Mols.gov.et

News

News

“የኢንዱስትሪ ሰላም ለምርታማነት፣ ምርታማነት ለሀገራዊ ብልጽግና!”

“የኢንዱስትሪ ሰላም ለምርታማነት፣ ምርታማነት ለሀገራዊ ብልጽግና!”
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን እና ለምርታማነትና ተግዳሮት የነበሩ ትርክቶችን ለመቀየር የሚያስችል አዲስ የሪፎርም እሳቤን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ግንኙነት ዴስክ ኃላፊ አቶ ውብሸት ዘለለው የሚኒስቴር መ/ቤቱ አዲስ የዘርፍ እሳቤ የኢንዱስትሪዎችንና የሠራተኞችን ተወዳዳሪነት የሚያልቅ ብሎም አቀፋዊ ዕድሎችንና ተግዳሮቶችን በአግባቡ የቃኘ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡
በኢትዮጵያ ስለ ምርታማነት የሚነሱ ትርክቶች ብዙ ጊዜ በሁለት ተቃራኒ ጎራዎች እንደሚፈረጁ የሚገልጹት አቶ ውብሸት፤ በአንድ በኩል አሠሪዎች “ሠራተኛው ዝቅተኛ የሥራ ዲሲፕሊንና ክህሎት፣ የሥራ ባህል የሌለው፣ መብቱን ብቻ የሚጠይቅ፣ ግዴታውን የማይወጣና ምርታማነቱ ዝቅተኛ ነው” የሚል ትርክት እንደሚያራምዱ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ሠራተኞች “ሰብአዊ ክብራችን፣ ጤንነታችንና ደህንነታችን የማይጠበቅ እንዲሁም በሕግ የተቀመጠ መብታችንን እንዳንጠቀም ክልከላ ይደረግብናል፤ ለምርትና ምርታማነት የሚያጎለብቱ ሐሳቦች ቢኖሩንም የሚሰማን ባለመኖሩ ምርታማነታችን ቀንሷል” በሚል አሠሪዎችን ሲከስሱ ይደመጣል፡፡
መሰል አመለካከቶች ሥር መስደዳቸውና “የበዝባዥና ተበዝባዥ” ትርክት መጎልበቱ በኢንዱስትሪዎች ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲፈጥሩና በኢንዱስትሪ ሰላም ላይ ጥላ ሲጥሉ ቆይተዋል፡፡
የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያመላክቱት ምርታማነትን ከሰው ክብርና ጥቅም ነጥሎ ማየት እንደማይቻልም የሚሉት አቶ ውብሸት ሚኒስቴሩ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን በምርትና ምርታማነት ላይ ምክክር በማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚችል እና የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያረጋግጥ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል ለመገንባት ላለፉት ዓመታት “የኢንዱስትሪ ማኅበረሰብ ምክክር ለምርታማነት” ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ያስረዳሉ፡፡
ይህንንም ተከትሎ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በማደራደርና በማስማማት ፈጣን መፍትሔ የሚያገኙበት አሠራር በመዘርጋቱ የሥራ ማቆም አድማዎችንና የሥራ መስተጓጎሎችን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል።
በሌላ በኩል ሠራተኛው ስለ መብቱና ግዴታው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ በተሠሩ ሥራዎች የሥራ ተነሳሽነትንና ዲሲፕሊንን በማጎልበት የኢንዱስትሪዎችን የምርት ጥራትና ብዛት ማሳደግ ተችሏል።
ኢንዱስትሪ ማኅበረሰቡ (አሠሪ፣ ሠራተኛና መንግሥት) በጋራ በሚያደርጉት ምክክር፣ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጤቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ ስልታዊ አቅጣጫዎች እየተቀመጡ ይገኛሉ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “የኢንዱስትሪ ሰላም ለምርታማነት” የሚለውን መሪ ሃሳብ ለማሳካት፣ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ምክክር ቀጣይነት ባለው መልኩ እስከ ታችኛው የዘርፉ መዋቅር እንዲሰርጽ በትኩረት እየሠራ መሆኑ የኢንዱስትሪው ማኅበረሰቡ ለምርታማነትና ለሀገራዊ ብልጽግና በጋራ የሚቆምበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር አቶ ውብሸት ዘለለው ገልጸዋል።

Read More »
News

ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለሀገር ምርታማነት ዕድገት

ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለሀገር ምርታማነት ዕድገት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰላማዊ የሥራ አካባቢን በመፍጠር ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም በአሠሪ፣ በሠራተኛና በመንግሥት መካከል የሚደረገውን የሶስትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛል።
በሚኒስቴሩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የሶስትዮሽ ግንኙነት ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳልክ ተክለኃዋርያት እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል በዘርፉ ይስተዋል የነበረው አሉታዊ ግንኙነት በአዲስ መልክ እንዲቀየር ተደርጓል።
“ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለሀገር ምርታማነት ዕድገት ወሳኝ መሠረት ነው” ያሉት አቶ እንዳልክ፣ ሚኒስቴሩ ወሳኝና አማካሪ ቦርዶችን በሁሉም ክልሎችና የኢንዱስትሪ መንደሮች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ሚኒስቴሩ የቦርዶችን አቅም ለመገንባትና አሠራራቸውን ለማዘመን በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። በዚህም መሰረት ለወሳኝ ቦርዶች የቀረቡ የወል የሥራ ክርክሮች በውይይትና በስምምነት እንዲቋጩ ተደርጓል። ይህም ሠራተኞች የሥራ ዋስትናቸው ሳይቋረጥ እንዲቀጥሉ፣ ድርጅቶችም ያለምንም መስተጓጎል ወደ ምርታማነት እንዲመለሱ አስችሏል ብለዋል፡፡

Read More »
News

በክልሉ በ8 ወራት ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ቢሮው አስታወቀ

በክልሉ በ8 ወራት ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ቢሮው አስታወቀ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ባለፉት ስምንት ወራት ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል።
ይህ አፈጻጸም ክልሉ ካስቀመጠው ግብ አንጻር ከፍተኛ ውጤት የታየበት መሆኑም ነው ቢሮው ያስታወቀው።
የቢሮው የሥራ ስምሪት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አለነ እንደገለጹት፣ ይህ ስኬት የተመዘገበው ቢሮው ተግባራዊ እያደረገ ባለው “አዲሱ የክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ” እሳቤ ነው።
ስራው በዘልማድ ከመመራት ወጥቶ በዕውቀትና በክህሎት ላይ እንዲመሠረት መደረጉ ለውጤቱ መገኘት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።
የተፈጠሩት የሥራ ዕድሎች ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ያካተቱና ፍትሃዊነትን የተከተሉ መሆናቸውንና በቴክኒክ ኮሚቴው መካከል ያለው የተቀናጀ አሠራር ለሥራው መፋጠን ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱም ነው የተገለፀው፡፡
የተመዘገበው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ መዘመን እንዳለበት የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴው በክልሉ የሚታየውን ሥራ አጥነት ለመቀነስ ፋይዳው የላቀ መሆኑ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

Read More »
News

ብቁ የሰው ኃይል በስፋት በማፍራት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን የማድረግ ጉዞ

ብቁ የሰው ኃይል በስፋት በማፍራት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን የማድረግ ጉዞ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የአሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በተደራጀ መልኩ የሠለጠነ እና ብቃት ያለዉን የሰዉ ሃይል ለመንግስት ተቋማትና ለድርጅቶች ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ለሀገር ዉስጥ ሥራና ሠራተኛ ኤጀንሲዎችና ለሴክተር መዋቅር ፈጻሚዎች በብሔራዊ የሥራ ስምሪት ፖሊሲና ስትራቴጂ ፣ በአዲሱ የሥራና ክህሎት እሳቤ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ፣ ደንብ እና መመሪያ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ምክትል ሃላፊና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዮት ሸጋ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ አሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ለመንግስት ተቋማትና ለድርጅቶች የሚያቀርቡት የሰው ኃይል ብቁ፣ ተወዳዳሪና፣ በሥነ ምግባር የታነፀ እንዲሆን ለማስቻል ኤጀንሲዎቹ ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
ቢሮዉ አዲሱን የዘርፉን እሳቤ መሠረት ባደረገ መልኩ ዜጎችን በስልጠና የማብቃትና መዝኖ ብቃታቸውን የማረጋገጥ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ዘገባ ያመላክታል፡፡
ብቁ የሰው ኃይል በስፋት በማፍራት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን የማድረግ ራዕይን የሰነቀው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በማንኛውም የሥራ መስክ ላይ የሚሰማሩ ዜጎች መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ስልጠናዎች ራሳቸውን እንዲያበቁ፣ ተመዝነው ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል ሥርዓት ዘርግቷል፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሀገር ወዳድ፣ በሙያ ሥነ ምግባር የታነፀና በተሰማራበት መስክ ሁሉ ውጤታማ የሆነ ብቁ የሰው ኃይልን ለማፍራት የሚያስችል አዲስ የሪፎርም እሳቤን በመቅረፅም ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር …

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ማብቃትና ማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአቪዬሽን ዘርፍ የሰው ኃይል አቅርቦት፣ ስልጠና እና ስምሪት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ ወጣቶች በዘርፉ አሰልጥኖ ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ብቁ አድርጎ ማቅረብ የሚያስችል ነው።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ የከባተ ልምድ ያለውን የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በሌሎችም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለአቬሽን ዘርፉ ብቁ ወጣቶችን አሰልጥኖ ለሀገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ ባይ በበኩላቸው፣ አየር መንገዱ በዓመት ከ3 ሺህ እስከ 4 ሺህ የሚደርስ አዲስ ሠራተኛ እንደሚቀጥር ጠቁመዋል።
ሰራተኞችን የመመልመል እና የማሰልጠን ሂደት አድካሚና ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር መሥራት የሥራ ድግግሞሽን ከማስቀረቱም በላይ የሀገሪቱን ወጣቶች በአግባቡ በማብቃት ተወዳዳሪ ዜጎችን መፍጠር ያስችላል ብለዋል።
ከኮቪድ-19 በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአቪዬሽን ባለሙያዎች እጥረት እንዳለ የገለጹት ኃላፊው ይህንን ክፍተት ለመሙላት በቂ እና ብቁ ወጣቶችን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እና በቅንጅት ማሰልጥን ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በዚህ ስልጠና የሚያልፉ ወጣቶች በዋናነት ለኢትያጵያ አየር መንገድና ለሌሎችም ሀገራት አቬየሽን የማቅረብ ሥራ በስፋት እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡
ይህ ስምምነት የዜጎችን ሙያዊ ብቃት በማጎልበት በማሳደግ፣ በየትኛውም የዓለም ብቁ ተወዳዳሪ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲሰሩ ያስችላል ተብሏል፡፡
በቀጣይም የመግባቢያ ስምምነቱ ወደ ዝርዝር ዕቅድ ተቀይሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል።

Read More »
News

ባለፉት ሰባት ወራት ከ447 ሺህ በላይ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል

ባለፉት ሰባት ወራት ከ447 ሺህ በላይ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ስትሪንግ ኮሚቴ ዕቅድ አፈፃፀሙን ክቡር አምባሳደር አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግሟል፡፡
በዚህም ባለፉት ሰባት ወራት ከ447 ሺህ በላይ ዜጎችን ጥራት ያለው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ ላይ እንደተመለከተው፣ የተመዘገበው ስኬት የሰው ኃይል ዝግጅትን፣ የሥራ ገበያ ፍላጎትንና ለሥራው ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርን ማዕከል ባደረገ የጋራ ዕቅድ ሁሉም ባለድርሻና አስፈፃሚ አካላት ተሰናስለው በመስራታቸው መሆኑ ተመላክቷል።
ይህ የተቀናጀ አሠራር የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ባለፉት ሰባት ወራት በተተከናወኑ ሥራዎች የተገኘው ውጤት፤ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሻሻል የታየበት መሆኑ ተመላክቷል።
በቀጣይም በሰው ኃይል ዝግጅት ረገድ የግል ዘርፉና ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ድርጅቶች በስፋት እንዲሳተፉ ማበረታታት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ይህም የዜጎችን ተወዳዳሪነትና የሥራ ጥራት ይበልጥ ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ መሆኑና የተጀመሩ የቅንጅት ሥራዎችን በላቀ ትጋት ማጠናከር እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ …

በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጨባጭ፣ ተስፋ ሰጪና አዳጊ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል
በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ያለውን ውዝፍ፣ አሁናዊ እና የመጪውን ጊዜ ሀገራዊ ፍላጎት መመለስ በዘርፉ ተግባራዊ የተደረገው ፎርም ዋና ማጠንጠኛ ነው።
በዚህ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተቀርፆ ወደ ሥራ እንዲገባ የተደረገው “ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ” ስትራቴጂ፣ ዛሬ ላይ በሥራ ዕድል ፈጠራ ስነምዳር ውስጥ ተጨባጭ፣ ተስፋ ሰጪና አዳጊ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ፣ ከ2.6 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል።
የሥራ ዕድል ፈጠራውን በዘርፍ ስንመለከተው፤ የአገልግሎት ዘርፉ የ40.5 በመቶ ድርሻ በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲመራ፣ የግብርናው ዘርፍ 37.5 በመቶ እና ቀሪው 22 በመቶ የሚሆነው የሥራ ዕድል በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተፈጠረ ነው።
ከተፈጠረው አጠቃላይ የሥራ ዕድል ውስጥም 53 በመቶው በከተማ አካባቢዎች ሲሆን፣ ቀሪው 47 በመቶው ደግሞ በገጠር ለሚኖሩ ዜጎች የተመቻቸ ነው። ይህ ስርጭት በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ ሥራ ፈላጊዎችን ተደራሽ ለማድረግ በመንግስት የተሰጠውን ልዩ ትኩረት ማሳያ ነው።
የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በፈጠራና በፍትነት በማከናወን ከዕድገት ተኮር ዘርፎች ጋር ለማስተሳሰር በየደረጃው የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረትና ርብርብ፣ ለዚህ ታላቅ ውጤት መገኘት የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል።
ለዜጎች ሰፋፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማሳደግና የኢንተርፕሪነርሺፕ ምህዳሩን በማስፋት፣ ዜጎች የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚደረገው ድጋፍ፤ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለሀገራዊው የድህነት ቅነሳ ጉዞ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው።

Read More »
News

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚካሄደው ድጋፍና ክትትል …

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚካሄደው ድጋፍና ክትትል የዜጎችን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ የተከናወኑ የሥራና ሥራ ሥምሪት፣ የክህሎት ልማት፣ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳዮች እና የተቋም ግንባታ ተግባራትን ላይ ጠለቅ ያለ የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑን የመሩት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ፤ በክልሉ ተሞክሮ የሚወሰድባቸው አበረታች ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል፡፡
በክልሉ በክህሎት ልማት ዘርፍ የተቀረጹ አዳዲስ እሳቤዎች ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገው ጥረት አድንቀው በተለይ ኢንተርፕራይዞች ለመደገፍ የሚደረገው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ሥራ፣ በተጨባጭ ውጤት እየታየበት መሆኑ በመስክ ምልከታው መረጋገጡን ጠቁመዋል።
ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር በኮሪደር ልማት እና በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቮች ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የተቀረጹ እሳቤዎች ወደ መሬት ለማውረድ የተጀመሩ ጥረቶች አሰሪም ሰራተኛውም ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡
ቡድኑ በቆይታው ጠንካራ ጎኖችን ተጠናክረው አንዲቀጥሉ ከማበረታታት ባለፈ፣ በሂደቱ የታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙና ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አመላክቷል፡፡
ይህ የድጋፍና ክትትል ሥራ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑና የዜጎችን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ በሚያስችል መንግድ ለመተግበር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንም የክልሉ የዘርፉ ኃለፊዎች ገልጸዋል።

Read More »
News

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነትን …

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ ነው – ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሠራተኛ ማኅበር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ 11ኛውን የሕብረት የስምምነት ተፈራርመዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
‎‎
የአሠሪና ሠራተኛ መልካም ግንኙነት መኖሩ ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዋነኛው መሣሪያ መሆኑንም አፅንዖት አንስተዋል።
‎በዕለቱ የተፈረመው የሕብረት ስምምነትም በአየር መንገዱ አመራርና በሠራተኛው መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚያረጋግጥና ለተቋሙ ዘላቂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አመላክተዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ ስምምነት በሚኒስቴሩ የታለመውን ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት የመገንባት ራዕይ በተግባር የሚያሳይ ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፤ የሕብረት ስምምነቱ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ቀጣይነት ያለው ስኬት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልፀዋል።
የሕብረት ስምምነቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዕድገት በማፋጠን የሠራተኞችን ጥቅም በዘላቂነት የሚያስከብር መሆኑንም አብራርተዋል።

Read More »
News

ስምምነቱ በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት…

ስምምነቱ በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር፤ ስምምነቱ ኢንስቲትዩቱ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችን በማሻሻል በኩል ትርጉም ያለው ስራ እንዲሰራ ዕድል የሚፈጥርና በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ገልፀዋል።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚፈቱ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች በኢንስቲትዩቱ እንደሚሰሩም አመላክተዋል።
ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ችግር ፈቺ የሆኑ ተኪ ቴክኖሎጂዎችን የመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት በትኩረት እንደሚከናወንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በበኩላቸው፤ የቡና ጥራትን በመጠበቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የክህሎት ስልጠናዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ ካለው የማሰልጠን፣ የፈጠራ እና የምርምር ሥራዎች አቅም አንጻር አብሮ መስራቱ ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የያዛቸውን ዕቅዶች ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚሆንም ነው ያመላከቱት። መረጃው የኢኒስቲትዪቱ ነው።

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
oroORO
Scroll to Top