Mols.gov.et

bini

ዜና

በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳታፊነት ዕውን ማድረግ ቀዳሚው አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳታፊነት ዕውን ማድረግ ቀዳሚው አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሴቶችና የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም›› በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
ፎረሙ አፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶች በፍጥነት እያደገ ከሚገኘው ዲጂታል ኢኮኖሚ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ያተኮረ ነው፡፡
በፎረሙ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ሰፊ የወጣት ቁጥር ተጠቅማ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳታፊነት ዕውን ማድረግ ቀዳሚው አጀንዳ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቶችን የዲጂታል ቢዝነስና የፋይናነስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በቀጣይም ከግል ዘርፎችና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር የኢትዮጵያውያን ኢንተርፕሪነሮችን ስኬታማነት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችሉ ዕቅዶች መነደፋቸውን አብራተዋል፡፡
በተለያየ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማሳደግና በማስፋት ረገድም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አበረታች የሆኑ ተሞክሮዎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ክቡር አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል፡፡
የሴቶችና ወጣቶች የፋይናነስ ተጠቃሚነት 2030 ሙሉ ለሙሉ እውን ለማድረግ የተያዘው ዕቅድም( WYFIE 2030) ሆነ አፍሪካውያን በጋራ የሚገበያዩበት ዲጂታል ፕላትፎርም (Sokokuu-Africa) ለማልማት እየተደረገ ካለው ጥረት ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
የአፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ከሚያደርገው ውይይት ጎን ለጎን ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተካሂዷል፡፡

Read More »
ዜና

የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ለምርታማነት!

የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ለምርታማነት!
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከክርክር ይልቅ ምክክርን ያስቀደመ የኢንዱስትሪ ባህል ለመገንባት አዳዲስ ሀሳቦችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ምክክሩ በኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚከሰቱ ግጭቶች እልባት ከመስጠት እንዲሁም የአሠሪና ሠራተኛን ግንኙነት አሻሽሎ ሁለንተናዊ የኢንዱስትሪ ሰላምን ከማምጣትና ምርታማነትን ከማሳደግ የላቀ ግብ ያለው ነው፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገራችን በሥራ ባህል ዙሪያ ያሉ የአመለካከት ማነቆዎችን በመሻገር እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ፀጋዎች አሟጦ መጠቀምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥን ዓላማው ያደረገ የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
በዚህም የምክክር መድረኩን የሚያመቻቹ የአመቻቾች ስልጠና በየክልሉ ተሰጥቷል፡፡
ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ አስተዳደር የአመቻቾች ስልጠና ከወሰዱ በመኋላ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ ተግባራዊ እያደረጉት ይገኛል፡፡
የተጀመረው የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይቱ በሥራ ባህል ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት በየአካባቢው የሚገኙ መልካም ዕድሎችን ተጠቅሞ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Read More »
ዜና

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች ከተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በአዲስ መልክ እየተከለሱ በሚገኙት የቴክኒክና ሙያ አዋጅና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
ውይይቱን የመሩት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ከዓመታት በፊት ሥራ ላይ የዋሉት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አዋጅና ስትራቴጂዎች ለዘርፉ መሰረት መጣል ያስቻሉ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን ወቅታዊ ከሆነው ሀገራዊ ፍላጎትና የአሠራር ስርዓት አንፃር መሻሻል ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች ተለይተው እየተሠራባቸው ቆይቷል።
ይህም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥና ዘመኑን የዋጀ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አስተዳደርን ማብቃት፣ ሥልጠና ጥራትንና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ ተፈላጊነትን ማሳደግና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ስነ -ምህዳር መገንባት የአዲሱ ስትራቴጂ ዋንኛ ምሰሶዎች መሆናቸው በመድረኩ በቀረበው ገለፃ ላይ ተብራርቷል፡፡
በቀረበው ገለፃ በእያንዳንዱ ምሰሶ ውስጥ የተካተቱ ቁልፍ ጉዳዮች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ከፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች፣ ከተቋማት አደረጃጀት፣ ከባለድርሻ አካላት ቅንጅት፣ ከፋይናንስ ስርዓት፣ ከስልጠና ጥራት ፣ከተደራሽነትና ተያያዥ ጉዳዮች አንፃር ሊታዩ የሚገቡ ሃሳቦች በተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂው ከአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ራዕይና ተልዕኮ ጋር መተሳሰር እንደሚኖርበት በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Read More »
ዜና

ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲጓዙ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል

ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲጓዙ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን “ህጋዊ መንገድን እናበረታታ” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በሕገ-ወጥ መንገድ የሚከናወን ስደት በዜጎች ላይ የተለያዩ አደጋዎችን እያደረሰ ይገኛል፡፡
ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ የሚያደርጉት ጉዞ በሕገ ወጥ ስደት የሚደርስባቸውን እንግልት ከመቀነስ በተጨማሪ በላኪና በተቀባይ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት ነው።
መንግሥት ዜጎች በአስተማማኝ እና በሕጋዊ መንገድ ወደ የተለያዩ ሀገራት እንዲጓዙ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህም ዜጎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከመመልመል አንስቶ የሥራ ላይ ሥልጠና በመስጠት ብቁ በማድረግ ወደ ውጭ ሀገራት እንዲጎዙ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡
መንግስት ዜጎች በሄዱበት ሀገር ክብራቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ከአጋር አካላት ጋር የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ዋና ተጠሪ አቡባቱ ዋኔ በበኩላቸው ስደተኞች በሕጋዊ መንገድ ወደ የተለያዩ ሀገራት መጓዛቸው ዘላቂ እድገት ለማምጣት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
በሕጋዊ መንገድ የሚደረግ ጉዞ ስደተኞች መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
ሀገራት ዜጎቻቸው በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲጠቀሙ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበው አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለውጤታማነቱ በጋራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ ህገ ወጥ ስደትን በመከላከል ህጋዊ ስደትን ለማበረታታት እያከናወነችው ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ እንደሚሰራ መገለፁን ኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

Read More »
ዜና

‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም››

ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተሰታፊ የሆነበት የሴቶችና የወጣቶች የፋይናንስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም›› በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ፎረሙ አፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶች በፍጥነት እያደገ ከሚገኘው ከዲጂታል ኢኮኖሚ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ በዋነኝነት በማተኮር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Read More »
ዜና

በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማትን አስፍቶ መተግበር ይገባል- ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማትን አስፍቶ መተግበር ይገባል-
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
በአፋር ክልል እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማት አስፍቶ መተግበር እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አሳሰቡ።
በሚኒስትሯ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ አሮሮ ላፍ ቀበሌ የሚገኘውን የእንሰሳት መኖ ልማት ምልከታ አከናውኗል።
በወቅቱም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንዳሉት በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማት አስፍቶ መተግበር ይገባል።
ክልሉ በእንስሳት መኖ ልማት ረገድ እምቅ ሃብት ያለው መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀው፥ እንደ አገር የወተት ልማት ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ የሚኖረው ሚና የጎላ በመሆኑ በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ መናገራቸውን የኢዜአ መረጃ ያመለከታል፡፡

Read More »
ዜና

በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአፋር ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በመመልከት ላይ ናቸው፡፡
በመስክ ምልከታው ኪልበቲ ረሱ አፍዴራ ወረዳ የጨው ፋብሪካዎችንና የአፍዴራ የጨው ሀይቅን ጨምሮ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ላይ ክብርት ሚኒስትር ባስተላለፉት መልዕክት ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ሀብት እና የቱሪዝም መስህቦች እንዳሉት ጠቅሰው ይህን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል ብለዋል፡፡
እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ የማዕድንና የቱሪዝም ዘርፉን ጨምሮ የክልሉ የልማት አቅሞች ለበርካታ የክልሉ ወጣቶች ሥራ መፍጠር እንደሚያስችሉ ጠቅሰዋል፡፡
ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የልማት ሥራዎችን የበለጠ ማስፋት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም የባለድርሻ እና አስፈፃሚ አካላት በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ያሳሰቡት ክብርት ሚኒስትር ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን መጠቀም እንደሚገባም ገልፀዋል
ከልማት ሥራዎቹ ከጉብኝት በኋላም ከወረዳዎች፣ ዞኖችና የክልሉ አመራርና የህብረተሠብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።

Read More »
ዜና

ሚኒስቴሩ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል አስተዳዳር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ

ሚኒስቴሩ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል አስተዳዳር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ ከተወካዮቹ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ዘርፍ በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ መካከል የተፈረመውን የሁለትዮሽ ስምምነት አተገባበርና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዓላማው ባደረገው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ስልጠናና ምዘና ድረስ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ አብራርተዋል፡፡
ሥራውን ይበልጥ ለማዘመንና ከብልሹ አሰራር በማጽዳት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለሥራ ገበያው ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴታው ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል አስተዳዳር ተወካዮች ጋር የተጀመረው ተቀራርቦ የመስራት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያ ተወካዮች በበኩላቸው እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን አድንቀው ከመነሻ እስከ መዳረሻ ድረስ ያለውን ሂደት ጤናማ በማድረግ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

Read More »
ዜና

ኢንስቲትዩቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ተጠቆመ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኢኒስቲትዩቱ ለሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በሥልጠናው የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት፤ የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ተወዳዳሪና የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ነው።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን በዚህ መሰረትም ኢኒስቲትዩቱ እስካሁን ለበርካታ ዜጎች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠት ችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ላለው የሥራ ገበያ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
በስልጠናው ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች እንደተካፈሉም ገልፀዋል፡፡
በዚህ በጀት አመት 150 ሰልጣኞች በሦስት ዙሮች የሰለጠኑ ሲሆን የተሰጠው ሥልጠና በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በምግብ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር መሆኑንና ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን ስልጠና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ አመራሮች ጠቁመዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሥልጠና እና የተቋማት አቅም ግንባታ ዴስክ ሀላፊ አቶ ተመስገን በቀለ በሦስተኛው ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስልጠናውን ያገኙ አሰልጣኞች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ እንደሀገር የተሰጣቸውን ኃለፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
amAM
Scroll to Top