Mols.gov.et

የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይኖርብናል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ህዳር 2, 2024
የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይኖርብናል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች የዘርፊን አፈፃፀም ለማላቅ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የምክክር መድረኩን አጠናቋል፡፡ የማጠቃለያ መድረኩ ላይ “Perspective” በሚል ርዕሰ በዘርፉ ትልቅ ልምድና ተሞክሮ ባለው ለማ ደገፋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ ዘርፉ ሀገር ብዙ የምትጠብቅበት በመሆኑ ሥራ አጥነትን ጨምሮ የዘርፉ አንገብጋቢ ችግሮችን ለመቅረፍ አዲስ ዕይታና ልዩ ተነሳሽነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በየዓመቱ በርካታ ዜጎች ሥራ ፈላጊ ሆነው እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ሰለሞን በሥራ ፈላጊው ልክ ረጅም ርቀት መሄድና አንገብጋቢነቱን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይገባል። በቀጣይ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ግብዓትና ግብይት ላይ እንዲሁም የቤተሰብ ቢዝነስና የማህበረሰብ አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። ተቋማዊ ግባችንን ለማሳካት ሁሉንም አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ የጠቆሙት ክቡር አቶ ሰለሞን በየደረጃው በቅንጅት እንዲሠራ አሳስበዋል።
amAM
Scroll to Top