Mols.gov.et

ቦርዱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ውጤታማነት በየጊዜው እያደገ እንዲሄድ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስተር

መስከረም 6, 2024
ቦርዱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ውጤታማነት በየጊዜው እያደገ እንዲሄድ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስተር የፌዴራል ቋሚ የአሠሪና ሠራተኛ አማካሪ ቦርድ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በምክክር መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቦርዱ የሚያከናዉናቸውን ተግባራት ውጤታማነት ለማሳደግ ሚኒስትር መ/ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ መንግስት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በአሠሪዎችም ሆነ በሠራተኞች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል። የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በበኩላቸው በ2017 በጀት ዓመት የሦስትዮሽ ግንኙነቱን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን ሚኒስትር መ/ቤቱ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቀዋል ። በመድረኩ በአማካሪ ቦርዱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እና በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
amAM
Scroll to Top