Mols.gov.et

News

News

ለአዳዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የሳይኮሜትርክስ ምዘና …

ለአዳዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የሳይኮሜትርክስ ምዘና …
የሳይኮሜትርክስ ምዘናው በባህር ዳር፣ በደብረታቦር እና በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጨምሮ በተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ተግባራዊ መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ምዘናው ለአዳዲስ ሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞች የሙያ መስክ ሲመርጡ በፍላጎቶት ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦና ዝንባሌያቸውን መሰረት በማድረግ ውጤታማ ሊሆኑባቸው የሚችሉ የሙያ መስኮች እንዲመርጡ የሚያግዛቸው ነው።
የሥልጠና ጥራትና አግባብነት እንዲሁም ውጤታማነትን ከሥራ ገበያ ፍላጎቱ ጋር በማጣጣም ብቁ፣ በቂና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን በማፍራት እንደ ሀገር ለሥራ ገበያው ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክና ሙያ ስርዓት ባለቤት እንድንሆን የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር እና የሳውዲ ዓረቢያው ተቋም ስትራቴጂያዊ ትብብር ፈጠሩ

የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር እና የሳውዲ ዓረቢያው ተቋም ስትራቴጂያዊ ትብብር ፈጠሩ
የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር (EYEA) እና የሳውዲ ዓረቢያ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተቋማት ባለስልጣን (ሙንሻአት) በዲጂታል እና በኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች ዘርፍ ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ትብብር መፍጠራቸው ተገለጸ።
በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነትም የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ሳሚያ አብዱልቃድር እና የ”ሙንሻአት” የጋራ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አብዱል ሙህሲን አል ሳሊም ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን በሳውዲ ዓረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) እና የ”ሙንሻአት” ዋና ገዥ የሆኑት አቶ ሳሚ ኢብራሂም አልሁሰይኒ በተገኙበት ተከናውኗል።
ይህ አጋርነት በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ እና በሳውዲ ዓረቢያ መካከል በሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች እና ስታርት አፖች መካከል ትርጉም ያለው ትብብርን ለማሳደግ ያለመ ነው።
ትብብሩ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ የጋራ ሥራዎችን፣ የአቅም ግንባታን እና ድንበር ተሻጋሪ የገበያ ተደራሽነትን ለማገዝ እንደሚረዳ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የወጣቶችን ፈጠራ ለማሳደግ፣ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ እና ወጣቶች ሁሉን አቀፍ ዕድገትን እንዲያመጡ እንዲሁም የረጅም ጊዜ የልማት ግቦች ላይ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ዘላቂ የሥራ ፈጠራ ሥርዓቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ትብብር መሆኑ ተገልጿል።
በመጨረሻም በዚህ ስምምነት “ሙንሻአት” ከሁለቱም ወገን ያሉ ሥራ ፈጣሪዎች ውጤት በማስመዝገብ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንዲጠቀሙ፣ በዓለም ዙሪያ ካሉ የሥራ ፈጣሪ ድርጅቶች ጋር ትብብርን እንዲያስፋፉ እና ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እድገትና ዘላቂነት የሚያበረታታ የተቀናጀ የንግድ ከባቢን እንዲፈጥሩ እንዲሁም ከሳውዲ አረቢያ ራዕይ 2030 ዓላማዎች ጋር እንዲጣጣሙ የሚያስችል – ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን እንዲያገኙ ለማስቻል የሚሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር የወጣቶችን የመፍጠር አቅም ለማጎልበት የሚሠራ ማኅበር ሲሆን፣ የማኅበሩ ዓላማ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እና ሃብት ማቅረብ እንዲሁም ቢዝነሶቻቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ የፈጠራ ሐሳቦችን የሚያገኙበትን ትስስሮችን መፍጠር ነው።
በስትራቴጂያዊ ምሰሶዎቹ እና ኢኒሼቲቮቹ አማካኝነትም ትብብርን፣ ፈጠራን እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያበረታታ ሕያው ሥነ-ምኅዳር ለመገንባትም ይሠራል። ዘገባው የኢቢሲ ነው።

Read More »
News

ክፍለ ከተማው በአንድ ጀምበር 1 ሺህ 100 የሥራ ዕድል መፍጠሩን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ

ክፍለ ከተማው በአንድ ጀምበር 1 ሺህ 100 የሥራ ዕድል መፍጠሩን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል” በሚል መሪ ሀሳብ የአንድ ጀንበር የሥራ ዕድል ፈጣራ ንቅናቄ አካሂዷል፡፡
ንቅናቄው በክፍለ ከተማው ባሉት ሁሉም ወረዳወቀች የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ለ1100 ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በንቅ በንቅናቄው መርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ክፍለ ከተማው ባለድርሻ አካላትን አስተባብሮ ለወጣቶች ሥራ ዕድል መፍጠሩ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።
ወጣቶች መንግስት ባመቻቸላቸው የሥራ ዕድል ገቢያቸውን በማሻሻል የራሳቸውና የሀገራቸው ሊለውጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሀላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው፤ ወጣቶች እውቀታቸውን እና ክህሎታቸውን ተጠቅመው ወደ ሥራ የሚገቡበት ሁኔታ እያመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በንቅናቄው ከተፈጠረው 1100 የሥራ ዕድል 61 በመቶ ወጣቶች መሆናቸውን ገልፀው ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎት፣ ንግድ እና ኮንስትራክሽን የሥራ ዕድሉ የተፈጠረባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Read More »
News

በማይታመን ፍጥነት በሁሉም ዘርፎች ውስጥ እየሰረፀ የሚገኘው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ

በማይታመን ፍጥነት በሁሉም ዘርፎች ውስጥ እየሰረፀ የሚገኘው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የጀመረውን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና ለማስተዳደር በሚያስችሉ ህጎችና ደንቦች ዙሪያ ያተኮረ ጥናት ኢኒስቲትዩቱ በየሳምንቱ በሚካሄደው ጥናትና ምርምር ጉባኤ ላይ ቀርቧል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ዓለም በአሁኑ ጊዜ እያስተናገደች የምትገኘውን የዕውቀት፣ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች በየሳምንቱ እየተካሄዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
ኢኒስቲትውቱ አዳዲስ እና ጠቃሚ የጥናትና ምርምር ርዕሰ ጉዳዮችን በመዳሰስ በተቋሙ የጀመረውን ፈጣን የሆነ የሪፎርም ሥርዓት በውጤታማነት እንደሚያስቀጥልም ተናግረዋል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በሁሉም ዘርፎች ውስጥ እያደገ የመጣ ቴክኖሎጂ ሲሆን በተለይም እንደ ኢንስቲትዩቱ ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተመራማሪዎች ዘርፉን ስርዓት ባለውና በኃላፊነትን በተላበሰ ስሜት ለመጠቀም በሚያስፈልጉ ህጎች፣ ደንቦችና ሥርዓቶች ላይ አተኩሮ ጉባኤው ተካሂዷል፡፡
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሥራን በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን ካለው ጠቀሜታ ባሻገር የሰው ልጅ ተጠቃሚነት ሳይጓደል ጎን ለጎን የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ለመሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከቀረበው የመነሻ ጥናት ላይ በመነሳት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከቴክኖሎጂው አጠቃቀም ረገድ ሌሎች ሀገራት ያጋጠማቸው አይነት ችግር ሀገራችንን እንዳይገጥማት ተሞክሮዎቻቸውን በመቅሰም ከወዲሁ ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግም በስፋት ተነስቷል፡፡
በዕለቱ በ‹‹በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም እንዴት የአየር ንብረት ብክለትን መቀነስ ቻላል ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Read More »
News

የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱ: አዲስ ምዕራፍ

የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱ: አዲስ ምዕራፍ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱ የስልጠና አግባብነትንና ጥራትን በሚጠበቀው ልክ የሚያሻሽልና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ለማድረግ መሰረተ ሰፊ ሪፎርም እያካሄደ ይገኛል።
የሪፎርሙ ዋነኛ ትኩረት ተዓማኒ፣ ግልፅ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ በቴክኖሎጂ የሚታገዝ እና የኢንዱስትሪውን ባለቤትነት ያረጋገጠ ሀገራዊ የብቃት ምዘናና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት ብቁ፣ ተወዳዳሪና አምራች ዜጎችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ማላቅ ነው።
በዚህም የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱን አውቶሜት ለማድረግ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናቆ የትግበራ ሥራን ለማስጀመር በኦሮሚያ እና በሀረሪ ክልሎች የመጀመሪያ የአውቶሜሽን ሲስተም ስልጠና ተሰጥቷል። በቀጣይ በሁሉም ክልሎች የአውቶሜሽን ስርዓቱን ለመተግበር ከኢትዩጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ኘሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በጋራ የማብቃት ሥራ የምናከናውን ይሆናል።
እንዲሁም ሁሉንም የክልልና የሁለቱም ከተማ አስተዳድሮች የሙያ ብቃት ምዘና ኤጀንሲዎች ዓለም አቀፉን ISO 17024 እውቅና እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር የቃል ኪዳን ውል የተፈራረሙ ሲሆን፣ ሲዳማ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ወደ ተግባር ሥራ የገቡ ክልሎች ናቸው።
በተጨማሪም የአዳዲስ የምዘና መሳሪያዎችን ዝግጅት እና የብቃት ምዘና መሳሪያዎች ብዝኃነትን ለማረጋገጥ ከክልሎች ጋር በመተባበር ቢያንስ አንድ ሙያ ከ4 በላይ ተጨማሪ ቨርዥን እንዲኖረው የማድረግ ሥራም እየተከናወነ እንደሆነ የሙያ ደረጃና ሥርዓተ ሥልጠና ዝግጅትና ብቃት ምዘና መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ማርታ ወልዴ ገልጸዋል።

Read More »
News

እንተርፕራይዞች ሥራቸውን ለማሳደግ የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተጠቆመ

እንተርፕራይዞች ሥራቸውን ለማሳደግ የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተጠቆመ
በተለያየ ደረጃ የሚገኙ እንተርፕራይዞች ሥራቸውን ለማሳደግ የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሥልጠናና የተቋማት አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙህዲን አባ ሞጋ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አጠናቃቂዎችና ኢንተርፕራይዞች ከሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የሥራ መጀመሪያና ማስፋፊያ ካፒታል እጥረት ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍም መንግስት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም የጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ እንተርፕራይዞች ቢዝነሳቸውን ለማሳደግ የሚያግዛቸውን የአቅም ግንባታ ሰልጠና የብድር አቅርቦት ላይ የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
የብድር አቅርቦት ጋር ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከስድስት ባንኮች ጋር ያለማስያዣ ወጣት ሥራ ፈጠሪዎች ብድር የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቶ ወደ ሥራ መገባቱ እና በቅርቡም የወጣጦች የሥራ ፈጠራ ኢንቨስትመንት ባንክ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱንም አስረድተዋል፡፡
ብድር የማግኘት ሂደቱ ከባንኮች መደበኛ የአሠራር ሂደት የተለየና ቀላል መሆን እንዳለበት፤ የንግድ ክህሎት ስልጠና የገንዘብ አያያዝና ብድር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሰልጠና መሰጠት እንዳለበት የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡
ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአነስተኛ ንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ከባንኮች በቀላሉ ብድር አግኝተው ሥራቸውን በማስፋፋት የኢንተርፕራይዞችን የመሞት ምጣኔ ለማሰቀረት እየተሰራ መሆኑም በዕለቱ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ ከአስራ አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማዎችና እና ከ12ቱ ሸገር ከተማ አስተዳዳር የሥራ ማዕከላት አስተባባሪዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲንና ምክትል ዲኖች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ፕሮጀክቱ ብቁ እና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን ለሥራ ገበያው ለማቅረብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ ብቁ እና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን ለሥራ ገበያው ለማቅረብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ትምህርትና ስልጠና ለሥራ ሥምሪት ፕሮጀከት (EASE Project) የአፈጻጸም ግምገማ እና ስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ አስተባባሪዎች እና የሥራ ቦታ ደህንነት ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ሐፍቶም ገ/እግዚያብሔር(ረ/ፕሮፌሰር)፣ ፕሮጀክቱ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በሥራ ገበያው ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ሰልጣኞች እንዲያፈሩ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በቀጣይ ፕሮጀክቱ የሥራ ጥራት ላይ እንደሚያተኩር የተጠቆመ ሲሆን አዳዲስ የሚጀመሩ እና የሚሻሻሉ ፕሮግራሞች ላይ ውጤታማ አፈጻጸም እንዲመዘገብ የጋራ አረዳድ ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ወደ ሥራ ሥምሪቱ የሚገቡ ሰልጣኞች የሥራ ቦታ ደህንነት የሚያረጋግጥ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በአለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስፈጻሚነት ሚኒስቴር መ/ቤቱን ጨምሮ በ24 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

Read More »
News

ኢንስቲትዩቱ ከአልጀሪያ መንግስት የተገኘ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ለሆኑ …

ኢንስቲትዩቱ ከአልጀሪያ መንግስት የተገኘ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ ለሆኑ የደረጃ 6(መጀመሪያ ዲግሪ) ሰልጣኞች የሽኝት መርሀግብር አካሄደ።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስልጠናና አቅም ግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) ይህ የግለሰቦች ትምህርት ጉዳይ ብቻ አይደለም አገርን በዓለምአቀፍ መድረክ የመወከል፣ ለዘርፉ ተጨማሪ አቅም የመፍጠር ጉዳይ ነው ብለዋል።
የአልጀሪያ ህዝብና መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያበረከቱት ይህ ስኮላርሺፕ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቅርብ ክትትል እውን መሆን ችሏል ያሉት ሐፍቶም (ረ/ፕሮፌሰር) ለዚህም ክብትር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ላደረጉት አመራር ሰጪነት ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢንስቲትዩቱ ለአገራችን የግብ ስኬት ቁልፍ ዘርፍ ለሆነው የክህሎት ልማት የመሪነት ሚና የሚወጣመሆኑን ገልጸው በዚህ ዕድል የሚጠቀሙ ወጣቶ ሲመለሱ የሚጨምሩት አቅም ብዙ ነው ብለዋል።
ተማሪ ታምራት ወንድምኩን እና ተማሪ ትህትና ለተሰጣቸው እድል አመስግነው በመጀመሪያ ኢንስቲትዩቱን መርጠው መግባታቸው በብዙ መንገድ እንደጠቀማቸው ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ፣ ውጤታማ ተማሪዎች ሆነን አገራችን የሰጠችንን አደራ በብቃት ተወጥተን ህዝባችንን ለመጥቀም ቃል እንገባለን ብለዋል።
በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅምግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) ከአደራ ጋር የአገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በክብር አስረክበዋል@FTVT

Read More »
News

መሶብ፡ የእፎይታ ማዕከል

መሶብ፡ የእፎይታ ማዕከል

አቶ ብሩክ በሚሠራበት ተቋም ውስጥ ተቀጥረው ለሚያገለግሉ የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፈቃድ ለማውጣት፣ ለማሳደስና ለማሰረዝ በየጊዜው አገልግሎቱን ይሰጡ ወደነበሩ ተቋማት ይመላለስ እንደነበረ ይናገራል፡፡
ወ/ሮ ትብለፅም በተመሳሳይ በምትሠራበት ካምፓኒ ከ 200 በላይ ቻይናውያን መኖራቸውን ትናገራለች፡፡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በሌለበት ሁኔታ በርካታ ቁጥር ያላቸውን የውጭ ሀገር ዜጎች ጉዳይ ማስፈፅም እጅግ ፈታኝ መሆኑን ትገልፃለች፡፡
አቶ አብዲማ ደግሞ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት ቡድን መሪ ናቸው ፡፡ እሳቸውም በዩኒቨርሲቲያቸው ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙ ህንዳውያንን የሥራ ፈቃድ ጉዳይ ለማስፈፀም ለበርካታ ዓመታት ወደ አዲስ አበባ ይመላለሱ እንደነበረ በማስታወስ የሚወስድባቸው የተራዘመ ጊዜ ለብዙ ችግርና እንግልት ይዳርጋቸው እንደነበረም ይናገራሉ፡፡
ቀደም ባሉት ዓመታት አገልግሎቱ የሚሰጠው ማኑዋል በሆነ መልኩ ስለነበር ፋይል መፈለግ፣ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል በነበረው ምልልስ ሳቢያ አንድን ጉዳይ ለማስፈፀም ከሁለት ሳምንት በላይ ይፈጅባቸው እንደነበር ሦስቱም ተገልጋዮች ያስታውሳሉ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመ በኋላ አገልግሎቱ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) አማካኝነት የሚሰጥ መሆኑ በተወሰነም ደረጃ ሥራውን አቀላጥፎት እንደነበር የሚገልፁት ተገልጋዮች ነገር ግን የተወሰኑ አገልግሎቶች በተለያየ ቦታ የሚሰጡ መሆናቸውበአሠራር ፍጥነት ላይ የራሱ የሆነ ተፅ ዕኖ እንደነበረው ይናገራሉ፡፡
ዛሬ ሦስቱም ባለጉዳዮች ቅልጥፍናን ከፍጥነት ጋር አጣምሮ በያዘው የ‹‹መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት›› ተገኝተዋል፡፡
ከጋምቤላ ከአንድ ቀን በፊት መምጣታቸውን የሚናገሩት አቶ አብዲማ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ዲጂታል በሆነ መልኩ በመጫናቸው ከግማሽ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ጉዳያቸውን ማጠናቀቃቸውን ይገልፃሉ፡፡
‹‹ከዓመታት በፊት የነበረውን ውጣውረድ ለሚያውቅ ሰው ይህ በእጅጉ ህልም ነው›› የሚሉት አቶ አብዲማ አሠራሩ ወደ ዲጂታል ከማደጉ በላይ የማዕከሉ ባለሙያዎች ብቃትና ሥነ ምግባርም አገልግሎቱን የበለጠ ምቹ እንዳደረገው ይናገራሉ፡፡
‹‹እንደ እኔ በርካታ ቁጥር ያላቸውን የውጭ ሀገር ዜጎች ጉዳይ ለሚያስፈፅም ሰው ፍጥነትና ቅልጥፍና በእጅጉ ወሳኝ ነው›› የምትለው ትብለፅ በመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት በተገኘች በውሱን ደቂቃዎች ውስጥ ጉዳዩዋን ማጠናቀቅ መቻሏ ህይወቷን በእጅጉ እንዳቀለለውም ትናገራለች፡፡
‹‹ላለፉት ስምንት ዓመታት አንድን ጉዳይ ለማስፈፀም ለሳምንታትና ለወራት እመላለስ ነበር›› የሚለው አቶ ብሩክም በበኩሉ በመሶብ አንድ ማዕከል ያገኘው አገልግሎት ጉልበቱንና ጊዜውን በእጅጉ እንደቆጠበለት በፈገግታ ታጅቦ ይናገራል፡፡
በ‹‹መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት›› የተጀመረው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲጠናከር ከሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትልና ትኩረት እንደሚፈልግ የሚናገሩት ሦስቱም ባለጉዳዮች በቀጣይ ሁሉም መንግስታዊ ተቋማት የአገልግሎት ደረጃቸውን ለማሻሻል ‹‹መሶብ መልካም አርዓያ የሆነ ተቋም ነው ›› በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Read More »
News

በክልሉ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታትና ህጋዊ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አሰራር እንዲጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ነው

በክልሉ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታትና ህጋዊ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አሰራር እንዲጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ነው
በኦሮሚያ ክልል ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታትና ህጋዊ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እንዲጠናከር በተቀናጀ አግባብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ።
ቢሮው በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ላይ ያተኮረ ኤጀንሲዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ በአዳማ አካሄዷል።
የቢሮ ሃላፊው አቶ አራርሶ ቢቂላ በወቅቱ እንደገለፁት፥ በክልሉ ህገወጥ የሰዎች ፍልሰትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
በዚህም ከፀጥታና ፍትህ አካላት እንዲሁም በዘርፉ ከተሰማሩና በክልሉ ከሚሰሩ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኤጀንሲዎች ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ህገወጥ ስደት በዜጎች ህይወት ላይ እና በአገር ገጽታ ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽእኖ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው፥ ዜጎችም ህጋዊ መንገድ ብቻ መከተል እንዳለባቸው መክረዋል።
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አቢት ኤዳኦ በበኩላቸው፥ በክልሉ ህገወጥ የሰዎች ፍልሰትን ለመግታት ለወጣቶች የግንዛቤ ማስረጽ ስራ እየተካሄደ ነው።
በተለይ ወደ ተለያዩ ሀገራት በደላሎች ተታለው በህገወጥ መንገድ የሚጓዙ ዜጎች ለአስከፊ ችግር እየተዳረጉ መሆኑን እንዲገነዘቡ ከማድረግ አኳያ አበረታች ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን የሚያከናውኑ ኤጀንሲዎች ህጋዊ አሰራርን ተከትለው እንዲሰሩ በ21 ዞኖችና በ23 ከተሞች ላይ ክትትል፤ ድጋፍና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በቢሮው የስራ ስምሪትና የገበያ መረጃ ስርዓት ዳይሬክተር ወይዘሮ ፋንታዬ ታደሰ ናቸው።
በተለይ የፀጥታና ፍትህ አካላትን ጨምሮ ከጨፌ ኦሮሚያ፤ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈው በጀት ዓመት በህጋዊ መንገድ ከክልሉ 153 ሺህ ዜጎች ወደ ተለያዩ ሀገራት ለስራ መጓዛቸውንም አስታውሰዋል።
በመድረኩ ላይ ከተሳተፉ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ኤጄንሲዎች ተወካዮች መካከል አቶ ኢዘዲን አህመድ፣ በርካታ ዜጎች በህጋዊ መንገድ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለስራ በኤጀንሲያቸው በኩል መጓዛቸውን ተናግረዋል።
ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፥ ዜጎችም በህጋዊ መንገድ ብቻ በመጓዝ ከሚገጥማቸው አደጋ ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው::

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
oroORO
Scroll to Top