Mols.gov.et

mols admin

News

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት”

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት”
“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ የአሰልጣኝ መምህራኖች ስልጠና ተጀመረ፡፡
በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የአሰልጣኞችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት ማዘጋጀት ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
በዚም 17 የስልጠና ማዕከላት 24 ሺህ የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ
ነሃሴ 22/2016
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Read More Âť
News

24 ሺህ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነገ ይጀመራል፡- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

24 ሺህ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነገ ይጀመራል፡- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
******************
ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ 24 ሺህ ገደማ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡
የዘመኑ የሥራ ገበያው የሚፈልገውን እውቀትና ክህሎት የተላበሱ ባለሙያዎችን ከማፍራት አኳያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ሚንስትሯ ገልፀዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ያሉት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፤ የሥልጠና ጥራትንና አግባብነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ዘርፉ ለሀገራዊ የብልጽግ ጉዞ የሚጫወተውን ሚና ለማላቅ ያለመ መሰረት ሰፊ ሪፎርም ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡
“በዘርፉ ያሉን አሰልጣኝ መምህራን የኢንዱስትሪው አማካሪ፣ አስተባባሪ እና ባለሙያም ጭምር በመሆናቸው በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት ከመሙላት ባሻገር የየአካባቢውን ችግር ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ረገድ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው” ብለዋል፡፡
የአሰልጣኞች መድረክ ዓላማ ግንዛቤን ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት እንዲዘጋጁ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
ከነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው መድረክ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ አሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃትና በትጋት እንዲከታተሉ የስራና ክህሎት ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read More Âť
News

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትብብር …

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትብብር በፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳርን ምቹ ለማድረግ ያለመ ስልጠና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች መሰጠት ጀምሯል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ- መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰውና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Read More Âť
News

በጀርመኗ ላይፕዚግ የደመቀው የእንጦጦዋ ፍሬ …

በጀርመኗ ላይፕዚግ የደመቀው የእንጦጦዋ ፍሬ …
አዲስ አበባ በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ አደባባይ እንደተሰየመላትና በሁለቱ የእህትማማች ከተሞች አጋርነት 20ኛ ዓመት የማክበር ስነ-ስርዓት ላይ ተመርቆ ስለመከፈቱ ተዘግቧል፡፡
በታሪካዊቷ የላይፕዚግ ከተማ ይህ አደባባይ መሰየሙ በሁለቱ ከተሞች ብቻ ሳሆን በሀገራቱ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር ነው፡፡
ለመሆኑ የሁለቱ የእህትማማች ከተሞች መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነ የተነገረለት ይህ አደባባይ ላይ የቆመው ሀውልት የተቀረፀው በማን ነው? የሚል ጥያቄ አንስተው ከሆነ መልሱ ወደ አዲስ አበባ ይመልስዎታል፡፡
ፍሬሽወይን እንድሪስ ትባላለች፡፡ በታሪካዊው እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኤስቴቲክስ ስልጠና ዘርፍ የስነ-ውበት ሠልጣኝ ናት፡፡ ባለፈው ዓመተት በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ በተካሄደው የሰዓሊያን ውድድር ላይ ተካፍላለች፡፡
በዚህም በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ 25 ተወዳዳሪዎች መካከል 1ኛ በመውጣት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች፡፡ እንሆ ዛሬ አሸናፊ የሆነችበት የጥበብ ሥራዋ የሁለቱ ከተሞችን አስተሳስሮ በላይፕዚግ ከተማ በኩራት ለመቆም ችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፍሬሽወይን እንድሪስን ሥራዋ ከፍ ባለ ደረጃ በመቀመጡ እንኳን ደስ ያለሽ ለማለት ይወዳል።
በክህሎት ልማቱ ላይ እየሰጡት ላለው ቁርጠኛ አመራር ለውጥ እያመጡ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን፣ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮን እንዲሁም የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክን ኮሌጅ አመራርና ባለሙያዎች በሙሉ ምስጋና ይገባቹኋል፡፡

Read More Âť
News

የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶችና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶችና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ማሰልጠን ፣ መሸለምና ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ የብሩህ -ኢትዮጵያ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በይፋ አስጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶችንና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡
በውድድሩ ከመላ ኢትዮጵያ በየደረጃው በተካሄዱ ውድድሮች አሸናፊ የሆኑ 150 ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪዎቹ የኢትዮጵያ ተስፋዎች ናቸው ብለዋል፡፡
የብሩህ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በየዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትሯ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮም የውድድሩን ተደራሽነት በመላ ኢትዮጵያ የማስፋት ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
የንግድ ፈጠራ ሃሳብን ጨምሮ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባካሄዳቸው የተለያዩ ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ወደ ምርት ገብተው የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈቱ የሚያስችል አዲስ ፕሮግራም ዕውን መደረጉንም ክብርት ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡
ከ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በልዩ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶችንና ቴክኖሎጂስቶችን በአንድ ማዕከል በማሰባስብ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን የማሻሻል ብሎም ቴክኖሎጂዎቻቸውን ወደ ሰፊ ምርት የማስገባት ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም አስረድተዋል፡፡
በፕሮግራሙ አንድ ዓመት ቆይታ አዳዲስ ተሞክሮዎች የተገኙበትና የሥራ ፈጣሪዎቾች ሃሳብ ወደ ፍሬ የተቀየረበት እንደነበረም ክብርት ሚኒስትር አመላክተዋል፡፡

Read More Âť
News

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከስልጠና ባለፈ ተልዕኳቸው ተጨባጭ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተጠቆመ

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከስልጠና ባለፈ ተልዕኳቸው ተጨባጭ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተጠቆመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በምህንድስና ልህቀት ማዕከል እየተሰሩ ያሉ የውጭ ምርት መተካት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ያሉበትን ደረጃ እንዲሁም ሚኒስቴሩ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላስገነባቸው ቤቶች የሚሆኑ የቤት ቁሳቁሶች ዝግጅትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በዚህም ሥራው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ክብርት ሚኒስትር በዘርፉ የተደረገው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ያመጣውን ውጤት ማሳያም እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከሥልጠና ባለፈው ተልዕኳቸው የሥልጠና ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው የአካባቢያቸውን ችግር እየፈቱ የውስጥ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ እና የውጭ ምርቶችን ሊተኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን እየሰሩ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ መደረጉንም ክብርት ሚነስትር አንስተዋል፡፡
ይህም ተጨባጭ ውጤት እየተገኘበት ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር በክረምት በጎ ፈቃድ ለተገነቡት ቤቶች የሚሆኑ ግብዓቶችን በአጭር ጊዜ በጥራት እያመረቱ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

Read More Âť
News

ለሥራና ክህሎት እንዲሁም ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የ “Public Entrepreneurship and Innovation” ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

ለሥራና ክህሎት እንዲሁም ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የ “Public Entrepreneurship and Innovation” ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::
ለሚኒስቴሩ ተጠሪ በሆነው የኢትዮጵያ ኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲቲዩት (EDI) እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠና በህዝብ አገልግሎት ዘርፍ የፈጠራ፣ የትብብር እና የለውጥ ተግባራትን የማዳበር ዓላማ ያለው ነው።
ስልጠናው ፈጠራና ፍጥነት በታከለበት አግባብ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የተቀመጡ ግቦችን ስኬት ማላቅ የሚያስችል ሲሆን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ የተወጣጡ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡

Read More Âť
News

ውይይቱ በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት የማምጣት አቅም ስላለው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቆመ

ውይይቱ በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት የማምጣት አቅም ስላለው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቆመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማኅበረሰብ አቀፍ የሥራ ባህልና ምርታማነት የውይይት የአስተባባሪዎች የጋራ መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ በየክልሉ የተካሄዱ የማህበረሰብ አቀፍ ምክክሮችና ውይይቶች ያመጡት ውጤትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በዚህም የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት በሚል መሪ ሀሳብ የአመቻቾች የአሰልጣኞች ስልጠና ወስደው ተግባራዊ ያደረጉ አመቻቾች ውይይቱን ላልጀመሩ ለአማራና ለትግራይ ክልል እንዲሁም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
ውይይቱ በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት የማምጣት አቅም ስላለው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ እና ለዚህም በየደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ለምክክሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡
የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀመራቸው ሀገራዊ ሪፎርም ሥራዎች አንዱ ሲሆን ውይይቱ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰብ ድረስ በሙያና ሙያተኛ፤ በሥራና ሠራተኝነት እንዲሁም በታታሪነትና ሠርቶ መለወጥ ላይ አውንታዊ እይታ በመፍጠር ምርታማነትን ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

Read More Âť
News

ኢትዮጵያ በዓለም አውትሶርሲንግ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ኢትዮጵያ በዓለም አውትሶርሲንግ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አውትሶርሲን ማህበር እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ኘሮግራም ጋር በጋራ ያዘጋጁት በኢትዮጵያ ቢዝነስ ኘሮሰስ አውትሶርሲንግ ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዜጎች ከሀገራቸው ሳይወጡ በትልልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አውትሶርስ በተደረጉ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ለማስቻል የባለድርሻ አካላት ውጤታማ ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ከዘርፉ ሀገራችን እንድትጠቀምና ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥር የተጀመሩ የዲጅታል ክፍያ ስትራቴጂና የስታርት አኘ አዋጅ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በየትምህርት ተቋማቱ ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች ለዘርፉ ሰኬት መጠቀም ይገባል ብለዋል።
ለዘርፉ ስኬት ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ፣ አይሲቲ ፓርክ፣ የኢንተርኔት መሠረት ልማት የመሳሰሉ ተግባራት ለማሟላት እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።
ዘርፉ በትኩረት ከተሰራበት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር ለሀገር የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ መሆኑን ተገልጿል።
በፍረንጆቹ 2023 የዓለም አቀፍ አውትሶርሲንግ ኢንዱስትሪ ወደ 245 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስመዝግቧል፣ በ2030 ወደ 525 ቢሊዮን ዶላር ሊያድግ እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉ።
በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረገው 5 ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ደግሞ ለዚህ ዘርፍ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርና እና ብቁና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማቅረብ ያግዛልም ተብሏል ።

Read More Âť
News

አይሶ 9001፡2015- ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽነት ለተላበሰ አገልግሎት

አይሶ 9001፡2015- ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽነት ለተላበሰ አገልግሎት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአይሶ ትግበራ ኮሚቴ አባላት ካሳንቺስ የሚገኘውን የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት የጥራት ሥራ ዓመራር አይሶ 9001፡2015 አተገባበር ምልከታ አደረጉ፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ የተመራ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የጥራት ሥራ አመራር አስተግባሪ ቡድን በካዛንቺስ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተገኝቶ የ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ያለበትን ደረጃ በየሥራ ክፍሎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
ዘርፉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተገልጋዮች የሚስተናገዱበት እንደመሆኑ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማርካት የ ISO የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት የተቀመጡ ስታንደርዶችን በመተግበር ፈጣንና ቀልጣፋ፣ ግልጽነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገልጿል።
በተለይ አገልግሎቱን ለማዘመን የተጀመረው ( የወረቀት አልባ ሥራ፣ የአውቶሜሽን፣ የኦን ላይን ምዝገባ፣ የሰነዶች ስርጭትና ዶኩመንቴሽን) የዲጂታይዜሽን ሥርዓት በ ISO የጥራት ስታንደርደ መሰረት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ አሳስበዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሰራሩን በ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት መሰረት ለመምራት እና የአሰራር ወጥነት እና የሥራ ቅልጥፍና ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለለት አይሶ 9001፡2015 በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በአሁን ወቅት የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተሰጠ ቢገኝም የሚሰጡ አገልግሎቶች በአይሶ ስታንዳርድ እንዲፈጸሙ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማነቱን ያሳድገዋል ተብሏል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
oroORO
Scroll to Top