Mols.gov.et

bini

News

ባለፉት 6 ወራት ከ 1.4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከክልልና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ አካሄዷል፡፡
በመድረኩ ባለፉት 6 ወራት 1.8 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ የዕቅዱን 81 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ55 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተገለፀው፡፡
የሥራ ዕድሉ የተፈጠረዉም 70 በመቶ ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም እና 30 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ በቅጥር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ከክህሎት ልማት አኳያም ነባር የሙያ ደረጃዎችን የመከለስና አዳስ የማዘጋጀት፣ አዲስ የምዘና መሳሪያዎች እና ተጨማሪ ቨርሽን፣ የስርዓተ ስልጠና እንዲሁም የማሰልጠኛ መሳሪያዎች የማዘጋጀት ሥራዎች በትኩረት መከናወናቸው ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በፌዴራል 5 እንዲሁም በክልሎች 525 ድርጅቶች ላይ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራ አመራር ሥርዓት ለመዘርጋት ታቅዶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የዕቅዱን 95 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ ነው የተጠቆመው።
ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያም ስርዓቱን ቀልጣፋ፤ ውጤታማ፣ የዜጎችን ክብር አስጠብቆ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከመዳረሻ ሀገራት ጋር ሁለትዮሽ ስምመነት መፍጠር ላይ ሲሰራ የቆየ 77 የሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጀችን ለስራ ዝግጁ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የስርዓተ ስልጠና ክለሳ እና የማሰልጠኛ መሳሪያ ዝግጅትም እንደተከናወነ ነው በመድረኩ የተገለፀው።

Read More »
News

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየዘረጋ መሆኑ ተጠቆመ።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየዘረጋ መሆኑ ተጠቆመ።

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ምክክርና ጉብኝት አካሂደዋል።

አምሳደሮቹ በተቋሙ መሰረታዊና ለውጥ አምጪ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ የዜጐችን ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

በመድረኩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየተዘረጋ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጠቁመዋል።

Read More »
News

”በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

”በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል”
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በዘርፉ ተወጥነዉ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እሳቤዎች ላይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሠው ሃብት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ዕድሎችና ፈተኛዎችን በመለየት ፈተናዎቹ ወደ ዕድል፤ ዕድሎችን ደግሞ ለመጠቀምና ወደ ዉጤት ለመቀየር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዘርፉን ስራዎች ግብ እንዲመቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

Read More »
News

ስምምነቱ የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የመመህራን አቅም በማጎልበት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ስምምነቱ የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የመመህራን አቅም በማጎልበት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር)
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቻይና አፍሪካ የሙያ ትምህርት ትብብር( CHINA-AFRICA VOCATIONAL EDUCATION ALLIANCE) ጋር የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ማላቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ፊርማ ተፈራርመዋል፡፡

የስምምነት ሰነድ ፊርማ የተፈራረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) እና የቻይና አፍሪካ የሙያና ትምህርት ትብብርን ወክለዉ ማርክ ጎንግ(ዶ/ር) ናቸዉ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በፊርማ ስነ-ስራት ወቅት፤ ስምምነቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለዉን ትብብር ይበልጥ የሚያሳድግ እና በጋራ አብሮ መስራት ያሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቻይና መንግስት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሰፊ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይህ ስምምነትም የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የመመህራን አቅም በማጎልበት፣ የ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልምድ መለዋወጥ እና በሌሎችም ዘርፎች አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የቻይና አፍሪካ የሙያ ትምህርት ትብብርን ወክለዉ ንግግር ያደረጉ ማርክ ጎንግ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ ቻይና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና በእጅጉ መጠቀሟን ገልጸዉ ልምዷን ደግሞ ለኢትዮጵያ ለማካፈል እና በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
ጥር 8/2015 ፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡
ለወቅታዊን ትኩስ የሥራና ክህሎት መረጃዎች
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols በመወዳጀት ይከታተሉን::

Read More »
News

የምንታወቅበት አፍሪካዊ የሆነ መለያ ያስፈልገናል’። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

የምንታወቅበት አፍሪካዊ የሆነ መለያ ያስፈልገናል’።
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
8ኛው የአፍሪካ አመታዊ የመሀንዲሶች ጉባኤ እና የአፍሪካ መሀንዲሶች ሣምንት ከጥቅምት 28 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንደተናገሩት አፍሪካ የማህበራዊ ሃብት ባለቤት ናት።
እነዚህን እሴቶች ታሳቢ በማድረግም የአፍሪካ ሴት መሃንዲሶችን አንተርፕርንሽፕና፣ የአዳዲስ ፈጠራዎች ባለቤት በማደረግ በከተማ ዲዛይን፣ በቤቶች ውበት፣ በሳኒቴሽንና በኮንስትራክሽን /ስማርት ሲት / በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡
ለዚህም ኢትዮጵያ ማሳያ አላት። ለአብነትም የቴሌኮም እና የትራንስፖርት መሰረት ልማት መስፋፋት ፣ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መታጠቃቸው፣ የአይ ሲቲ ፓርኮች መገንባታቸው እንዲሁም በቅርቡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የብየዳ ክህሎት ስልጠና የምትሰጥ ብቸኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሆናለች ፡፡
በቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት፣ የብየዳ ስልጠና ማዕከል ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የብየዳ ኢንስቲትዩት ብቁ የብየዳ ስልጠና ማዕከልነት የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት አግኝተናል፤ ስለዚህ በሌሎች አፍሪካ ሃገራትም በተመሳሳይ የተለያዩ የአዳዲስ ፈጠራና አንተርፕርንርሽፕ ሥራዎች በመኖራቸው አፍሪካን ተመራጭና በቀጣይ ተስፋ ያላት አህጉር ለመሆኗ ማሳያ ነው በልዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ የአፍሪካ ሴት መሃንዲሶች የየአገራቱን ጉልህ ችግር በአንክሮ ስለሚረዱ የሥርዓተ-ፆታ አለመመጣጠንን፣ በቴክኖሎጂ የበለጸገ ከተማ አንዲሁም ፈጣንና ቀላል የሆኑ መጓጓዣዎች፣ የቤትና የመሰረተ ልማት ግንባዎች ላይ ሴቶችን ከማሳተፍ ባለፈ ወደፊት ማምጣትና በአፍሪካዊያን ብቻ የተሰራ የምንታወቅበት አፍሪካዊ የሆነ ብራንድ መለያ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጋራ ዕቅድ ትግበራ ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጋራ ዕቅድ ትግበራ ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር አቶ ገ/መስቀል ጫላ ናቸው ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ስምምነቱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረታዊ ደረጃዎችን የሚያወጣና የሚመራ እንደመሆኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚከናወኑ ስራዎች ጥራትንና ተወዳዳሪነት ማዕከል ያደረጉ ትልቅ አብክቶ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር የንግድ ስርዓቱ የሚያዘምኑ ግቦችን ለመተግበር፣ በክህሎት ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጣሪነት አስተሳሰብ ላይ በጋራ የሚሰሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸዉን ገልጸዉ ለጋራ እቅዱ ተግባራዊነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ክቡር አቶ ገ/መስቀል ጫላ በበኩላቸዉ ስምምነቱ ለንግዱ ማህበረሰብ ተወዳዳሪነትና ቅልጥፍና ወሳኝ የሆነውን የሰዉ ሃይል ምርታማነት ከማጎልበት አንፃር ቁልፍ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡
በተለይም ወደ ንግድ ሥርዓቱ ለሚገቡ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠርና እና ስራ አጥነት ለመቀነስ ይህ የጋራ እቅድ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top