
የልል ክህሎት(soft skills) ግንባታ- ለሥልጠና ጥራት
የልል ክህሎት(soft skills) ግንባታ- ለሥልጠና ጥራት
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በየሳምንቱ የሚያካሂደው የጥናትና ምርመር መርሃ ግብር በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሥርዓት ውስጥ የልል ክህሎት(soft skills) ግንባታ አስፈላጊነት ላይ ያተኮሩ የዳሰሳ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በጥናቱ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ስርዓት በሚጠበቀው ደረጃ ያለመሆኑ በዋነኛነት በስልጠና ሥርዓቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ተገልጿል፡፡
በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ላለፉት 20 አመታት የእንግሊዘኛ ትምህርት ከስልጠና ፕሮግራምነት ውጪ ሆኖ መቆየቱ የሰልጣኞች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ዝቅተኛ እንዲሆን እንዳደረገውና ይህም ለዘርፉም ዋነኛ ተግዳሮት ሆኖ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡
ሰልጣኞች የቋንቋ ክህሎት ላይ የሚታየው ክፍተት በእንግሊዘኛ የሚዘጋጁ የትምህርት መርሃግብሮችን፣ መመሪያዎች እና ቴክኒካል የሆኑ ቃላቶችን ለመረዳት አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን ይህም በስልጠና ጥራት ላይ ጉልህ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ተብራርቷል፡፡
በመሆኑም ከሥልጠና ዘርፎች ጋር ሊጣጣም የሚችል የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ አጠቃላይ የስልጠና ሂዱቱን መደገፍ የሚያስችል አሠራር መዘርጋት እንደሚኖርበትም ምክረ ሃሳብ ቀርቧል፡፡








