Mols.gov.et

mols mols

News

የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር …

የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር ቢሮው በትኩረት እየሰራ እንደሆነ አስተዋቀ
የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
የቢሮ ምክትል ኃላፊና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለዉ ከበደ እንደገለፁት፤ የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊ ዜጎች የሚመዘገቡባቸው፣ ኢንተርፕራይዞች የሚፈልቁባቸውና አስፈላጊውን መንግስታዊ ድጋፍ የሚያገኙባቸው ሥፍራዎች ናቸው፡፡
በመሆኑም ቢሮው ለሥራው ልዩ ትኩረት በመስጠት በሁሉም አካባቢ ተደራሽ እንዲሆኑ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በእስካሁኑ ሂደት ህብረተሰቡን በማስተባበር 86 የሚሆኑ አዳዲስ የሥራ ማዕከላት እየተገነቡ እንደሚገኙ ጠቁመው በቅርቡ ተጠናቀው ለሥራ ክፍት እንደሚሆኑም አስረድተዋል፡፡
ተደራሽነቱን ከማስፋት ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ ማዕከላቱን በቴክኖሎጂና በመሰረተ ልማት የማሟላትና በብቁ የሰው ሃይል እንዲደራጁ የማድረግ ሥራም እየተሰራ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ ዕድል የተቀመጡ ግቦቹን ለማሳካት ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል ሥራ ፈላጊዎችን የመመዝገብ፣ የማደራጀትና መንግስታዊ ድጋፎችን የማመቻቸት ተግባራትን የሚያከናውኑ የሥራ ማዕከላትን ማጠናከር በዋነኛነት ይጠቀሳል፡፡
በዚሁ መሰረት ማዕከላቱ ለሥራ ፈላጊ ዜጎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ማዕከላቱን ሪፎርም የማድረግ ሥራ በክልሎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

Read More Âť
News

ከ120 ሺህ በላይ ወጣቶችን ለማብቃት ያለመው ኢኒሺየቲቭ

ከ120 ሺህ በላይ ወጣቶችን ለማብቃት ያለመው ኢኒሺየቲቭ
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የሰው ኃይል ልማት ግብ ለማሳካት፤ በአማራ ክልል በ”ዲጂታል አማራ ኢንሼቲቭ” አማካኝነት ከ120 ሺህ በላይ ወጣቶችን በዲጂታል ክህሎት ብቁ ለማድረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።
ይህ መርሃ ግብር በተለይም የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ከትምህርት ቢሮ እና ከክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዴሊቨሪ ዩኒት ጋር በመቀናጀት “ዲጂታል ክህሎት ለሼል ፈጠራ እና ሙያ ልማት” በሚል መሪ ቃል በኮምቦልቻ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ ነው።
የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ ዓለሙ እንደገለጹት፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በቴክኖሎጂ በማገዝ ወጣቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በመሠራት ላይ ነው።
በዚህም ወጣቶች በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በኔትወርክ ኮንፊግሬሽን፣ በግራፊክ ዲዛይን፣ በዌብ ዲቨሎፕመንት እና በኮንቴንት ክሬሽን ዘርፎች የላቀ እውቀት እንዲጨብጡ በማድረግ የሀገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ታቅዷል።
ይህ ሥራ የሀገሪቱን ብልጽግና በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ የተቀናጀ የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ የትምህርት ጥራትና የክህሎት ሽግግርን ለማፋጠን ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት ስርዓቱ በዲጂታል አሠራር እንዲቃኝ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የICT ዳይሬክቶሬት እና በዘርፉ ባለሙያዎች የተደገፈው ይህ ንቅናቄ፣ ወጣቶች ዘመኑን የዋጀ ክህሎት እንዲታጠቁ ከማድረግ ባለፈ፣ የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የክህሎት ትስስርና የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ተግባር የሚያግዝ ነው።

Read More Âť
News

የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እያደገ የመጣ …

የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እያደገ የመጣ ቢሆንም አሁንም አሠራራችንን መፈተሽ እና ከሚመለከተው አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ይጠበቅብናል
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የአካል ጉዳተኞች፣ የህጻናት፣ የፀረ ፆታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) እና የአለም የኤድስ ቀንን በጥምረት አክብረዋል፡፡
በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ዕለቶቹን አስመልክቶ በሚተላለፉት መልዕክቶች ግንዛቤን ከመጨበጥ ባሻገር የዕለት ተዕለት ህይወታችን አካል ማድረግ እና የአስተሳሰብ ለውጥ ማስፈን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት እያደገ የመጣ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቁ ጉዳዮች በመኖራቸው አሠራራችንን መፈተሸ እና ከሚመለከተው ተቋም ጋራም ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
የክህሎት ልማት ሥራችን አካል ጉዳተኞችን በሚጠበቀው ደረጃ ማካተት እንዲችል ሥርዓተ ስልጠናችንን መፈተሽ፣ ምቹ የማሰልጠኛ መርጃ መሳሪያዎችን በተገቢው መልኩ ማደራጀትና ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ አካል ጉዳተኝነትንና ኤች አይቪ ኤድስን አስመልክቶ ከአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽንና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Read More Âť
News

የህዝብ አገልግሎቱን ፈጠራን ማዕከል ያደረገና መፍትሄ አመንጪ እንዲሆን ማስቻል

የህዝብ አገልግሎቱን ፈጠራን ማዕከል ያደረገና መፍትሄ አመንጪ እንዲሆን ማስቻል
እንደ ሀገር ምንፈልገውን ለውጥ ለማምጣት የህዝብ አገልግሎትን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከብልሹ አሠራሮች የፀዳ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ይህን መሰሉን የአሠራር ማሻሻያ ዕውን ለማድረግ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የህዝብ አገልግሎት የፈጠራ ማዕከል (public sector innovation lab) በሚል ስያሜ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።
ፈጠራን፣ አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅና አዳዲስ ሃሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ የህዝብ አገልግሎት ለመስጠት ያለመውን የዚህን ሥርዓት ተግባራዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት ግንባታን ጨምሮ የአሠራር ሥርዓት የመዘርጋትና ተገቢውን መዋቅር የማደራጀት ሥራ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ሲሠራ ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከየሥራ ክፍሉ ለተውጣጡ የተለያዩ ባለሙያዎች በቀጣይ አሠራሩን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ በሚቀጥሉት አመታት ውስጥ 500 ችግር ፈቺና መፍትሔ አመንጪ የህዝብ አገልግሎት ፈጣሪ አሸናፊዎችን መፍጠር ነው፡፡
ለአንድ ወር የሚቆየውን ይህ ስልጠና በመጀመሪያዎቹ ሦስት ቀናት የህዝብ አገልግሎት ፈጠራን በተመለከቱ እሳቤዎች (በ system thinking, feature thinking, design thinking, እና innovation ላይ) በማተኮር ይሰጣል፡፡
በቀሩት ቀናቶች ሰልጣኞች በየሥራ ክፍላቸው ውስጥ በተጨባጭ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲለዩና ፈጠራ በታከለበት መልኩ መፍትሔዎችን እንዲያመነጩ ይጠበቃል፡፡ የቀረጿቸው የመፍትሔ ሃሳቦች ከተመዘኑና ከተገመገሙ በኋላም የሃሳቡ ባለቤቶች የምስክር ወረቀት ባለቤት እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡
ስልጠናው በቀጣይም ለክልሎች፣ ለዞኖች፣ ለፌዴራል እና ለተጠሪ ተቋማት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Read More Âť
News

ኢንስቲትዩቱ ሰዎችንና ተቋማትን የሚቀይር ሥራ የሚሰራ ትልቅ የሀገር ሀብት ነው

ኢንስቲትዩቱ ሰዎችንና ተቋማትን የሚቀይር ሥራ የሚሰራ ትልቅ የሀገር ሀብት ነው
የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያደረገ የሚገነውን የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ቀጥሎ በኢንተርሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የተገኙ ውጤቶች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፣ የመስክ ምልከታው ዓላማ የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቶ ተግዳሮቶችን መፍታት እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
ከቢሮ አደረጃጀት ጀምሮ ኢንስቲትዩቱ በብዙ ቦታዎች ያልተለመደና ለሥራ ምቹ የሆነ ከባቢ መፍጠር መቻሉን አንስተው፤ አፈፃፀሙም ትልቅ ነገርን አስቦ በማቀድ፤ አቅዶም በመተግባር የሚመጣ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ሰዎችንና ተቋማትን የሚቀይር ሥራ የሚሰራ ትልቅ የሀገር ሀብት እንደሆነም የተከበሩ ዶ/ር ገልፀዋል፡፡
ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየርና ፀጋዎቻችንን በአግባቡ በማልማት እንደ ሀገር ወደፊት እንዳንሄድ ያደረጉንን እንቅፋቶች ሁሉ እንድናልፍና ወደ ግባችን እንድንደርስ የሚያደርግ በመሆኑ አቅሙን ማባዛትና ሥራውን ማስፋት እንደሚገባውም ጠቁመዋል፡፡
ሀገርና ተቋም የሚቀየረው ትክክለኛ አመራር ሲኖር ነው ያሉት የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ፤ ሰርተው የሚያሰራና የማያሰሩ ቢሮክራሲዎችን የሚገሩ አመራሮችን ለማፍራት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ቤተልሔም ላቀው በበኩላቸው፤ በተቋሙ ሪፖርት ችግር አለመቅረቡን ገልጸው ይህም ችግሮችን ወደ መልክም እድልነት የሚቀይር ተቋም መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ባልተለመደ መንገድ በመሄድ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልፀው ውጤቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት በተቋማት አመራሮች ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመላክተዋል፡፡
የኢንተርፕሪነርሺፕ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀሰን በበኩላቸው፣ ኢንስቲትዩቱ የኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳሩን በማስፋት ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር የተቋማት አመራሮችን አቅም ከማሳደግ አኳያ እያደረገ ያለውን ጥረትና የተገኙ ውጤቶችን አብራርተዋል፡፡
በኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ኢትዮጵያ ምንም ከማትታወቅበት ምራፍ ወጥታ በዚህ ዓመት በዓለም አቀፍ መድረክ የመጀመሪያ ደረጃ መያዟንም ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ የዓለማችን ታላለቅ ባለሀበቶችና ኢንቨስተሮች የሚሳተፉበትን የኢንተርፕሪነርሺፕ ኮንግረንስ ለማዘጋጀት ጥያቄ መቅረቡንም አንስተው ለስነ-ምህዳር ግንባታው ቋሚ ኮሚቴው ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

Read More Âť
News

በኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት ወደ ሼል እንዲገቡ …

በኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ
ቢሮው የወጣቶችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተግባርና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን በቅንጅት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።
“ዛሬን ለነገ” በሚል የብቃት ፕሮጀክት በአዳማ ከተማ የሥራ ላይ የተግባር ስልጠና የወሰዱ 1ሺህ 799 ወጣቶች ተመርቀዋል።
የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ እ/ር ኤባ ገርባ እንደገለፁት፤ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመቀናጀት ወጣቶችን በክህሎት ለማብቃት የአጫጭርና ረጃጅም ጊዜ ስልጠናዎች እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል።
የሥራ ላይ ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈና የወጣቶቹን የሥራ ተወዳዳሪነት ማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል።
በክልሉ የዚሁ ተግባር አካል የሆነው የወጣቶችን የሥራ ብቃት ማሳደግን ዓላማ ያደረገ “ዛሬን ለነገ” በሚል የብቃት ፕሮጀክት የሥራ ላይ ሙያዊ ስልጠና በአዳማ፤ በሻሸመኔ እና በጅማ መሰጠቱን ገልጸው፤ የዛሬው በአዳማ የተከናወነው ምረቃ የዚሁ ጥረት አካል ነው ብለዋል።
የሥራ ላይ ስልጠናውን ከወሰዱ ወጣቶች መካከል 1,799 ውጤታማ በመሆናቸው በኢንዱስትሪዎች የመቀጠር ዕድል ማግኘታቸውንም ተናግረዋል።
ዘገባው የኦሮሚያ ክልል፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ነው

Read More Âť
News

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የለውጥ ሥራው ላይ ውይይት ማድረግ ጀምረዋል፡፡
በመድረኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራዎች የተግባር ምዕራፍ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በስኬት ማጠናቁን አውስተው ይህን ስኬት ያለሠራተኛው ንቁ ተሳትፎና ርብርብ ማምጣት አይቻልም ነበር ብለዋል፡፡
ሥራው ሀገርን የመገንባት ጉዞ አንዱ አካል በመሆኑ ለብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይዞ መውጣት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም ሥራው ባለቤት ሠራተኛው ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ሁሉም ይህን ተገንዝቦ የትግበራ ምዕራፉን እቅድ በማዳበር በባለቤትነት አልቆ ለመፈፀም መዘጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የውይይት መድረክ በመደበኛውና የሪፎርም ሥራዎች የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ነገም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Read More Âť
News

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ…

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ሀገር የመሥራት ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ የሚያግዝ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆው የአፈፃፀም ግምገማ፣ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ምዕራፍ እቅድ ትውውቅ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መድረክ አመራርና ሠራተኛው ለቀጣይ ሥራዎች ያላቸውን የላቀ ቁርጠኝነት ያሳዩበት ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫና ቃለ መሐላ በመፈፀም ተጠናቋል፡፡
በማጠቃለያ ላይ የቀጣይ ሥራዎች መመሪያ የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የራሱን አዳዲስ እሳቤዎች ቀርፆ በለውጥ አስተሳሰብ መቋቋሙ የመንግስት አስተዳደር ሪፎርምን በተገቢው ደረጃ ለመተግበር መሰረት መጣሉን አስረድተዋል፡፡
አዳዲስ እሳቤዎቹ በክህሎት ልማት ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር የሪፎርሙ ትግበራው ሀገር የመሥራት ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረትም ሚኒስቴር መ/ቤቱን የጥራት አመራር (ISO 9001 : 2015) ሰርተፍኬት ባለቤት ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡
የዜጎችን ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰፋፊ ሥራዎች የሚጠብቁ እንደመሆኑ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም መደበኛ ሥራዎችን በተቀላጠፈና በተፋጠነ መንገድ በማሳካት የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
በሪፎርሙ ሂደት ራሳችንን ለማስተማር የነበረን ዝግጁነት የዝግጅት ምዕራፉን በስኬት ለማጠናቀቅ አስችሎናል ያሉት ክብርት ሚኒስትር የተግባር ምዕራፍ ሥራዎች ግልፅነትንና ባለቤትንትን በሚያጎለብት መልኩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች እንደሚተገበሩ አብራርተዋል፡፡
የሪፎርም ትግበራው ሠራተኞች በሠሩት ልክ ዕውቅና የሚያገኙበት፣ የማትጊያ ሥርዓት የሚተገበርበትና፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች የበለጠ ተጠናክረው የሚቀጥሉበት መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስረድተዋል፡፡
ሪፎረሙን በውጤታማነት መተግበር እንዲቻል ለሠራተኞች የተሰጡ የቅድመ ምዘና ውጤቶችን መሰረት ያደረጉ ሥልጠናዎች በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚሰጡና ጠንካራ የሜንቶርሺፕ ስርዓት እንደሚተገበርም ተገልጿል፡፡
የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ትግበራውን በውጤታማነት ማስቀጠል፣ ችግር ፈቺና መፍትሔ አመንጪ ሃሳቦችን በማፍለቅ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት ለመተግበር በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተቋቋመውን (public service innovation lab) የማጠናከር ሥራ በትኩረት እንደሚሠራም አሳውቀዋል፡፡

Read More Âť
News

ብሩህ ሀገር አገፍ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር መካሄድ ጀመረ

ብሩህ ሀገር አገፍ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር መካሄድ ጀመረ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከኤስ ኤን ቪ ሊዌ ፕሮግራም ጋር በትብብር ያዘጋጀው 6ኛው ሀገር አቀፍ ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የቡት ካምፕ ስልጠናና ውድድር መድረኩ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር ከአካባቢያቸው አልፈው ሀገርን የመቀየር አቅም ያላቸው፣ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ትላልቅ ሃሳቦች የሚለዩበት እና አሸናፊ የሆኑ ሀሳቦች በተደራጀ መንገድ ወደ ካምፓኒ እንዲሸጋገሩ አቅማቸው የሚገነባበት ነው ብለዋል፡፡
ባለፉት 5 ዓመታት በተካሄዱ የፈጠራ ሃሳብ ውድድሮች ከ12 ሺህ በላይ አዳዲስ ሃሳቦች በፌዴራል ደረጃ ቀርበው ችግር ፈቺና መፍትሄ አምጪ ሆነው የተገኙ 1ሺህ 350 የሚሆኑ የፈጠራ ሃሰቦች ለሽልማት መብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡
በማወዳደር እና በመሸለም የማይቆመው ብሩህ-ኢትዮጵያ፤ በውድድሩ ከተሸለሙት መካከል 580 የሚሆኑ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው በአሁን ወቅት ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር እንደቻሉም አስታውቀዋል፡፡
በዘንድርሮ ብሩህ- ኢትዮጵያ 2018 ከመላው የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ 251 የሚሆኑ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች እንደሚሳተፉ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዘርፉ ባለሙያዎች ተገምግመው የሚያሸንፉ የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ካምፓኒ እንዲሸጋገሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ለቀጣይ 10 ቀናት በሚቆየው በዚህ የቡት ካምፕ ስልጠናና ውድድር የሚሳተፉ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች ሃሰባቸውን ይበልጥ ማበልጸግ የሚያስችላቸው ስልጠና፣ የልምድ ልውውጥ እና የኢንዱስትሪ ጉብኝቶችም የተካተቱበት መሆኑን ተመላክቷል፡፡

Read More Âť
News

የሀገር ብልጽግናን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ለመደገፍና ኮትኩቶ ወደ ውጤት ለመቀየር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

የሀገር ብልጽግናን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ለመደገፍና ኮትኩቶ ወደ ውጤት ለመቀየር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች መደገፍና ወደ ውጤት መቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከፋይናንስ ተቋማት እና ከልማት አጋሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ሀገር ወደ ብልጽግና የሚያሻግሩ ትላልቅ ካምፓኒዎች ለመፍጠር መሰረት የሚጥሉ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን ለመደገፍ እና ወደ ውጤት ለመቀየር በተናጠል ከመሄድ ይልቅ ተቀናጅቶ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ብሩህ ኢትዮጵያ- የፈጠራ ሃሳቦች በሚል ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው አወዳድሮ በመለየት ወደ ፌዴራል የሚያልፉ ሀሳቦች ላይቶ የማሰልጠን፣ የመሸለም እና የማብቃት ስራ ሲሰራ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር እየፈለቁ የሚገኙ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች በርካታ ከመሆናቸው የተነሳ ሃሳቦች በሚፈለገው ልክ ደግፎ እና ኮትኩቶ ለሀገር እድገትና ብልጽግና ለመጠቀም የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ሥራውን በማገዝ ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደገባ ጠቁመዋል፡፡
ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ5 መቶ በላይ የፈጠራ ሃሳቦች መለየታቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ከነዚህ መካከል 251 የሚሆኑ የፈጠራ ሀሳቦች ከህዳር 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ አቅማቸው የሚገነባበት ቡትካምፕ ይገባሉ ብለዋል፡፡
በዘንድሮ ብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳቦች ውድድር ላይ ተወዳድረው ከሚያልፉት መካከል የተወሰኑት ሀሳባቸውን ወደ ውጤት እንዲቀይሩ በኤስ ኤን ቪ ሊዌ ፕሮግራም(SNV, LIway program) ለመደገፍ መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡
የፋይናንስ ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች ቀሪ የፈጠራ ሀሳቦች ወደ ውጤት እንዲቀየሩ በመደገፍ ሀገራዊ ሃላፊነታቸው እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
tigTIG
Scroll to Top