bini


ከአብሮ ማደግ እስከ አብሮ መበልፀግ …
ከአብሮ ማደግ እስከ አብሮ መበልፀግ …
መገኛው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማረቆ ልዩ ወረዳ ሆቤ በሚባል ቀበሌ ነው፤ አብሮ አደግ ኢንተርፕራይዝ፡፡
በአካባቢው በመስኖ ሥራ በተሰማሩ አልሚዎች ተቀጥረው ይሰሩ በነበሩ አብሮ አደግ ወጣቶች በገጠር የሥራ ዕድል ፈጠራ በተደራጁ ወጣቶች የተመሰረተ ነው፡፡
ወጣቶቹ የርስ በርስ መስተጋብራቸው ይበልጥ ለማጎልበት አብሮ አደግነታቸውን ወደ ብልጽግና ለመቀየር አዋጭነቱን ተነግሯቸው ሳይሆን በተግባር አልፈውበት ባረጋገጡት የመስኖ ስራ ተሰማሩ፡፡
ተቀጥረው በሚሰሩበት ወቅት ያጠራቀሙት አስር ሺህ ብር ቆጥበው አንድ መቶ ሺህ ብር ተበድረው ወደ መስኖ ስራ የገቡት እነዚህ ወጣቶች በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የጓሮ አትክልቶችን ማምረት ጀመሩ፡፡
በገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርት፣ በተሰማሩበት ሥራ የነበራቸው ክህሎት እና በሥራው የመቀየር ፍላጎታቸው ተዳምረው ወደ ውጤት ለመሸጋገር ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡
ወደ ሥራው ከተሰማሩበት ዕለት አንስቶ መንግስታዊ ድጋፍ ያልተለያቸው እነዚህ ወጣቶች አሁን ላይ ተቀጥሮ ከመስራት ወደ ቀጥሮ ማሰራት ተሸጋግረዋል፡፡ በዚህም 20 ለሚሆኑ ሥራ የሌላቸው ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እና 200 ለሚሆኑት ደግሞ ጊዚያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡
በ8 ሄክታር መሬት ላይ በስፋት የመስኖ ሥራቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት እነዚህ ወጣቶች በአሁን ወቅት አጠቃላይ ሀብታቸው 12 ሚሊየን ብር ተሻግሯል፡፡ በልማት ያስተሳሰሩት አብሮ አደግነታቸው ወደ ብልጽግና እያሸጋገራቸው መሆኑን የተመዘገበው ውጤት አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
የኢንተርፕራይዙ ሰብሳቢ አቶ ሞሳ አብራር፤ ወጣቶች በዙሪያቸው ያለውን ጸጋ ቢመለከቱ እና ተደራጅተው ወደ ስራ ቢገቡ መቀየር እንደሚችሉ እኛ አይነተኛ ማሳያ ነን ይላል፡፡ በሥራ ሂደት ውስጥ በተለያዩ ጊዚያቶች ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ቢያጋጥማቸውም ውጤት ከማስመዘገብ እንዳላስቆማቸውም ይናገራል፡፡
የአብሮ አደግ ኢንተርፕራይዝ ተግባራዊ የሥራ እንቅስቀሴ እና ለውጥ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀመረውን ቤተሰብ እና ማህበረሰብ የምርታማነት ማዕከል የማድረግ አዲሱ እሳቤን ማዕክል ያደረገ ነው፡፡


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!


በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡
ያለንን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማላቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት በውይይታቸው ላይ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ እያከናወናቸው ያሉ የሪፎርም ሥራዎችንና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችንን ከማየት ባለፈም ረዥም ጊዜ ባስቆጠረው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችንም ተመልክተናል ብለዋል ፡፡
በቀጣይም የኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳሩን ምቹ በማድረግ በተለይ የሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ጨምሮ በቀጣይ በሚለዩ የትብብር መስኮች ላይ በጋር ለመሥራት ተግባብተናል፡፡
በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከርና በማስፋት የሁለትዮሽ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነትም አመስግነዋል፡፡



