን፣ በክልልና በፌዴራል ደረጃ የተደረጉ የፈጠራ ውድድሮችን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የ260 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ማግኘቱ ለስራው ማደግ የራሱ ሚና እንደነበረው ጠቅሷል፡፡
ይህ ሽልማት ለትልቅ ሕልሙ መነሻ እንደሆነው የሚናገረው ወጣት ፌደሳ፤ መጀመሪያ በ300 ኪሎ ዋት የጀመረው የፈጠራ ሥራ ዛሬ ወደ 600 እና አንድ ነጥብ አምስት ሜጋ ዋት መሸጋገሩንም ተናግሯል፡፡
ፌዶ ፓወር ሶሉሽን የሚያመርታቸው ጄኔሬተሮች ድምፅና ጭስ አልባ መሆናቸው ለአካባቢ ጥበቃና ለጤና ተስማሚ አድርጓቸዋል።
ፌዶ ፓወር ሶሉሽን የሥራና ክህሎት፣ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት በክህሎት ኢትዮጵያ ካፈሯቸው የሥራና የፈጠራ ሥራ ባለሙያውች አንዱ ነው። ዘገባው የኢዜአ ነው

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
somSOM
Scroll to Top