Mols.gov.et

bini

News

በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ክቡር ጁንግ ካንግ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ…

በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ክቡር ጁንግ ካንግ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡
በዚህም ልህቀት ማምጣት በሚያስችሉ የክህሎት ልማት እንዲሁም የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ተግባብተናል፡፡
ኮሪያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለኢትዮጵያ ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል እንዷ ስትሆን ትብብሩ ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ የሚያሳድገው ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያና ኮሪያ ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ክቡር አምባሳደር ጁንግ ካንግ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ!
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Read More »
News

በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡

ያለንን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማላቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት በውይይታቸው ላይ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ እያከናወናቸው ያሉ የሪፎርም ሥራዎችንና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችንን ከማየት ባለፈም ረዥም ጊዜ ባስቆጠረው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችንም ተመልክተናል ብለዋል ፡፡
በቀጣይም የኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳሩን ምቹ በማድረግ በተለይ የሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ጨምሮ በቀጣይ በሚለዩ የትብብር መስኮች ላይ በጋር ለመሥራት ተግባብተናል፡፡
በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከርና በማስፋት የሁለትዮሽ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነትም አመስግነዋል፡፡

Read More »
News

የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ የግሉ ዘርፍ፣ መሠረተ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሰለሞን ኩይኖር ከተመራው የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ በግብርናው ዘርፍ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር ለዜጎች ሰፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በኢትዮጵያና በአፍሪካ የልማት ፈንድ መካከል በተፈረመው ስምምነት መሰረት የተከናወኑ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ መመልከታቸውንና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም ማስቀመጣቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ልማት ባንክ የግሉ ዘርፍ፣ መሠረተ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሰለሞን ኩይኖር እና የልዑካን ቡድን አባላት ለስምምነቱ ተግባራዊነት እያደረጉ ላለው ጠንካራ ድጋፍና ክትትልም አመስግነዋል፡፡

Read More »
News

በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ የክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የክህሎት መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የተፈረመው ስምምነት በፍጥነት ወደ ትግበራ የሚሸጋገርበትን ሁኔታ በዝርዝር መመልከታቸውንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ስለማስቀመጣቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል ፡፡
በቅርቡ የተፈረመው ይህ ስምምነት በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ዘርፉ በርካታ ሴቶችንና ወጣቶችን የሙያ ባለቤት በማድረግ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአፍሪካ በአይነቱ ልዩ የሆነውን የክህሎት ፓርክ በመገንባት ኢትዮጵያ ለያዘችው ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዞ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
የጣሊያን ኤምባሲ ምክትል ልዕክ ኃላፊ ክቡር ሉካ ካርፒንቲየሪ፣ የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሚሼል ሞራና እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ስምምነቱን ወደ ተግባር እንዲሸጋገር እያደረጉ ላለው ያለሰለሰ ጥረትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

ሥራው ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ፀጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሥራው ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ፀጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ውስጥ ከሚካተቱ አገልግሎቶች መካከል የቨርቹዋል የኢንተርፕራይዝ ምስረታ አገልግሎት ይገኝበታል።
ይህ አገልግሎት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስርዓቱ ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ጸጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሥራው ሀገራዊ የመረጃ ስርዓትን ዘመኑን በሚዋጅ አሰራር የሚያዘምን ከመሆኑም ባሻገር ኢንተርፕራይዞች በአካባቢ ሳይወሰኑ የገበያ ድጋፍ እንዲያገኙ፣ አካታች የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና ጸጋቸውን ማዕከል ያደረገ ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል ሆኖ መበልፀጉን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ጠንካራና ተወዳዳሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ለማፍራት ዜጎችን በሥርዓቱ የመመዝገብ እና እንዲደራጁ የማድረግ ሥራ በልዩ ንቅናቄ እና በትኩረት እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡

Read More »
News

ቀጣናዊ ትስስር በክህሎት ልማት …

ቀጣናዊ ትስስር በክህሎት ልማት …
የክህሎት ልማት ሥትራቴጂና አቅጣጫችን ከሀገራዊ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና አቅጣጫዎች ጋር እንዲሰናሰል ተደርጎ የተቃኘ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ከሀገራዊው ባሻገር ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ቀጣናዊ የሙያ ብቃት ማዕቀፍ ተዘጃቶ ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡
በዚህም ዜጎች ተንቀሳቅሰው የመስራት ብቻ ሳይሆን የመሰልጠን መብታቸው እንዲከበር ለማድረግ ትልቅ ሥራ ተሰርቷል፡፡
ይህ በመሆኑም የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በሀገራችን በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለቀጣናው ሀገራት ዜጎች የስልጠና ዕድል በመስጠት ብዙዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም ሰሞኑን በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የሶማሊ ላንድ ዜጎችን አስመርቋል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ ቢሮው ከከተማው ባሻገር የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮትን በትምህርትና ስልጠናው መስክ የማዋሃድ ሥራን በልዩ ትኩረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በዚህም 45 የሚሆኑ የሶማሊ ላንድ ዜጎችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ለምረቃ ማብቃቱን ገልፀው በቀጣይም ሌሎች የቀጣናው ሀገራትን ዜጎች የሥልጠና ዕድል በመስጠት ቀጣናውን በትምህርትና ስልጠና የማስተሳሰር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የድሬዳዋና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሠለሃዲን አብዱልሃሚድ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ቀጣናውን በትምህርትና ስልጠና ለማዋሃድ በንቃት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ስልጠናቸውን አጠናቀው ለምረቃ የበቁተት የሶማሌ ላንድ ዜጎች የህዝቦች ወንድማማችነት ማሳያ ናችሁ ብለዋል፡፡

Read More »
News

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ…

ፖሊሲውን ተከትለው እየተዘጋጁ የሚገኙት የህግ ማዕቀፎች ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተቃኙ ናቸወ፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ እና ፖሊሲውን ተከትለው ተግባራዊ በሚደረጉ የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የየክልሉ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እና የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፤ በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀውን የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ እና ፓሊሲውን ተከትለው እየተዘጋጁ የሚገኙት የህግ ማዕቀፎች ሚኒስቴሩ የጀመረውን የዘርፉ የለውጥ እሳቤ ላይ ያተኮሩ እና ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ማሳካት በሚያስችል መልኩ የተቃኙ ናቸው፡፡
የሥራ አጥነት ችግር መቅረፍ የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እነዚህ ፓሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች በዘርፉ የሚታዩ የአተገባበር ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
በመድረኩ አዲሱ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ እና ፖሊሲውን ተከትሎ የሚወጡ የሕግ ማዕቀፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
somSOM
Scroll to Top