Mols.gov.et

bini

News

ተስፋ ሰጪው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት …

ተስፋ ሰጪው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት …
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተሰጠው ተልዕኮ አንዱና ዋነኛው የማክሮ ኢኮኖሚው ትልቁ ፈተና የሆነውን የሥራ አጥነት ምጣኔን በዘላቂነት መቀነስ ነው፡፡
በዚህም ፈጠራና ፍጥነት የታከለባቸው ሥራዎችን በየደረጃው ተግባረዊ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም መታየት ጀምረዋል፡፡
ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት መርሃ ግብር ተጠቃሽ ነው፡፡
በዘርፉ የአምስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ የኦሮሚያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው በሰጠው ትኩረትና ተግባዊ እየተደረገ ባለው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት ፕሮግራም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቶበታል፡፡
በክላስተር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው በዚህ ፕሮግራም ከ3ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ከመቶ ሺህ በላይ ወጣቶችንም የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም አመላክተዋል፡፡
በክልሉ እየተተገበረ የሚገኘው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት ሥራ በስንዴ ልማት፣ በጎጆ ኢንዱስተሪ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በቅመማ ቅመም፣ በአሳ እርባታ፣ በከብት ማድለብና መሰል ክላስተሮች ተለይተው እንደሆነ ያመላከቱት ምክትል ኃላፊው የክልሉ መንግስት የተለያዩ መንግስታዊ ድጋፎች እያደረገ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

ሪፎርሙ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በየዘርፉ ያስቀመጥናቸው ግቦች የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ በመሆናቸው በልዩ ንቅናቄ ወደ ሥራ ማስገግባት ያስፈልጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከዘርፉ አመራሮች ጋር ሲያካሂድ የነበረውን መድረክ አጠናቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፉት አምስት ወራት ከክልል ክልል የአፋጻጸም ልዩነት ቢስተዋልም እጅግ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በየዘርፉ ያስቀመጥናቸው ግቦች የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ በመሆናቸው በልዩ ንቅናቄ ወደ ሥራ ማስገግባት ያስፈልጋል፡፡
በፍጥነት ማጠናቀቅና በጥራት ማከናወን ደግሞ የቀሪ ወራት ሥራዎቻችን መለኪያዎች ይሆናሉ ብለዋል።
ከውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አኳያ ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም ዜጎችን በጥራት አሰልጥኖ ማዘጋጀት ልዩ ትኩረት ይሻል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት መተግበር፣ ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስራዓት ላይ ተመዝግዘው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ማድረግ፣ የእሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን ተግባራዊ ማድረግ፣ የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና፣ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ቢዝነስን ማስፋት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑም አመላክተዋል።
ከክህሎት ልማት አኳያ መደበኛ እና አጫጭር ስልጠና ቅበላ፣ የተቋማት ኢንተርፕሪነሪያላይዜሽን፣ ኢንተርፕራይዝ ምስረታ እና የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማቋቋም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደሆኑም ነው ክብርት ሚኒስትር የጠቆሙት፡፡
የኢንዱስትሪ ሰላምን፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ማረጋገጥ እንዲሁም ማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን አጠናክሮ ማስቀጠል ከአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍ አኳያ በቀጣይ በልዪ ትኩረት መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የሪፎርም ሥራዎች እና…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የሪፎርም ሥራዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ የዘርፉ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም የሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ምክክር በማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአዲስ አበባ በተጀመረው በዚህ መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት፣ የክልልና የከተማ አስተዳድሮች ቢሮ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሪፎርም ሥራዎች

መድረኩ በበጀት ዓመቱ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጠን ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ያዘጋጀውን የውይይት መድረክ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት መድረኩ በበጀት ዓመቱ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጠን ነው፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ወርዶ ስራዎችን እንደተመለከተ ገልጸው በዚህም ከሀገራዊ ሪፎርም ጋር በተጣጣመ መልኩ ሚኒስቴሩ ያወረዳቸው የሪፎርም ሥራዎች ፍሬ ማፍራት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡
በድጋፍና ክትትል ቡድኑ እና በዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ከቦታ ቦታ የአፈጻጸም ልዩነት መኖሩን በግልጽ መታየቱን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይ እነዚህን ተቋማት ወደ ተቀራረበ አፈጻጸም ለማምጣት በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት፣ ከተቋም ግንባታ፣ ከሙያ ብቃት ምዘና አኳያ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ ከውይይቱ ባሻገር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አካል የሆኑና የማበልፀግ ሥራቸው የተጠናቀቁ የዲጂታል ስርዓቶች ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Read More »
News

በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳታፊነት ዕውን ማድረግ ቀዳሚው አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳታፊነት ዕውን ማድረግ ቀዳሚው አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሴቶችና የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም›› በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
ፎረሙ አፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶች በፍጥነት እያደገ ከሚገኘው ዲጂታል ኢኮኖሚ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ያተኮረ ነው፡፡
በፎረሙ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ሰፊ የወጣት ቁጥር ተጠቅማ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የሴቶችና የወጣቶችን ተሳታፊነት ዕውን ማድረግ ቀዳሚው አጀንዳ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቶችን የዲጂታል ቢዝነስና የፋይናነስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በቀጣይም ከግል ዘርፎችና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር የኢትዮጵያውያን ኢንተርፕሪነሮችን ስኬታማነት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችሉ ዕቅዶች መነደፋቸውን አብራተዋል፡፡
በተለያየ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማሳደግና በማስፋት ረገድም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አበረታች የሆኑ ተሞክሮዎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ክቡር አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል፡፡
የሴቶችና ወጣቶች የፋይናነስ ተጠቃሚነት 2030 ሙሉ ለሙሉ እውን ለማድረግ የተያዘው ዕቅድም( WYFIE 2030) ሆነ አፍሪካውያን በጋራ የሚገበያዩበት ዲጂታል ፕላትፎርም (Sokokuu-Africa) ለማልማት እየተደረገ ካለው ጥረት ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
የአፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ከሚያደርገው ውይይት ጎን ለጎን ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተካሂዷል፡፡

Read More »
News

የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ለምርታማነት!

የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ለምርታማነት!
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከክርክር ይልቅ ምክክርን ያስቀደመ የኢንዱስትሪ ባህል ለመገንባት አዳዲስ ሀሳቦችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ምክክሩ በኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚከሰቱ ግጭቶች እልባት ከመስጠት እንዲሁም የአሠሪና ሠራተኛን ግንኙነት አሻሽሎ ሁለንተናዊ የኢንዱስትሪ ሰላምን ከማምጣትና ምርታማነትን ከማሳደግ የላቀ ግብ ያለው ነው፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገራችን በሥራ ባህል ዙሪያ ያሉ የአመለካከት ማነቆዎችን በመሻገር እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ፀጋዎች አሟጦ መጠቀምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥን ዓላማው ያደረገ የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
በዚህም የምክክር መድረኩን የሚያመቻቹ የአመቻቾች ስልጠና በየክልሉ ተሰጥቷል፡፡
ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ አስተዳደር የአመቻቾች ስልጠና ከወሰዱ በመኋላ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ ተግባራዊ እያደረጉት ይገኛል፡፡
የተጀመረው የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይቱ በሥራ ባህል ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት በየአካባቢው የሚገኙ መልካም ዕድሎችን ተጠቅሞ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Read More »
News

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች ከተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በአዲስ መልክ እየተከለሱ በሚገኙት የቴክኒክና ሙያ አዋጅና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
ውይይቱን የመሩት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ከዓመታት በፊት ሥራ ላይ የዋሉት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አዋጅና ስትራቴጂዎች ለዘርፉ መሰረት መጣል ያስቻሉ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን ወቅታዊ ከሆነው ሀገራዊ ፍላጎትና የአሠራር ስርዓት አንፃር መሻሻል ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች ተለይተው እየተሠራባቸው ቆይቷል።
ይህም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥና ዘመኑን የዋጀ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አስተዳደርን ማብቃት፣ ሥልጠና ጥራትንና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ ተፈላጊነትን ማሳደግና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ስነ -ምህዳር መገንባት የአዲሱ ስትራቴጂ ዋንኛ ምሰሶዎች መሆናቸው በመድረኩ በቀረበው ገለፃ ላይ ተብራርቷል፡፡
በቀረበው ገለፃ በእያንዳንዱ ምሰሶ ውስጥ የተካተቱ ቁልፍ ጉዳዮች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ከፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች፣ ከተቋማት አደረጃጀት፣ ከባለድርሻ አካላት ቅንጅት፣ ከፋይናንስ ስርዓት፣ ከስልጠና ጥራት ፣ከተደራሽነትና ተያያዥ ጉዳዮች አንፃር ሊታዩ የሚገቡ ሃሳቦች በተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂው ከአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ራዕይና ተልዕኮ ጋር መተሳሰር እንደሚኖርበት በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Read More »
News

ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲጓዙ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል

ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲጓዙ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን “ህጋዊ መንገድን እናበረታታ” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በሕገ-ወጥ መንገድ የሚከናወን ስደት በዜጎች ላይ የተለያዩ አደጋዎችን እያደረሰ ይገኛል፡፡
ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ የሚያደርጉት ጉዞ በሕገ ወጥ ስደት የሚደርስባቸውን እንግልት ከመቀነስ በተጨማሪ በላኪና በተቀባይ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት ነው።
መንግሥት ዜጎች በአስተማማኝ እና በሕጋዊ መንገድ ወደ የተለያዩ ሀገራት እንዲጓዙ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህም ዜጎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከመመልመል አንስቶ የሥራ ላይ ሥልጠና በመስጠት ብቁ በማድረግ ወደ ውጭ ሀገራት እንዲጎዙ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡
መንግስት ዜጎች በሄዱበት ሀገር ክብራቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ከአጋር አካላት ጋር የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ዋና ተጠሪ አቡባቱ ዋኔ በበኩላቸው ስደተኞች በሕጋዊ መንገድ ወደ የተለያዩ ሀገራት መጓዛቸው ዘላቂ እድገት ለማምጣት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
በሕጋዊ መንገድ የሚደረግ ጉዞ ስደተኞች መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
ሀገራት ዜጎቻቸው በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲጠቀሙ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበው አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለውጤታማነቱ በጋራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ ህገ ወጥ ስደትን በመከላከል ህጋዊ ስደትን ለማበረታታት እያከናወነችው ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ እንደሚሰራ መገለፁን ኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

Read More »
News

‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም››

ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተሰታፊ የሆነበት የሴቶችና የወጣቶች የፋይናንስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ‹‹የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም›› በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ፎረሙ አፍሪካውያን ሴቶችና ወጣቶች በፍጥነት እያደገ ከሚገኘው ከዲጂታል ኢኮኖሚ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ በዋነኝነት በማተኮር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
oroORO
Scroll to Top