Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ

የህይወት ታሪክ

አቶ ንጉሡ ጥላሁን ገ/አማኑኤል በኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው፡፡ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነበሩ፡፡ በኮሚሽነርነት ከመሾማቸው በፊት ደግሞ በጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አቶ ንጉሡ በትምህርት ዘርፍ በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከማስተማር ጀምሮ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ፣ ም/ቢሮ ኃላፊ እና ቢሮ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚህም በመቀጠል የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጂኦግራፊ እንዲሁም ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አመራር በድህረ ምረቃ ዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢጁኬሽናል ሳይኮሎጂ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

አቶ ንጉሡ በተለያዩ ሀገራት እና በሀገር ውስጥም ባካበቱት ዕውቀት በተለይም በትምህርት እና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አስተዋፃኦ አበርክተዋል፡፡ በመንግስት የተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ህዝብን ያገለገሉት አቶ ንጉሡ በፖለቲካ ተሳትፏቸውም ከፍተኛ አስተዋፃኦ አበርክተዋል፡፡ በተለያዩ የትምህርት እና የሚዲያ ተቋማትም የቦርድ አባል ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

amAM
Scroll to Top