የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ …
ጥቅምት 20, 2026
የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የጋራ ኃላፊነትና የተቀናጀ አሠራር ያስፈልጋል
ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብድልቋድር
የሥራ፣ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብድልቋድር ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ዘርፍ ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላትን የጋራ ርብርብን የሚጠይቅ ሀገራዊ ጉዳይ ነው፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው የሥራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን የሥራ ተሳትፎ ከማሳደግና የሰው ኃይልን አቅም ከመጠቀም ባለፈ፣ የሀገራዊ ምርታማነትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ዘርፉ የተጣለበትን ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደር መካከል የተቀናጀ የሥራ አፈጻጸምና የጋራ ተጠያቂነት መኖር እንደሚገባ አመልክተዋል።
የዘርፉ አመራሮች በመድረኩ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በግልጽነት በመገምገም፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥና ለታዩ ክፍተቶች የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ የቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማስፈጸም እንደሚሠሩ ይጠበቃል።
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።












