Mols.gov.et

mols admin

News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የ2016 ዓ.ም በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች እና የአረጋዋያን ቤት እና ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ አስጀምረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ለባቢሌ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የማሰልጠኛ ቁሳቁስ እና ለ1000 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

Read More Âť
News

ፈጠራና ፍጥነት በታከለበት መልኩ ምርታማነትን ለማረጋገጥ በዞኑ የአመራር አቅም ግንባታ ላይ በቋሚነት ድጋፍ እናደርጋለን፡፡

ፈጠራና ፍጥነት በታከለበት መልኩ ምርታማነትን ለማረጋገጥ በዞኑ የአመራር አቅም ግንባታ ላይ በቋሚነት ድጋፍ እናደርጋለን፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የ2016 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የአቅመ ደካሞችና አረጋውያን እንዲሁም የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታን አስጀምረዋል፡፡
ለባቢሌ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅም የተለያዩ የማሰልጠኛ እና 1000 ለሚሆኑ የዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በባቢሌ ወረዳ ኢፋና ጃለሌ ቀበሌ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከሁለት ሺህ በላይ የተሻሻሉ የሙዝ ችግኞችን የተከሉ ሲሆን በቀጣይ 10 ሺህ የተሻሻሉ የሙዝ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ተጠቁሟል፡፡
በባቢሌ ከተማ አስተዳደር በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈረሃት ካሚል እንደገለጹት፤ ዜጎች ሀገራቸውን እንዲያውቁ፣ አመራሩ ከህብረተሰቡ ጋር እንዲመካከርና ችግሮቹን እንዲፈታ ታሳባ በማድረግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግስት አቅጣጫ ሆኖ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
በዚህ መሰረት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በተለያዩ ክልሎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ዛሬ ያስጀመርነው መርሃ ግብር በክልሉና በዞኑ የተጀመሩ ጥረቶችን የማገዝና የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡
ፈጠራና ፍጥነት በታከለበት መልኩ ምርታማነትን ለማረጋገጥ በዞኑ የአመራር አቅም ግንባታ ላይ በቋሚነት ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ይህም ሁሉም ምርታማ የሚሆንበትን ዕድል ይፈጥራል ያሉት ክብርት ሚኒስትር በመርሃ ግብሩ የሚከናወኑ ተግባራት የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንዳልሆኑም ጠቁመዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሚስኪ መሐመድን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማቱ እንዲሁም የክልል፣ የዞንና የወረዳው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Read More Âť
News

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ሙሉ አባል ሆነች

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ሙሉ አባል ሆነች
ይህን አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትር በመግለጫቸው ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት የአባልነት ጥያቄ አቅርባ ላለፉት ሁለት አመታት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ምላሹን ስትጠባበቅ ቆይታለች፡፡
የድርጅቱ ቦርድ ሰሞኑን ባሳለፈው ውሳኔ ኢትዮጵያ የድርጅቱ 88ኛ ሙሉ አባል ሆናለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የክህሎት ድርጅት አባል መሆኗ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ እንዳለው አመልክተው ሀገራችን በክህሎት ልማት ከተቀረው ዓለም አኳያ ያለችበትን ደረጃ ማየት የሚያስችልና ልምድና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በየሁለት ዓመቱ በኦሎምፒክ መልክ የሚካሄድ የዓለም የክህሎት ወድድር መኖሩን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በዚህ መድረክ ዓለም አቀፍ ልምዶች የሚቀሰሙበት፣ የኢንዱስትሪ ትስስር የሚፈጠርበት እና የክህሎት ሽግግር የሚደርግበት በመሆኑ የተሻሉ ልምዶችን እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
በመጪው መስከረም ወር ላይ በፈረንሳይ፣ ሊዮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በሶስት የሙያ መስኮች የምትሳተፍ መሆኑን ክብርት ሚኒስትር በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

Read More Âť
News

ሰፋፊ፣ ዘላቂና ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ …

ሰፋፊ፣ ዘላቂና ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከመጣንበት መንገድ የተለየ ፈጣንና ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ይጠበቅብናል
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ እየተገበራቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎትሚኒስቴር ለዜጎች ሰፊና ውጤታማ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ ከሚገኙ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በሀገራችን ያለውን ሰፊ ፍላጎት የሚመጥን ስራ መስራት ይጠይቃል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ሰፋፊ፣ ዘላቂና ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን በብዛት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም ከመጣንበት መንገድ የተለየ ፈጣንና ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

Read More Âť
News

የኢፌዴሪ ተክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአይሶ 9001፡2015

የኢፌዴሪ ተክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአይሶ 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት ሆነ፡፡
የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፍኬቱ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ እንየው ለኢፌዴሪ ተክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ኢኒስቲትዩት በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር የተቀመጡ መስፈርቶች አሟልቶ የሰርተፍኬት ባለቤት በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በተቋሙ ጥራት ቀጣይነት ባለው መልኩ ባህል እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ሚኒስቴሩ በየደረጃው የሚገኙ ተቋማትና ባለሙያዎች ጥራት ባህላቸውን ያደረጉ፣ ራሳቸውን ያዘመኑና ከወቅቱ ጋር የሚራመዱ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት መሆን የተቋማቱ እና ከተቋመቱ የሚወጡ ባለሙያዎች በየትኛውም አለም ተቀባይነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋሙ የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት መሆኑ የአሰራር ወጥነት እንዲኖር፣ የሰራተኛ ብቃት ለማሳደግ፣ ምርታማነትን ለመጨመር እና የኢንስቲትዩቱን ግብ ለማሳካት ያለው ፋይዳ የጎላ ገልጸው ለስኬቱ አስተዋጽዎ የነበራቸው አካላትን አመስግነዋል፡፡

Read More Âť
News

የታሰበውን ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የቅንጅት ሥራና ምክክር ወሳኝ ነው፡፡ ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ- መስተዳድር

የታሰበውን ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የቅንጅት ሥራና ምክክር ወሳኝ ነው፡፡

ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ- መስተዳድር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላት ጋር በዘርፉ ተልዕኮና ሀገራዊ ግቦች ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በዘርፉ ተልዕኮ፣ ሀገራዊ ግቦች እና ግቦቹን ለማሳካት የአመራሩ ሚና ላይ ያተኮረ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ- መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጸት፤ ክልሉ በርካታ የልማት ፀጋዎች አሉት፡፡
እነዚህን ፀጋዎች በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ሲሆን የታሰበውን ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የቅንጅት ሥራና ምክክር ወሳኝ ነው ብለዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ከግምት በማስገባት እያከናወነ ያለው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት ክቡር ርዕሰ-መስተዳድሩ ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ ለመስራት ትክክለኛውን አቅጣጫ በመያዝ ሰርቶ የሚያሰራ አመራር እንደሚያስፈልግ ጨምረው ገልፀዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፣ የተቀረፁት አዳዲስ እሳቤዎች በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የነበሩ የተከማቹ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ አንደ ሀገር ያሉብንን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ስብራቶችን መጠገን የሚያስችል አቅም ያላቸው ናቸው።
ይህን በአግባቡ ተረድቶ በፍጥነት፣ በጥራትና በብዛት ተግባራዊ የሚያደርግ አመራር ወሳኝ ነው ብለዋል።
የካቢኔ አባላቱ በበኩላቸው መድረኩ ዘርፉ ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ጠቅሰው በዘርፉ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት ርብርብ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው፡፡
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሎ ሙፈሪሃት ካሚል እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ – መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝነተዋል፡፡
በመድረኩ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ እንዲስሪ ግንኙነት ዙሪያ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን በማጽናት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስለሚቻልበትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ወይይትይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም

Read More Âť
News

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር…

” #ክሂሎት ”
ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ፣ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ በነበሩበት ወቅት “ክሂሎት” በሚል ርዕስ መፅሀፍ ማሳተማቸው ይታወቃል።
ይህንኑ መፅሀፋቸውን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ በመተርጎም በድጋሜ አሳትመዋል::
ይህንን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕትም ሚንስትር መስሪያ ቤቱ በክህሎት ልማት ዘርፉ በማጣቀሻነት እንዲያገለግል ለሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስረክበዋል።
ክብርት ሚኒስትር መፅሀፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት፣ ክህሎት ከፍላጎትና ምኞት ወደ ስኬት የመሻገሪያ ድልድይ ነው::
የብዙዎችን ምኞት እና ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት በክህሎት ልማቱ ዘርፍ መሰል የማጣቀሻ መጽሀፍት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ቢሆንም በሀገራችን ምሁራን የተዘጋጁ ማግኘት ቀላል አይደለም።
ፀሀፊው ዘርፉን የመሩና እንደ ሀገር በመስኩ ያሉ ዕድሎችንና ተግዳሮቶችን በአግባቡ የለዩ እንዲሁም በመስኩ ያካበቱትን ሰፊ ልምድ ያካፈሉበት እንደመሆኑ ለዘርፉ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።
ባላቸው የተጣበበ ጊዜ ይንን መጽሐፍ በማዘጋጀት ለንባብ በማብቃታቸው ያላቸውን አድናቆት የገለፁት ክብርት ሚኒስትር መጽሐፉን ለዘርፉ በማበርከታቸው ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

Read More Âť
News

ለ43,500 ሰዎች የሥራ እድል!…

ለ43,500 ሰዎች የሥራ እድል!
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ የግብርና ናሙና ቆጠራ ያከናውናል፡፡ስለሆነም በቀበሌው የሚሰማሩ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ መረጃ ሰብሳቢዎችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት(ሌበር ማርኬት ፖርታል- E-LMIS) በመጠቀም ከመላ የሀገሪቱ ክፍሎች 43,500 ሰራተኛ ይፈለጋል። ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ አንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይዛችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- የስታቲስቲክስ መረጃ ሰብሳቢ
ብዛት፡- 43,500
ፆታ ፡- ጾታ አይለይም
የሥራ መደቡ ዓላማ ፡-ጥራቱን የጠበቀ የገጠር/ከተማ የቤተሰብ/ባለይዞታ የግብርና መረጃ መሰብሰብ እና ወደ ሰርቨር መላክ

Read More Âť
News

ከ16 በላይ የሆኑ የእህል ዘሮችን መውቃት የሚያስችለው ማሽን …

ከ16 በላይ የሆኑ የእህል ዘሮችን መውቃት የሚያስችለው ማሽን
ታምራትና ጓደኞቹ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች ህልም ዕውን ለማድረግ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል የተሰባሰቡት እኒህ ወጣቶች የአርሶ አደሩን ህይወት የሚያቀል የግብርና ማሽን አስራ ሁለት ሆነው አንድ ቡድን በማዋቀር በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ማሽኑ እህል መውቃት እና ጥራጥሬ መፈልፈል የሚያስችል በመሆኑ የአርሶ አደሮችን ጉልበትና ጊዜ ከመቆጠብ አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
አርሶ አደሩ ምርቱን ከማሳ ላይ ሰብስቦ ወደ ማሽኑ ማስገባት በቻ ነው የሚጠበቅበት ፡፡ ገላባ በማንሳት ፣እብቅ በማራገብ አይደክምም፡፡
በሌላ በኩል ወንፊት የተገጠመለት በመሆኑ ገለባና አላስፈላጊ ነገሮችን መለየት ይችላል፡፡ ይህም የእናቶች ድካም ለመቀነስ ያስችላል፡፡
‹‹የእኛ ማሽን ከውጭ ከሚገባው እና አሁን ገበያ ላይ ካለው በዋጋ፣ በጥራት እና በአገልግሎት አሰጣጡም በጣም የተሻለ ነው›› የሚሉት ወጣቶቹ ከውጭ የሚገቡት ማሽኖች በአብዛኛው እንድ ዓይነት እህል ብቻ የሚወቁ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ጤፍ የሚወቃ ከሆነ ማሽላ ላይወቃ ይችላል ፤ በቆሎ ወይም ሩዝ የሚፈለፈል ከሆነ ሌላ ነገር ላያደርግ ይችላል ፡፡
እነ ታምራት ያመረቱት ማሽን ግን 16 ዓይነትና ከዚያ በላይ የሆኑ እህሎችን መውቃት እንደሚችል ይገልፃሉ፡፡ ሌላው ማሽኑን ልዩ የሚያደርገው ተበታትኖ የሚታሰርና የሚፈታታ እንደገናም በቀላሉ መገጣጠም የሚቻል መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሁኔታውም ማሽኑን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማንቀሳቀስ ምቹ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች አካባቢያዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማሽኑ በጄኔሬተር ፣ በጸሐይ (በሶላር) እና በኤሌክትሪክ ኃይልን በመጠቀም መስራት የሚችል መሆኑ ደግሞ ችግር ፈቺነቱን የላቀ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
ታምራትና ጓደኞቹ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተመቻቸው የሠመር ካምፕ ፕሮግራም ተሳታፊ በመሆናቸው የፈጠራ ሥራቸውን የበለጠ ለማጎልበት እንደቻሉ ይገልፃሉ፡፡
የሠመር ካምፕ ቆታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የራሳቸውን ካምፓኒ የማቋቋም ዕቅድ ይዘዋል፡፡ በቀጣይም ያመረቱትን ማሽን ወደ ተጠቃሚው ደርሶ የአርሶ አደሩ ችግር ሲፈታ ለማየት በእጅጉ ጓጉተዋል፡፡ በእህል አሰባሰብ ወቅት የሚከሰተው የምርት ብክነት ተወግዶ አርሶ አደሩ በድካሙ ልክ ተጠቃሚ የሚሆንበትንና የዜጎች የምግብ ዋስትና የሚረጋገጥበትን ጊዜም በናፍቆት ይጠብቃሉ፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
somSOM
Scroll to Top