Mols.gov.et

የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች በቻይና…

ሐምሌ 28, 2025
የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች በቻይና አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ዓለምአቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የፈጠራ ውድድር ላይ አሸነፉ። በቻይና ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በኬኒያ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለምአቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የፈጠራ ውድድር (SEA-CICSIC 2025) እየተወዳደሩ የሚገኙት የክህሎት ኢትዮጵያ የፈጠራ ባለሙያዎች የብር ሜዳሊያ አምጥተዋል። ኤፍራታ ጥበቡ፣ ጽጌ በየነ እና ሀብቱ በየነ የብር ሜዳሊያ ያገኙት የሮቦት እጅ በመገጣጠም ውድድር ሲሆን ከዚህም ባሻገር የፈጠራ ስራቸውን ፕሮቶታይፕ ይዘው በመቅረብ ለውድድሩ ተጨማሪ ድምቀት ሆነዋል። በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አመቻችነት እየተሳተፉ የሚገኙት ተወዳዳሪዎች ባመጡት ድል የአገራቸውን ስም ከፍ አድርገው አስጠርተዋል።
amAM
Scroll to Top