Mols.gov.et

አምስቱ የዩኒቨርሲቲ የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር አሽናፊዎች ተሸለሙ

ሰኔ 16, 2022
በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተባባሪ አካላት ሲካሄድ የቆየው ውድድር የግብርና ውጤቶችን በኢንዱስትሪ ማዘመንን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ውድድሩ ሲጠናቀቅ በሥነስርዓቱ ላይ ተገኘተው የመነሻ ገንዘብ ሽልማቱን ያበረከቱት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የአገራችን የጀርባ አጥንት የሆነውን እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዓመት 44 ከመቶ ሥራ ለመፍጠር የሚያቅድበት የግብርና ዘርፍ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ህይወት ለማቃለል ያለመ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር በመካሄዱ አዘጋጆቹን እና አስተባባሪዎቹን አመስግነዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የቀለም ብቻ ሳይሆኑ ዕውቀት እና አመለካከት የሚቀረጽባቸው እንደመሆናቸው የወጣቶቹ ሃሳቦች ወደሥራ እንዲያድጉ በማሰልጠን እና በመደገፍ ላይ ያሉትን በማበረታታት ሌሎችም የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ኢትዮጵያ ሃሳቦች ተወዳድረው የሚያሸንፉባት እንድትሆን ተባብረን መስራት አለብን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ አምስቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው ብር 230ሺህ የሥራ ማስጀመሪያ ገንዘብ እና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡ አሸናፊ የሆኑት የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሃሳቦች ከተረፈ ምርት ማዳበሪያ ያመረቱ ፣ከቀርከሃ ብስክሌት የሠሩ፣ የእንስሣት መኖ ከተረፈ ምርቶች ያዘጋጁ፣ ከቡና ቅጠል በዘመናዊ መልክ ሻይ ቅጠል ያመረቱ እና ከእንሰት ስታርች እና የተለያዩ ምግቦችን ያቀረቡ ናቸው፡፡
amAM
Scroll to Top