Mols.gov.et

bini

News

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን አስመልክተዉ ከተናገሩት፡-

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን አስመልክተዉ ከተናገሩት፡-
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተመሰረተ አንድ ዓመት ቢሆንም እጅግ አመርቂ ስራ ከሚሰሩ ተቋማት አንዱ ነዉ፡፡
በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ 10 ዓመት እንደቆየ ተቋም እራሱን አደራጅቶ ለረዥም ጊዜ የሁላችንም ጥያቄ የነበረዉ የስራ መረጃ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የመስራት ስራ ጀምረናል፡፡
ይህ ደግሞ በየአካባቢዉ በየእለቱ እየተፈጠረ ያለ ስራ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ያስችለናል፡፡
በዚህ ቴክኖሎጂ ታግዘን እንደ አደጉት ሀገራት በየእለቱ ስንት ሰዉ ስራ እንዳገኘ፣ ስራ እንደቀየረ እና እንደተመዘገበ ትክክለኛ መረጃ መግኘት እንችላለን፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ ስራ የሰዉ ያለህ ብሎ ይጮሃል ሰራተኛዉ ደግሞ የሥራ ያለህ ብሎ ይጮሃል ጠፍቶ የነበረዉ ድልድይ ሆኖ የሚያገናኝ አካል ነበር፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተቋቋመዉ ሥራዉ እና ሰሪዉን ድልድይ ሆነዉ እንዲያገናኝ ነዉ፡፡

Read More Âť
News

የግሉ ዘርፍ ተስፋ ሰጪ የሆነ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርህያት ካሚል ገለፁ።

የግሉ ዘርፍ ተስፋ ሰጪ የሆነ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርህያት ካሚል ገለፁ።
ሚኒስትሯ ይህን የገለፁት በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘውን የካርቪኮ ጨርቃጨርቅ ማምረቻ ፋብረካን በጎበኙበት ወቅት ነው።
በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው የካርቪኮ ጨርቃጨርቅ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ዘመናዊ ማሽኖችን ከመትከል ባሻገር ሰራተኞቹን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ስልጠናዎች እንዲበቁ አድርጓል፡፡
የስራ ላይ ደህንነትና ጤንነትን እንዲሁም የአካባቢ ደህንነትን ለመጠበቅ ድርጅቱ እያደረገ ያለው ጥረት በተሞክሮነት የሚነሳ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ሙፈርህያት ይህ ጥረት ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆንና የግሉ ዘርፍ ተስፋ ሰጭ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የሚያመላከት ነው ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር አጉስቲኖ ፓሌሲ ተገኝተዋል፡፡

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻን ጨምሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እንየው ጌትነትና የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በመከላከያ ሚኒስቴር ተገኝተው ድጋፉን ለክብርት ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉጂ አስረክበዋል፡፡
እስከ አሁን የተደረገው ድጋፍ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብና ቀሪው በአይነት የተበረከተ ነው፡፡

Read More Âť
News

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤ ከማሰልጠንና ዳቦ በልቶ ከማደር ያለፈ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል በመገንባት ምርታማነትን መጨመር እና ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር ነው

ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ዘላቂ ጉዞን በአዲስ አስተሳሰብ መቃኘትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ጀምረዋል።
በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሀገረ መንግስት እና የሀገረ ብሔር ግንባታ ችግሮችን አበይት ተግዳሮቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሀገረ መንግስት ግንባታ በዋናነት ነፃና ገለልተኛ ተቋማት መገንባትን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ተቋማትን የስርዓት ሳይሆን የዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የለውጡ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ሀገርና ህዝብ ዘመን ተሻጋሪ በመሆናቸው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ገልፀዋል።
ሀገር እና ህዝብን ማዕከል በማድረግ በተሰሩ ሥራዎች ሩቅ የነበሩ ተቋማትን ማቅረብ መቻሉን የተናገሩት ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት የሰው ኃይልን ዝግጁ አድርጎ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ምን አይነት መዋቅራዊ ችግርን መፍታት ይጠበቃል ለሚለው መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ሀገር ወዳድ እና ዝግጁ ትውልድ መገንባትም ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ሲገልፁ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከማሰልጠንና ዳቦ በልቶ ከማደር ያለፈ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል በመገንባት ምርታማነትን መጨመር እና ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል መቀየር ነው ብለዋል ።

Read More Âť
News

“የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለቁመና በመመልከታችን ተደስተናል።”

“የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለቁመና በመመልከታችን ተደስተናል።”
ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር)
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፎች ከደህንነት ተቋማት ጋር መስራትን መሰረት ያደረገ ጉብኝት አካሂዷል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዋናውን መስሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የመከላከያ ዋናው መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያውያን አልፎ አፍሪካውያንን የሚሰበስብ የሁሉም ቤት ነው።
ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት እና በሥራ ቦታ ደህንነት በለየናቸው መስኮች ጠንካራ ሥራዎችን በጋራ መስራት ጀምረናል ያሉት ክቡር በከር ሻሌ(ዶ/ር) የደህንነት ተቋማት የሀገራችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ዋስትና በመሆናቸው የተደራጁበትን ዘመናዊ ተክለ ቁመና በመመልከታችን ተደስተናል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሠራተኞችም ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በታጠቀው እና የኢትዮጵያን ልክ በሚያሳይ መልኩ በተደራጀው መከላከያ ሠራዊት ዋና መስሪያ ቤት ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

Read More Âť
Announcements

Call for application

#Ahun Round 2 High Growth Digital Startups Incubation Program
Ministry of Labor and Skills in collaboration with the UNDP invites digital startups with innovative business solutions for the #Ahun2022 round 2 call.
#Ahun is a 4-month incubation program for digital business ideas to be incubated and secure a seed funding.
Please follow the link to apply: https://enkopa.org/high-growth/
Or use P.O. Box 25534
Application Deadline: July 31, 2022

Read More Âť
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገልግሎቱን ለማዘመን ያደረገውን ዝግጅት ለተለያዩ ዘርፎች የክልል አመራሮች አስጎበኘ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች ተቋሙ የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ በማድረግ ለአገልግሎት ምቹ የሆነውን ህንፃ እና ያበለፀጋቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለክልል አመራሮች እና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች አስጎብኝቷል።
በአዲስ አበባ በተለምዶ ላምበረት በሚባለው አካባቢ ከዚህ ቀደም ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ሲገለገልበት የነበረውን ሕንፃ ለሥራው በሚመች መልኩ መዘጋጀቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የገለፁ ሲሆን ቦታው ዘመናዊ የቢሮ አስተሳሰብን የያዘ እና ደረጃውን ለጠበቀ የቢሮ አደረጃጀት ምቹ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ሕንፃ አገር በቀል ቁሳቁሶችን እና የወጣቶችን ፈጠራ በመጠቀም የሥራ ባህል ማዳበርን እና የክህሎት ፅንሰ ሃሳብን በማጎልበት መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል ፡፡
ምርታማነትን እና ፈጠራን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀው የህንፃው ይዘት ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አኳያ የተደራጀ እንዲሁም ግልፅነት የተላበሰ መሆኑ ለሠራተኛውም ሆነ ለተገልጋዩ እርካታ የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የበለጸጉት የቴክኖሎጂ ውጤቶችም ተቋሙን ከማስተዋወቅ ባሻገር ለውስጥም ሆነ ለውጭ ተገልጋይ በቀላሉ መገናኘት እና ጉዳይን መፈፀም የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የክልል ቢሮ ኃላፊዎቹ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮቹ ላምበረት ከሚገኘው ዋናው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሕንፃ ባሻገር የሠራተኛ ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጥበትን እና እንደ አዲስ እየተገነባ የሚገኘውን ጊቢ ጎብኝተዋል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አሰግድ ጌታቸው እየተገነባ የሚገኘው ቢሮዎችን ከቴክኖሎጂ ያቀናጀ እና ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን የሚፈታ ቴክኖሎጂን ያጣመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለኤጀንሲዎችም ሆነ ወደተለያዩ አገራት ለሚደረግ ጉዞ ይፈጅ የነበረውን 30 ቀን ወደ 15 ቀን ለማምጣት የአሰራር ለውጦችንም ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Read More Âť
News

በአገር አቀፍ ደረጃ የአንተርፕርነርሺፕ ስልጠናን በወጥነት ለመስጠት የሚረዳ መመሪያ ርክክብ ተካሄደ

ድጋፉ የተገኘዉ ከጀርመን መንግስት (Kfw) ልማት ባንክ እና ከኖርዌይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን ርክክቡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የጀርመን ልማት ባንክ ኬ ኤፍ ደብልዩ (Kfw) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋማቱ አስረክበዋል፡፡
የግብዓት ርክክብ በተደረገበት ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የጀርመን መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ ልዩ ቦታ የሚሰጠዉ መሆኑን ገልጸዉ ባንኩ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዉጤታማ ለማድረግ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለዉም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብዙ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ አሁን የተደረገዉ ድጋፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ ስርዓተ ስልጠና ለማዘመን እንደሚያግዝ እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባደረገዉ ሪፎርም ስርዓተ ስልጠናው ከገበያ ፍላጎት የሚመነጭ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የጀርመን ልማት ባንክ (Kfw) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬከተር ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ በበኩላቸዉ ላለፉት ሃያ ዓመታት ጀርመን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ገልጸዉ በዘርፉ አመርቂ የሚባል ዉጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጉብኝት በባንኩ የሚደረገው ድጋፍ ምን ያህል ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጣቸውንም ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ኢንስትቲዩት ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ ከዚህ ቀደም ከሚደረጉ ድጋፎች ይህንን ለየት የሚያደርገዉ በዘርፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልፀው ድጋፉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በገፅ ለገፅ የስልጠና አሰጣጥ ስርዓት ሳይወሰን በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡
ከድጋፍ ርክክቡ ጎን ለጎን ከጀርመን መንግስት የ32 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚያስችል ስምምነትም ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች በአግሮ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ሥልጠና እንዲገኙ ለማስቻል ነው፡፡ ስምምነቱ በፓይለት ደረጃ በሦስት ክልሎች ማለትም በሲዳማ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ፓርኮች ውስጥ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top