Mols.gov.et

bini

ዜና

ሚኒስቴሩ ካጉል(kagool) ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ፡፡

ሚኒስቴሩ ካጉል(kagool) ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ ካጉል ዓለም አቀፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅት በኢትዮጵያ በአይሲቲ ዘርፍ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም የኮደርስ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ በዘርፉ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ዜጎች ድርጅቱ የሚሰጠውን ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ በስመ ጥር የቴክኖሎጂ ተቋማት በአውት ሶርሲንግ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኘው ሰፊ የወጣት ሀይል፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና፣ በርካታ የስልጠና ተቋማት መኖር እና በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ኩባንያው በኢትዮጵያ በዘርፉ እንዲሰማራ ሳቢ ምክንያቶች እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

Read More »
ዜና

ሚኒስቴሩ በቴክኖሎጂ ታግዞ ፈጠራን፣ ጥራትንና ፍጥነት አስተሳስሮ እየሠራ ያለበት መንገድ የሚደነቅ ነው፡፡ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ

ሚኒስቴሩ በቴክኖሎጂ ታግዞ ፈጠራን፣ ጥራትንና ፍጥነት አስተሳስሮ እየሠራ ያለበት መንገድ የሚደነቅ ነው፡፡
የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የተመራ የምክር ቤቱ ጉዳዮች አማካሪና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የሠው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማቱ የሥራ ምልከታ አድርገዋል፡፡
በምልከታው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በተጠሪ ተቋማቱ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ሥራዎች ታይተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባለፉት ሦስት ዓመታት ሚኒስቴሩ ያከናወናቸውን የሪፎርም ሥራዎች አስመልክተው ለምክር ቤቱ ኮሚቴ አባላት ማብራርያ እና ገለጻ አድርገዋል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሚኒስቴሩ እጅግ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የተበታተነውን የሰው ሀይልና ሀብት አደራጅቶ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቁመው ለዚህም በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጠራን፣ ጥራትንና ፍጥነትን አስተሳስሮ እየሠራ ያለው ሥራ ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ የታዩት ሥራዎች ብልጽግናን እውን ለማድረግ የተቀመጡ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች እየተተገበሩ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የጠቆሙት የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ ምክር ቤቱ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ በሚያስፈልገው ጉዳች ላይ ለማገዝ ግንዛቤ እንዲኖረው ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

Read More »
ዜና

ከንብ ትጋት የተቀሰመ ጣፋጭ ስኬት

ከንብ ትጋት የተቀሰመ ጣፋጭ ስኬት
ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ የሆነው አቶ አብዱልቃድር ሁሴን እብራሂም ከዓመታት በፊት ከተማረው ኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ጋር የተያያዘ ሥራ ላይ ነበር የተሰማራው፡፡
የሥራው ባህሪ ሆኖ ረጅም ሰዓት ተቀምጦ መቆየቱ የሚያመጣውን የሰውነት ክብደት እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ለመከላከል በቀን የተወሰነ ሰዓት ጎንበስ ቀና ብሎ ሊሠራው የሚችለውን ሥራ ማሰብ ጀመረ፡፡
በቤተሰቦቹ ግቢ ውስጥ አትክልትና ፍራፍሬ ማልማት በሃሳቡ ከመጡ ሥራ አይነቶች መካከልም ቀዳሚው ነበር፡፡ ሥራውን እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር በመውሰድ ቲማቲም፣ ጎመን ቃሪያ የመሳሰሉ የጓሮ አትክልቶችንና እንደ ብርቱካንና ሎሚ የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን ማልማት ጀመረ፡፡
እንደ ቀላል የጀመረው ሥራ እያደገና እየተስፋፋ ሲሄድ ከቤተሰብ ፍጆታ አልፎ የገቢ ምንጭም መሆን ከመቻሉም በላይ አቶ አብዱልቃድር ለግብርና ሥራዎች ምን ያህል ፍቅርና ፍላጎት እንዳለውም ጭምር ያስተዋለበት አጋጣሚ ነበር፡፡
የመኖሪያ ግቢው በአትክልትና ፍራፍሬ ሙሉ በሙሉ ሲሸፈን ደግሞ ከግብርና ባለሙያዎች ባገኘው ምክር አንድ የንብ ቀፎ ገዝቶ ወደ ንብ ማነብ ሥራ ገባ፡፡
አቶ አብዱልቃድር ለንብ ማነብ ሥራው አዲስ በመሆኑ ሥራውን በጀመረበት ወቅት በጣም ተቸግሮ እንደነበርና የሚጠበቀውን ያህል የማር ምርት እንዳላገኘም ይናገራል፡፡ ይህን ክፍተት ለመሙላት በንብ እርባታ ላይ የተፃፉ ፅሁፎችንና የሬድዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን መከታተል እንዲሁም ከባለሙያዎች ጋር መመካከር የዕለት ተዕለት ተግባሩ ሆነ፡፡
በሥራው ላይ ያለው ዕውቀት እየጨመረ ሲመጣም በቅድሚያ አስር ባህላዊ ቀጥሎም ወደ ዘመናዊ የሚያሻግሩ 15 ቀፎዎችን እና 2 ዘመናዊ ቀፎዎችን ገዝቶ የንብ ማነቡን ሥራ በሰፊው ተያያዘው፡፡
በጊዜ ሂደትም ዘመናዊ ቀፎዎችን መጠቀም ምርታማነትም ሆነ ጥራት ለመጨመር የሚያስችል መሆኑን በመረዳቱ በ50 ዘመናዊ እና በ27 የሽግግር (የባህላዊና ዘመናዊ ቀፎ ባህሪን አጣምረው የያዙ) ቀፎዎችን በመጠቀም በዓመት አስከ 100ኪ.ግ የሚደርስ ማር ማምረት ቻለ፡፡
‹‹የሙያ ፍቅርና የቢዝነስ ክህሎት›› አንድ ላይ ሲጣመሩ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለው አቶ አብዱልቃድር ለንብ ማነብ ሥራ ያደረበትን ጥልቅ ፍቅር በስኬታማ ቢዝነስ ለመደገፍ የሚስችሉትን አማራጮች ዘወትር ከማማተር ወደኋላ ብሎ አያውቅም፡፡
ባካሄደው ጥልቅ ምልከታም ምንም እንኳን ድሬዳዋ ሞቃታማ የአየር ፀባይና በአካባቢው የሚበቅሉ እፅዋት ለንብ ማነብ ሥራ ምቹ ቢሆንም በአካባቢው በቂ የንብ መንጋ የማግኘት ችግር መኖሩን ተገነዘበ፡፡
ንብ ማባዛትና ማከፋፈል አስመልክቶ በግል ጥረቱ ባገኘው ዕውቀት መነሻነት የንብ መንጋዎች እያባዛ ለግብርና ቢሮዎች፣ በመስኩ የሥራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶችና የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ከ7ሺ እስከ 20ሺ ብር በሚያወጣ ዋጋ ከአንድ መቶ በላይ መንጋዎችን መሸጥ እንደቻለ ይናገራል፡፡
አቶ አብዱልቃድር በአሁኑ ጊዜ ከማር ምርትና ከንብ መንጋ ሽያጭ በተጨማሪ የማር እንጀራ በመጋገር ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በሥራው ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ የአካባቢው ወጣቶች ስልጠናም ይሰጣል፡፡
ከንብ ማነብ ጋር በተያያዘ ያለውን ዕውቀትና ክህሎት ለማዳበር በየዕለቱ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ዘርፉን አስመልክተው የተዘጋጁ ፅሁፎችን እንደሚያነብ ይናገራል፡፡ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአውሮፓ ፈንድ የሚደገፍና በዘርፉ የሚሰጥ ዓለም አቀፍ ስልጠናን በኦንላይን ተከታትሎ የምስክር ወረቀት ባለቤት መሆን የቻለ ሲሆን በ2025 በዴንማርክ፣ ኮፐንሃገን በሚካሄደው ‹‹ዓለም አቀፍ የንብ ማህበረሰብ ጉባኤ›› ላይ ተሳታፊ ለመሆንም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
አማርኛ፣ ኦሮምኛ ሶማልኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው አቶ አብዱልቃድር ‹‹የምስራቅ አፍሪካ የንብ ማህበረሰብ›› ለመፍጠር የዋትሳፕ ፕላትፎርምን በመጠቀም በሶማሊያ፣ በኬኒያ፣ በኢትዮጵያና ታንዛኒያ የሚገኙ 350 በመስኩ የተሰማሩ ሶማልኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በግሉ ማሰባሰብ እንደቻለ ይናገራል፡፡ በአማራና ትግራይ ክልል ከተቋቋሙ መሰል ፎረሞች ጋር የፈጠረው ግንኙነትም አዳዲስ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም በር ከፍቶለታል፡፡
አቶ አብዱልቃድር የማር ምርት በምስራቅ አፍሪካ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው መሆኑን በመረዳቱም በሥፋት ለማምረት የሚያስችል የመሬት ጥያቄ ለድሬዳዋ አስተዳደር አቅርቦ ምላሽ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ የመሬት ጥያቄው ምላሽ ሲገኝም በዓመት 40ሺ ኪሎ ግራም ማር አምርቶ ወደ ውጭ የመላክ ዕቅድን ይዟል፡፡
ከራሱ አልፎ የአካባቢውን ማህበረሰብም ጭምር ተጠቃሚ ለማድረግ ለአርሶ አደሮች ተገቢውን ሥልጠና በመስጠት፣ ጥራት ያለውን የንብ መንጋ በማቅረብና የምርት ሂደታቸውን በመቆጣጠር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ዕቅድ መንደፉንም ይናገራል ፡፡

Read More »
ዜና

የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራት- ለምርታማነት

የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራት- ለምርታማነት
ሠራተኞች የሥራ ሁኔታቸውን ለማሻሻል፣ መብትና ጥቅማቸዉን ለማስከበርና የኢንዱስትሪ ሠላምን ለማረጋገጥ በማህበር የመደራጀት፣ የመመካከርና የመደራደር መብት እንዳላቸው በአለም ሥራ ድርጅት ድንጋጌ 87/1948 እና 98/1949 በግልፅ ሰፍሯል፡፡
የሀገራችን የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 113/1 ሠራተኞችና አሠሪዎች እንደአግባቡ የሠራተኞች ወይም የአሠሪዎች ማህበር ለማቋቋምና ለማደራጀት፣ የማህበር አባል ለመሆን እና በማህበር ለመሳተፍ መብት እንዳላቸው ይገልፃል፡፡
በሌላ በኩል አንቀጽ 114/3 የሠራተኛ ማህበራት በአንድ ላይ በመሆን የሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ሊመሰርቱ ይችላሉ በማለት ደንግጓል፡፡ በተጨማሪም የኢፌዲሪ አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ስልጣን ለመወሰን የወጣዉ በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 25/ ሰ/ሸ/ተ ሥር አሠሪዎችና ሠራተኞች በማህበር የመደራጀትና የኀብረት ድርድር የማድረግ መብቶቻቸውን እንዲጠቀሙ ያበረታታል፣ ይደግፋል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደራጁትን የሠራተኛና የአሠሪ ማህበራት ይመዘግባል፣
ማህበራትን ማጠናከር የሚያስገኘው ጠቀሜታ
• አሠሪና ሠራተኞች በጋራ ጥቅሞቻቸዉ ላይ በመመካከርና በመደራደር ስምምምነት ለመድረስ ይረዳል፣
• አሠሪና ሠራተኞች የሥራ ቦታቸዉን ምቹ ለማድረግ ይረዳል፣
• ዲሞክራሲያዊ ባህልን ብሎም መልካም አስተዳደርን በማዳበር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት እንዲመዘገብ አስተዋፆ ያደርጋል፤
• በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሰመረ ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙት እንዲኖር እና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ሠራተኞች ግዴታቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ ይረዳል፤
• ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ፣በሚገኘዉ ትርፍ የሠራተኛዉ ኑሮ እንዲሻሻል፣ እንቨስትመንት እንዲስፋፋና ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ያስችላል፤
• አሰሪና ሠራተኞችን ጥቅምና መብት በሚነኩ ጉዳዮች ላይ ሁለትዮሽና በሶስትዮሽ ማህበራዊ ምክከር ለማድረግ ያስችላል፤
• የሠራተኞች የሥራ ዋስትና እንዲረጋገጥ የደርጋል፡፡
የሠራተኞች በማህበር መደራጀት ምርትና ምርታማነትና ከማሳደግና የሠራተኞችንና የአሠሪዎችን መብት ከማረጋገጥ አንፃር ከላይ የተገለፁት ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ አሠሪዎች የሠራተኛ ማህበራትን በማቋቋምና በማጠናከር ረገድ ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

Read More »
ዜና

ባለፉት ሦስት ዓመታት 9.8 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ባለፉት ሦስት ዓመታት 9.8 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ባለፉት ሦስት ዓመታት 9.8 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች እውቀትን መሰረት ያደረገ ቋሚ የሥራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባለፉት ሶስት ዓመታት መንግስት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማሳለጥ ብሎም የሀገሪቷን ልማት ለማፋጠን የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
ብቁ የሰው ሀይልን በማፍራት ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ፖሊሲዎች፣ አዋጅ እና የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረጉን ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩም በእነዚህ ዓመታት በክህሎት የዳበረ አምራች ዜጋን የመፍጠር እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
እንደ ሀገር ዜጎችን ከክህሎት አኳያ ማብቃት እና የስራ እድል መፍጠር ብቻ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት የማያረጋግጥ በመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ግኑኑኝነትን ሰላማዊ ማድረግ ላይም መሰራቱን ገልጸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ብቁ እና ሙያ ያለው ዜጋን ለማፍራት የዘርፉን አሰራርና ተቋማቶችን የስልጠና አሰጣጥ ስርዓቶችን ማዘመን የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
ለላፉት ሶስት ዓመታትም አጫጭር የክህሎት ልማት ተግባራት ተጠናክረው የቀጠሉበት መሆኑን ተናግረዋል።
በባለፉት ሶስት ዓመታት ዘጠኝ ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች አጫጭር ስልጠናዎች በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት እንዲያልፉ መደረጉን አብራርተዋል።
ባለፉት ሶስት ዓመታት 9 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች እውቀትን መሰረት ያደረገ ዘላቂ የስራ እድል መፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የገበያ መረጃ ስርዓት ቴክኖሎጂ ዘርፉን ሙሉ በሙሉ በማዘመን የመረጃውን ተአማኒነት እንደሚያሳድገው አክለዋል።
ኢትዮጵያዊያን የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን ስራ ጠባቂ ከመሆን ይልቅ ስራን በራስ መፍጠር የሚያስችላቸውን አቅም ሊያጎለብቱ እንደሚገባ መግለፃቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡

Read More »
ዜና

ኢንስቲትዩቱ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት የቴክኒክና ሙያ ማዕከል (UNEVOC) አባል ሆነ

ኢንስቲትዩቱ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት የቴክኒክና ሙያ ማዕከል (UNEVOC) አባል ሆነ፡፡
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት የቴክኒክና ሙያ ማዕከል (UNEVOC) የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩትን አባል አድርጎ መቀበሉን አስታወቀ።
ማዕከሉ አባል ሀገራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ከመደገፍ ባለፈ የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች መፍጠር፣ የፈጠራ ፕሮጀክቶች መደገፍ፣ የአለም አቀፍ የእውቀትና ክህሎት ሽግግር እንዲሁም ትስስር እንዲፈጥሩ ዕድሎችን ይፈጥራል፡፡

Read More »
ዜና

ተስፋ ሰጪው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት …

ተስፋ ሰጪው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት …
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተሰጠው ተልዕኮ አንዱና ዋነኛው የማክሮ ኢኮኖሚው ትልቁ ፈተና የሆነውን የሥራ አጥነት ምጣኔን በዘላቂነት መቀነስ ነው፡፡
በዚህም ፈጠራና ፍጥነት የታከለባቸው ሥራዎችን በየደረጃው ተግባረዊ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም መታየት ጀምረዋል፡፡
ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት መርሃ ግብር ተጠቃሽ ነው፡፡
በዘርፉ የአምስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ የኦሮሚያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው በሰጠው ትኩረትና ተግባዊ እየተደረገ ባለው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት ፕሮግራም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቶበታል፡፡
በክላስተር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው በዚህ ፕሮግራም ከ3ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ከመቶ ሺህ በላይ ወጣቶችንም የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም አመላክተዋል፡፡
በክልሉ እየተተገበረ የሚገኘው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት ሥራ በስንዴ ልማት፣ በጎጆ ኢንዱስተሪ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በቅመማ ቅመም፣ በአሳ እርባታ፣ በከብት ማድለብና መሰል ክላስተሮች ተለይተው እንደሆነ ያመላከቱት ምክትል ኃላፊው የክልሉ መንግስት የተለያዩ መንግስታዊ ድጋፎች እያደረገ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Read More »
ዜና

ሪፎርሙ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በየዘርፉ ያስቀመጥናቸው ግቦች የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ በመሆናቸው በልዩ ንቅናቄ ወደ ሥራ ማስገግባት ያስፈልጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከዘርፉ አመራሮች ጋር ሲያካሂድ የነበረውን መድረክ አጠናቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፉት አምስት ወራት ከክልል ክልል የአፋጻጸም ልዩነት ቢስተዋልም እጅግ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በየዘርፉ ያስቀመጥናቸው ግቦች የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ በመሆናቸው በልዩ ንቅናቄ ወደ ሥራ ማስገግባት ያስፈልጋል፡፡
በፍጥነት ማጠናቀቅና በጥራት ማከናወን ደግሞ የቀሪ ወራት ሥራዎቻችን መለኪያዎች ይሆናሉ ብለዋል።
ከውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አኳያ ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም ዜጎችን በጥራት አሰልጥኖ ማዘጋጀት ልዩ ትኩረት ይሻል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት መተግበር፣ ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስራዓት ላይ ተመዝግዘው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ማድረግ፣ የእሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን ተግባራዊ ማድረግ፣ የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና፣ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ቢዝነስን ማስፋት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑም አመላክተዋል።
ከክህሎት ልማት አኳያ መደበኛ እና አጫጭር ስልጠና ቅበላ፣ የተቋማት ኢንተርፕሪነሪያላይዜሽን፣ ኢንተርፕራይዝ ምስረታ እና የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማቋቋም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደሆኑም ነው ክብርት ሚኒስትር የጠቆሙት፡፡
የኢንዱስትሪ ሰላምን፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ማረጋገጥ እንዲሁም ማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን አጠናክሮ ማስቀጠል ከአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍ አኳያ በቀጣይ በልዪ ትኩረት መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

Read More »
ዜና

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የሪፎርም ሥራዎች እና…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የሪፎርም ሥራዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ የዘርፉ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም የሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ምክክር በማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአዲስ አበባ በተጀመረው በዚህ መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት፣ የክልልና የከተማ አስተዳድሮች ቢሮ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Read More »
ዜና

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሪፎርም ሥራዎች

መድረኩ በበጀት ዓመቱ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጠን ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ያዘጋጀውን የውይይት መድረክ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት መድረኩ በበጀት ዓመቱ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጠን ነው፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ወርዶ ስራዎችን እንደተመለከተ ገልጸው በዚህም ከሀገራዊ ሪፎርም ጋር በተጣጣመ መልኩ ሚኒስቴሩ ያወረዳቸው የሪፎርም ሥራዎች ፍሬ ማፍራት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡
በድጋፍና ክትትል ቡድኑ እና በዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ከቦታ ቦታ የአፈጻጸም ልዩነት መኖሩን በግልጽ መታየቱን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይ እነዚህን ተቋማት ወደ ተቀራረበ አፈጻጸም ለማምጣት በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት፣ ከተቋም ግንባታ፣ ከሙያ ብቃት ምዘና አኳያ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ ከውይይቱ ባሻገር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አካል የሆኑና የማበልፀግ ሥራቸው የተጠናቀቁ የዲጂታል ስርዓቶች ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
amAM
Scroll to Top