Mols.gov.et

mols mols

News

ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም! ክቡር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም!
ክቡር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው‹‹የአፍሪካ ክህሎት ሳምንት 2025›› ከጥቅምት 3 እስከ 7/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በአፍሪካ ህብረት ዋና መ/ቤት ይካሄዳል፡፡
ይህ አህጉር አቀፍ ሁነት በመጀመሪያው ቀን ውሎው ‹‹የወጣቶች ክህሎት ለኢንዱስትሪያላይዜሽን….ከራዕይ ወደ ተግባር›› በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀውን የወጣቶች ጉባኤ አስተናግዷል፡፡
ከመላ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበትን ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት በ2050 አፍሪካ ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች የሆኑ 1ቢሊዮን በላይ የህዝብ ብዛት እንደሚኖራት ጠቁመው ይህን ሰፊ የወጣት ኃይል በተገቢው መልኩ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካ ነገን በተስፋ የምትጠብቅ አህጉር ትሆናለች ብለዋል፡፡
ኢንዱስትሪያላይዜሽንን በአፍሪካ ዕውን በማደርግ ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ለወጣቶቻችንን በክህሎት በማስታጠቅና የዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል እንዲሁም የኢንተርፕሪነርሺፕና ኤኖቬሽን አቅማቸውን ማላቅ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል እሴት የማከል፣ ምርታማነትን የማጎልበትና ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት የማቅረብ ግብ የያዘውን አጀንዳ 2063ን በመተግበር መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በሀገሪቱ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ርብርብ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
‹‹ከራዕይ ወደ ተግባር መሸጋገር›› የጉባኤው ዋንኛ ማጠንጠኛ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በወጣቶቿ ኃይል የኢንዱስትሪ እድገት ዕውን የሆነባት፣ ሰላማዊ፣ የበለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተጨባጭ ሥራ ውስጥ መግባት እንደሚኖርባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡
‹‹ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም!›› በማለትም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መልዕክታውን አጠቃለዋል፡፡

Read More »
News

ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሰማራው የሰው ኃይል እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሰማራው የሰው ኃይል እያደገ መምጣቱ ተገለጸ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ፣ በከሳዑዲ አረቢያ የሙሳነድ ፖርትፎሊዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካሊድ አልቱኪ ከተመራ ልዑክ ጋር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዙሪያ በሰራው የማሻሻያ ሥራዎችን ተከትሎ ወደ ሳውዲ የሚሰማራው የሰው ኃይል እያደገ መጥቷል፡፡
የዜጎች መብት፣ ደህንትና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያም ሁለቱ ሀገራት ተቀራርበው እየሰሩ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሂደቱ የሚሰተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ሳውዲ ለማሰማራት በሥራ ላይ ያለውን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት አዋጅ በማሻሻል ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡
በታካሞል ሆልዲንግ የሙሳነድ ፖርትፎሊዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካሊድ አልቱኪ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ቀዳሚ የሰው ኃይል አቅራቢ አገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ወደ ሳውዲ ዓረቢያ የሚሰማራውን የሰው ኃይል ቁጥር ለማሳደግም ፍላጎት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡

Read More »
News

በክህሎትና በሙያ የበቁ ዜጎችን ለማፍራት የአሰልጣኝ መምህራን የክህሎት ብቃት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ።

በክህሎትና በሙያ የበቁ ዜጎችን ለማፍራት የአሰልጣኝ መምህራን የክህሎት ብቃት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአዲሱ እሳቤ የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ የሥልጠና ጥራትን ማስጠበቅ ነው፡፡
ይህንንም መሰረት በማድረግ ቀደም ብሎ ለክልል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራን ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡
የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮም በበኩሉ ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራን ለ20 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የክህሎት ክፍተት ማሟያ ስልጠና መጠናቀቁን አሳውቋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የሙያ ስልጠናና የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍስሃ ፍቾላ በዕውቀትና በክህሎት የበቃ የሰው ሀይል ማፍራትና በተለዋዋጭ አለም የሚመጥን ዜጋን ማፍራት የዘርፉ ተልዕኮ መሆኑን ገልፀዋል ።
ለ20 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች የክህሎት ማሟያ ስልጠና በስስ ክህሎት እና በተግባር ተኮር ስልጠና ዘርፎች ለሁለት ተከፍሎ መሰጠቱን ጠቅሰው ስልጠናውም የሪፎርም ትግበራ ለማጠናከር እንደሚረዳ አያይዘው ተናግረዋል።
ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመቀናጀት በተሰራው ሥራ የስልጠና ጥራት ለማረጋገጥና የግብዓት ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ እገዛ እንዳደረገም ገልጸዋል ።
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወርክ ሾፖችንና የሰው ሀይል በማዘጋጀት ለሥልጠናው ስኬት ትልቅ ድርሻ መወጣቱን አንስተው በዚህም ያስቀመጥነው ግብ ማሳካት ችለናል ብለዋል።
በመቀጠል በክላስተር ደረጃ የሚሰጥ ስልጠና ጥቅምት 10/2018 ጀምሮ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው 340 የሚሆኑ አሰልጣኝ መምህራን መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን ስልጠናውን በብቃት ሲያሰለጥኑና ሲሰለጥኑ ለቆዩ አሰልጣኞችና ሰልጣኝ መምህራን የዕውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
መስከረም 29/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

Read More »
News

ኢንስቲትዩቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ከ10 በላይ አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞች መጀመሩ አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ከ10 በላይ አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞች መጀመሩ አስታወቀ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዜጎች ስለተቋሙ አገልግሎት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ የሚያስችል የመረጃ ሳምንት በይፋ አስጀምሯል፡፡
የመረጃ ሳምንቱን አስመልክተው ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) የመረጃ ሳምንቱ ዜጎች ተቋሙ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና ስለሚሰጣቸው ስልጠናዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በሀገራችን የብቃት ማዕቀፍ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 8 የፒኤች ዲ ደረጃ ድረስ ስልጠና መስጠት የሚችል ብቸኛ ተቋም መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በዘንድሮ አመት ብቻ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ከ10 በላይ አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞች መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ በደረጃ 6 ዲግሪ፣ በደረጃ ሰባት ማስተርስ እና ደረጃ ስምንት ፒኤችዲ ማስልጠን እንደሚጀምር አብራርተዋል፡፡
በደረጃ 6 በቅድመ ምረቃ የሚጀመሩት ባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ፣ ሳይበር ሰኩዩሪቲ ቴክኖሎጂ ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኒው ኢነርጂ ቬሂክል ቴክኖሎጂ ፣ ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ፣ ሆርቲካልቸር እና ኢንተለጀንት ሮቦቲክስ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ በደረጃ 7 በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ደግሞ ኢንቴርየር ዲዛይን እና ሌዘር ፕሮዳክት ቴክኖሎጂ እንዲሁም በደረጃ 8 በፒኤች ዲ ደረጃ በቲቬት ሊደርሺፕ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡
ተቋሙ ብቁ ሰልጣኞች ያሉት እና የተሟላ ግብዓት ያለው በመሆኑ ዜጎች በእነዚህና በሌሎችም በፈለጉት የሙያ ዘርፍ ገብተው ሰልጥነው ዘመን የማይሽረውን ክህሎት እንዲታጠቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

🌏✨ለውጪ ሃገር ሥራ ፈላጊዎች በሙሉ! ✈️

🌏✨ለውጪ ሃገር ሥራ ፈላጊዎች በሙሉ! ✈️

በተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ 🇦🇪 /UAE/ 3000 የሰው ሃይል ይፈለጋል።

በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት ⚖️፣ ደህንነት 🛡️ እና ጥቅም 💰 አስጠብቆ በማሰማራት በተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል።

አሁንም በዚሁ ህጋዊ ⚖️ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች 3000 የሰው ሃይል ይፈለጋል።

📌 የሥራ ቦታ: 🇦🇪 የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ (UAE)
📌 የኮንትራት ቆይታ: ሁለት ዓመት
📌 ተፈላጊ ፃታ: ወንድ

✨ የሙያ ዘርፎች:
1️⃣ Mason (block & plaster)/ ግንበኛ 🧱 (የብሎኬት እና የልሰና ሰራተኛ)
2️⃣ Steel fixer/የብረት ሙያተኛ 🔩
3️⃣ Shuttering Carpenter /የሸተር ሰራተኛ/አናጺ 🪚
4️⃣ Electrician /ኤሌክትሪክ ባለሙያ ⚡
5️⃣ Plumber /ቧንቧ ሰራተኛ 🚰
6️⃣ Fitter /ፊተር / መካኒክ አቀናጅ ⚙️ / የማሽን አቀናጅ ባለሙያ
7️⃣ Technician /ቴክኒሺያን 🧰

☝️ከላይ በተጠቀሱት የሙያ ዘርፎች ለመወዳደር ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት ትክክለኛ የትምህርት የሥራ ልምድ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

🔗https://forms.lmis.gov.et/

📆አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመስከረም 29/2018 ዓ.ም እስከ⏩ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

Read More »
News

ውበት፣ ምቾትና ቀልጣፋ አገልግሎት መገለጫው የሆነ ማዕከል

ውበት፣ ምቾትና ቀልጣፋ አገልግሎት መገለጫው የሆነ ማዕከል
‹‹አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት›› በአዲስ አበባ ከተማ፣ መሃል አራት ኪሎ ፣ አራዳ ክፍለ ከተማ ህንፃ ላይ ይገኛል፡፡ የህንፃውን የመግቢያ በር አልፈው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ከፊት ለፊትዎ አምሮ በተሠራ እንግዳ መቀበያ ላይ የተቀመmች ትሁት አስተናጋጅ ‹‹ እንኳን ደህና መጡ›› ብላ በትህትና የተሞላ ፈገግታ ትቸርዎታለች፡፡
ይህ ስፍራ አንድም ስለሚፈልጉት አገልግሎት መረጃ የሚያገኙበት ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ስካን ተደርገውና ወደ ዲጂታል መረጃነት ተለውጠው ወደ አገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎች የሚላክበት ነው፡፡
በመረጃ ዴስክ ላይ ያለዎትን ቆይታ ሲያጠናቅቁ በስተቀኝዎ ወደሚገኘው አዳራሽ ያመራሉ፡፡ በዚህ ክፍል አይን በሚስብ ዲዛይን የተሰሩ ባለጉዳይ የሚስተናገድባቸው መስኮቶች ይመለከታሉ፡፡ ከመስኮቶቹ ጀርባ ደረጃውን የጠበቀ የደንብ ልብስ የለበሱና በትህትና የተሞሉ ባለሙያዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት በፍጥነትና በቅልጥፍና ሊሰጥዎት በተጠንቀቅ ይጠብቅዎታል፡፡
እያንዳንዱ ባለሙያ ከተቀመጠበት ወንበር በላይ ማንነቱን፣ የየትኛውን ተቋም አገልግሎት እንደሚሰጥና ፎቶውን ጭምር የያዘ ዲጂታል ስክሪን ይታያል፡፡ የክፍሉ ዲዛይን ፣ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶቹ የተላበሱት ፀአዳ ቀለም ንፁህና ምቹ የሆነ ስሜትን ያላብስዎታል፡፡
የማዕከሉ የአገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ እንደሚገልፁት በማዕከሉ በርካታ የተገልጋይ ቁጥር የሚያስተናግዱ በ13 ተቋማት ውስጥ የነበሩ 107 አገልግሎቶች ዲጂታል ስርዓትን በመጠቀም በፍጥነትና በቅልጥፍና አገልግሎት እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
በህንፃው አራት ወለሎች ላይ በተመሳሳይ መልኩ የተደራጀው ማዕከል በውስጡ የኢኮኖሚ፣የመሬትና የመሬት ግንባታ፣ እንዲሁም የቤቶች አገልግሎቶችን አካትቶ ይዟል፡፡
ማዕከሉ ራሱን የቻለ የዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ያለው ሲሆን አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሶፍትዌሮችን እና የኔትዎርክ መሰረተ ልማትን ይከታተላል፡፡ አጠቃላይ በማዕከሉ በሚሰጠው አገልግሎት ውስጥ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ይቆጣጠራል፡፡ የተቋሙን የሳይበር ደህንነት ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑ አገልግሎቱ ደህንነት የተረጋገጠ እንዲሆን ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡
በማዕከሉ የሚሰጠው አገልግሎት ያለምንም መቆራረጥ እንዲሰጥ ራሱን የቻለ የጀነሬተርና ዩፒኤስን ጨምሮ ዘመናዊ የሆነ የኃይል አቅርቦት ሥርዓት የተሟላለት መሆኑንም አቶ ቴዎድሮስ ይገልፃሉ፡፡
ቅልጥፍና እና ፍጥነት የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዋንኛ መገለጫ እንደመሆኑ የማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ የራሱ የሆነ የአሠራርና ስታንዳርድ እንደተዘጋጀለትም አቶ ቴዎድሮስ ይናገራሉ፡፡ እያንዳንዱ ባለሙያ ከደንብ ልብስ አጠቃቀም ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥበትና ለእንግዶች የሚያሳየው ባህሪ ጭምር በስታንዳርዱ ውስጥ ተካቷል፡፡
በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሥራና ክህሎት ዘርፍ 3 አገልግሎቶችና 10 ተግባራት ይሰጣሉ፡፡ ሥራ ፈላጊ ግንዛቤ ማደራጀት፣ የሀገር ውስጥ ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ቁጥጥር እና ለሥራ ፈላጊዎች መንግስታዊ ድጋፎችን በተገቢው መልኩ ማመቻቸት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
አገልግሎቶቹ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (LMIS) የሚሰጡ መሆናቸው ከዚህ ቀደም ተደራጅቶ ወደ ሥራ ለመግባት የሚወስደውን ረጅም ጊዜና እጅግ የተንዛዛ አሰራር መቀየር ተችሏል፡፡ የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመውና ተደራጅተው ለመስራት የሚፈልጉ ወጣቶች አስፈላጊ የሆነውን ሰነድ ሙሉ በሙሉ አሟልተው ወደ ማዕከሉ ከመጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ጉዳያቸውን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም ሂደት አስፈላጊ የሆኑ የፈቃድ ምዝገባ፣ የስም ስያሜ፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የመሳሪያ ሊዝና የዘርፍ ማህበራት ማደራጃ አገልግሎት በማዕከሉ ውስጥ በተሟላ መልኩ መገኘቱ ለገልግሎቱ በሚፈለገው ደረጃ ፍጥነትንና ቅልጥፍናን እንዲላበስ አስችሎታል፡፡
የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በማስፋፋት መንግስታዊ አገልግሎቶችን ምቹና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ተደራሽ የማድረግ ጥረቱ ቀጥሏል፡፡
እርስዎም በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት መስጫ ማዕከል የነበርዎትን ቆይታ አጠናቀው ሲወጡ ውብና ምቹ በሆነ ቦታ፣ ተገቢው ክብር ተቸርዎት የሚፈልጉትን ማግኘት ችለዋልና ‹‹መሶብ ማለት ውበትና ምቾት ነው፡፡›› ብለው ቢያስቡ የሚገርም አይሆንም፡፡
ብቃትን፣ ትህትናን እና ስነምግባርን በተላበሱ ባለሙያዎች የተሰጥዎትን አገልግሎት በማሰብ ‹‹መሶብ ማለት ጥራት ያለው አገልግሎት ነው›› ከሚል ድምዳሜ ላይ ቢደርሱም አልተሳሳቱም፡፡
ግዜዎን ቆጥበውና በአገልግሎቱ ረክተው በመውጣትዎ ‹‹መሶብ የሀገራችንን የመንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በእጅጉ ልቆ የታየበት ማዕከል ነው›› ብለው ቢመሰክሩም ፍፁም ትክክል ነዎት!

Read More »
News

የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች የሚያስተዋውቅ ፌስቲቫል ..

የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች የሚያስተዋውቅ ፌስቲቫል
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ የምግብ አይነቶች በሆቴሎች የምግብ ሜኑ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በጥናት ለይቶ ያቀረባቸው 31 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ የምግብ ፌስቲቫል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ፣በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ከኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል ።
ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የባህላዊ ምግቦች ፌስቲቫል ጥቅምት 1/2018 የኢትዮጵያውያንን ባህላዊ ምግቦች ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
መስከረም 28/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

Read More »
News

ሚኒስቴሩ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሠራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ሚኒስቴሩ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሠራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዓመታዊ የቤተሰብ ቀን በዛሬው እለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ተሳትፈዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ሚኒስቴሩ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሠራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
በመሆኑም የሥራና ክህለሎት ሚኒስቴር የቤተሰብ ቀን ማክበር የተፈለገው የእርስ በእርስ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር ሠራተኛው ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ቤተሰቡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብም ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሚኒስቴሩ እስካሁን ካሳካቸው ስኬቶች በላይ በቀጣይ ሰፋፊ ስራዎች ከፊት ለፊቱ መኖራቸውን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይም ሠራተኛው ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ቤተሰቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሚኒስቴሩም ሰራተኛውና ቤተሰቡን ለማገዝ እና ችግሮቻቸውን ለማቅለል የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በሚኒስቴሩ እና በተጠሪ ተቋማት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን መጎብኘትን ጨምሮ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የሥራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

Read More »
News

የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት…

የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክቡር ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት – የልህቀት ብስራት በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አስር የክልል ቢሮዎች እና አራት ከፌዴራል ተቋማት 42 የሚሆኑ ገልግሎቶች ወደ ሥራ ይገባሉ፡፡
ወደ ሥራ ከገባው የባህዳር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተጨማሪም በደሴ እና በጎንደር ማዕከላቱ እየተፋጠኑ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ካስገባቸው አገልግሎቶች መካከል የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ አገልግሎት ይገኝበታል፡፡
በዚህም የሥራ ፍቃድ ዕድሳት፣ የሥራ ፈቃድ መተካት እና የሥራ ፈቃድ ክሊራንስ የሚሰት ሲሆን የኦንላየን የኢንተርፕራይዝ ምስረታ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶች ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት ፈጣን፣ ቀልጠፋ እና ምቹ አገልግሎት ለዜጎች ለመስጠት ወደ ስራ የገባ ማዕከል ነው፡፡

Read More »
News

የምን ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ? 🔹

የምን ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ? 🔹
የቴክኖሎጂ 🖥️፣ የውበት 💄፣ የአውቶሞቲቭ 🚗፣ የፈርኒቸር 🪑፣ የሆቴልና ቱሪዝም 🏨፣ የኮንስትራክሽን 🏗️፣ የፋሽን ዲዛይን 👗 ወይስ ሌላ? 🔧
ፍላጎትዎን እውን ያደርጉ ዘንድ የቴክኒክና ተቋሞቻችን (TVET) ሙሉ ዝግጅታቸውን አጠናቀው እርስዎን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ✅
አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቴክኒክና ሙያ ተቋም በመሄድ ፍላጎቶን እውን ማድረግ የሚያስችልዎትን ስልጠና ያግኙ።✨
እጀ-ወርቅ ባለሙያ ሆነው የነገ መዳረሻዎን እራስዎ ይወስኑ! 🥇

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top